Postlar filtri


ለሚሊኒየም ኮ /ቻ አጠ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በሙሉ
የአድዋ በዓል ለማክበር እሁድ ከጧቱ 1ሰዓት ድረስ ቢራሮ አዳራሽ እንዲትገኙ ያስተላለፍነው መልዕክትመነሻችን ከት/ቤት ይሁን ስለተባለ ከጧቱ 1ሰዓትሚሊኒየም ት/ቤት እንድትገኙ ት/ቤቱ ያሳስባል፡፡
ት/ቤቱ


ማስታወቂያ
የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሁሉም ተማሪዎች በተማሩበት ሥርዓተ ትምህርት ይዘት ይዘጋጃል፡፡

የ2017 ዓ.ም ተፈታኝ ተማሪዎች ከ9ኛ - 10ኛ በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት፣ ከ11ኛ - 12ኛ ደግሞ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ናቸው። ነገር ግን በ2015 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በናሙናነት በተመረጡ ት/ቤቶች የስርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ ላይ የተሳተፉ ት/ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች 10ኛ ከፍልን በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ናቸው፡፡ በአማራ ክልል በ2016 የትምህርት ዘመን መፈተን ሲገባቸው በጸጥታ ችግር ምክንያት ሳይፈተኑ የቀሩና የ11ኛ ክፍልን በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ት/ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች በ2017 ዓ.ም የሚፈተኑ አሉ፡፡ በመሆኑም የ2017 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከላይ የተገለጹትን ሶስቱንም ነባራዊ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ባስገባ እና ሁሉንም የዘመኑን ተፈታኝ ተማሪዎች በማከለ መንገድ ስታንዳርዱን፣ ደህንነቱንና ሚስጢራዊነቱን ጠብቆ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል።

ስለሆነም የፈተና ዝግጅቱ፡-
1) ከ9ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከነባሩ ሥርዓተ ትምህርት፣
2) ከ10ኛ ክፍል በነባሩና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ተመሳሳይ ይዘቶች፣
3) ከ11ኛ ከፍል በነባሩና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ተመሳሳይ ይዘቶች፣
4) ከ12ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሰረት የሚዘጋጅ ይሆናል።

ከላይ የተዘረዘረው የዝግጅት ሂደት በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ላይ እንደተጠበቀ ሆኖ የኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነት ግን በስርዓተ ትምህርቱ አዲስ የተጀመረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በ12ኛ ክፍል ይዘት ላይ ብቻ ተመስርቶ የሚዘጋጅ ይሆናል።

በአጠቃላይ ሁሉም ተማሪዎች ከ9ኛ -12ኛ ክፍል በየተማሩበት የሥርዓተ ትምህርት ይዘት ላይ መመስረት ፈተናው እንደሚዘጋጅ አውቀው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

ስለሆነም ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ወላጆች፣ መምህራንና መላው የትምህርት ማህበረሰብ ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት!
የካቲት 2017 ዓ.ም


ለሚሊኒየም ት/ቤት ማህበረሰብ በሙሉ
2ኛ ሴሚስተር ትም/ የሚጀመረው ነገ በ3 /6/17 ዓ.ም ሲሆን
ከጧት ፈረቃ 11 ኛ ክፍሎች ያለበት
ከሠዓት ፈረቃ 12 ኛ ክፍሎች ይ ያሉበት መሆኑን እናሳውቃለን!!
ት/ቤቱ


በዚህ ፎርም መሠረት እስከ አርብ 30/05/17 ዓ.ም 3 ሰዓት ትም/ ክፍሎች ለም/ር /መምህር ገቢ አድርጉ !!






ለትምህርት ውድድር የሚሳተፉ ተማሪዎች ብዛት በሴክሽን ሁለት ተማሪዎች መሆናቸውን እናሳውቃለን።




ለመ/ራን በሙሉ
ከላይ በመግባት ነበሩ ደመወዝ፣ ደረጃ እንድሁም
ማዕረግ አረጋግጡ! ችግር ካላ ሪፖርት አድርጉ።
ት/ቤቱ




ማስታዎቂያ ለት/ቤቱ መምህራን በመሉ፤
አድሱን የደመወዝ ማሻሻያ ለማሳዎቅ አሁን የሚከፈላችሁን ደመወዝ የሚያሳይ፦
1-የደረጃ እድገት ደብዳቤ
2-የትምህርት ማሻሻል ደብዳቤ
3-የጂኤጂ ደብዳቤ
4-አድስ ቅጥር ከሆኑ የሙከራ ቅጥር ደብዳቤ
እስከ 30/3/17 ደረስ እንድታመጡ ት/ቤቱ መልክቱን ያስተላልፋል።


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish








በሚሊኒየም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 19ኛው የብሄር ብሄረቦች ቀን በዓል በት/ቤቱ ማህበረሰብ በደማቅ ሁኔታ 27 -03- 2017 ተከበረ ::









20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.