የተደበቀው ምስጢር dan repost
የሀገራችን ሰንደቅ ዓላማ
መቼ መጣ?
በማን መጣ?
እንዴትስ መጣ?
እነሆ
@TibebeEthiopia
እንደ ነገ ጥዋት ካሳ ሀይሉ ደረስጌ ማርያም ላይ ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ተብለዉ ንግስና ሊቀቡ አዳራቸዉን በጣም ጨንቋቸዋል ብልህ የነበረችዉም ባለቤታቸዉ ተዋበች አሊ ጭንቀታቸዉን ተረድታ ካሳ መከታየ ምነዉ አለቻቸዉ የጭንቀታቸዉ መንስኤም ነገ ስነግስ ለህዝቤ ምን ብየ ቃል ልግባለት? ነበር እንዲህም ነበር ያሉት "ይሄዉ እስከዛሬ በኔ ድካም ሳይሆን በእግዜር ፈቃድ እዚህ ደርሻለሁ ጠላቶቼንም እኔ ስሰነዘር እሱ ቀድሞ ይጥልልኛል ተመስገንም እለዋለሁ ስለትስ ባስገባለት ምን የከበረ ነገር አስገባለታለሁ" ግን አለ መይሳዉ! "ነገ ቅባቱን ልቀባ ነዉ ህዝቤም ከኔ እምነትን ይጠብቃል ምን ይዤ ልማልለት ምን ጨብጬ ልቁረብለት ምንስ ብየ ልናገር እስኪ መላ ካለሽ ተዋቡ በማተቤ እንዳልምል የባለሌጣ የስላሙም ናት ይቺ ሀገር በ ግዮን እንዳልምል የ ጉደር የ አዋሽ የ ተከዜ የጉማራ የ ሎንያ ሁሉም የኛዉ ነዉ የቱንስ አስበልጣለሁ በምን ልማልለት" አሉ ተዋበችም እህም አሉና "እስላም ብትል ሸማኔዉ አህመዴ ቦጋለ ትዝ አለኝ አሽከር አስጠራልኝማ የታለ ገብርየ" ካሣ ግራ ገባዉ ግን አይጠይቃትም "የታለ ገበርዬ" ብሎ አስጠራዉ ገብርዬም ከታንጉት ሙቅ እቅፍ ተላቆ ከነ ጋሻ ጃግሬዉ ገስግሶ ደረሰ ተዋቡም በወጉ እንኳን እጅ አልነሳችዉም "ደገኞቹ መንደር እጁ ወርቅ የሆነ አህመዴ ሚባል እጀ ወርቅ ሸማኔ አለ ሂድና ቃሌን ሳትጨምር ሳትቀንስ እንዲህ ብለህ ንገር በሀገር ሰማይ ላይ ሁሉም እንደሚያያት የማሪያም መቀነት አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ጥለት በጅህ ስትለካት ሁለት ክንድ የሆነች ባንዲራ ሰርቶ ነግ ማርያም ድረስ እንዲያመጣ" ብላ ግብፆች ከላኩላቸው መሐል የሃር የሆነውን ጥለት ሰጥታው ሂድ አለች ካሳም ፈገግ አለ ገብርዬም ከነ ጀሌዎቹ ቶሎ ወጥቶ ሂደ አህመዴ ቤትም ደረሰ አህመዴም የፈረስ ኮቴ ደጁን ሲረመርም ሰምተው ሰማዩ ሳይፈጅር ደሞ ማነው ብለው ደነገጡ "ቤቶች እንዴት አደራችሁ" አለ ገብርዬ ይበልጥ ተረበሸ ድምፁን ያቀዋልና ደነገጠ በሩን ሳይከፍት ገብርዬም ደጋግሞ ተጣራ የበሩን ግርግም ገፋ አድርጎ ብቅ አለ በድንጋጤም "ወይኔ ወንድሜ ጦርነት ዘምቶ ሞተ" ብሎ ሲጮህ ገብርዬ አቋረጠውና "ተዋበች ልካን ነው" ብሎ የተባለውን ነገረው አህመዴም ደስ አለው "ያገሬን ባንዲራ ያውም ለመይሳው በኔ ጥበብ ታሪክም አይረሳኝ" ብሎ እየዘለለ ወደ ቤቱ ገባ ከዛም ሚስቱን ቀስቅሶ ነገራት ከዘሃም ምርጡን ዘሃ እንድትመርጥለት ዝግ ዘሃው ተቋጥሮ ድምድም ተመትቶ ጥለቱ ተጥሎ በጌጥ ተሸልሞ በቶሎ ጨርሶ ለገብርዬ ተሰጠ ገብርዬም በቅሎውን ንሮ ሲሮጥ ገስግሶ ደረስጌ ማርያም ላይ ሆታው ሲቀልጥ አንድ ላይ ደረሱ ገብርዬም በህዝቡ መሀል ሰንጥቆ ለካሳ ባንዲራውን ሰጠው ካሳም ደስ አለው አሰራሩ ደነቀው ቁርጥማን አይንካህ ብሎም አህመዴን መረቀው መይሳውም ቅባቱን ተቅብቶ ለህዝቡ በሰንደቅ ዓላማው ምሎ ቃል ገባ ይህንም ህዝቡ ባየ ግዜ ምድር ቀለጠች ። በባንዲራው ማለ ለዚህም ነው ከመይሳው ጀምሮ አባቶቻችን ከባንዲራው በፊት እኔን ያስቀድመኝ ብለው በየዘመቻው ድባቅ ሲመቱ የኖሩት...!
ተፃፈ በ @Yibekal16