334 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
የካቲት 22/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
ከየካቲት 14 እስከ 20 ቀን 2017 ዓ.ም በተደረገው ክትትል 334 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢ እና የወጭ የኮንትሮባንድ እቃዎች በሞያሌ፣ በአዋሽ እና ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች አማካኝነት ተይዘዋል፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ ጥራጥሬ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች ፣ መድኃኒት፣ የቁም እንስሳት እና የወጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡
የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ እና በበረራ የተያዙ ሲሆን የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 20 ተጠርጣሪ ግለሰቦች እና 11 ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
ምንጭ፡- የጉምሩክ ኮሚሽን