የወቶአደር ቅኔ
ከአምባው ላይ ቆሜ
ከሰላሙ ፍቅርሽ ትዝታን ቀስሜ
በተራራው አናት በተኙ ጉሞች ላይ
እንደእኔ ሆድ ብሶት ከሚያለቅሰው ሰማይ
መሀከል ላይ ቆሜ ትዝታን ሳስታምም
አልታየኝ ይሆናል ፂሜም ሲያቀመቅም
ችግር በቆፈረው በቀበሮ ጉድጓድ
የአረሩን ፉጨት በጣቶቼ ሳግድ
በእንዲህ ያለ ኑረት ያ ልቤ ቢዛክር
አይቻለው ጎኔ ሳያስብሽ ሊያድር
ፈገግታሽን ቋጥረሽ ላኪልኝ በአህያ
ውብ አይንሽን ላኪው ይደር ከእኔ ጉያ
ፈገግታሽ በሶዬ ህይወቴን ማቆያ
ስንደዶ ፀጉርሽን ላኪልኝ እባክሽ
የጠላት መትረየስ ሲንደቀደቅ ቢያድር ተከልዬ ልሽሽ
ውብ ከንፈርሽ ይምጣ ባይኔ ይበል ውልብ
ጠላት ማርኮ ከቦኝ ይሰማኝ የልብ ልብ
ትንፋሽሽን ላኪው ህመሜን ማበሻ
ይሆነኛል እና ለቁስሌ ፋሻ
አንቺ የአይኔ አበባ
በኔ ስጋት ምድር ወዲያ ዳር ያልሽው
ቅዠት ብቻ ሆኗል ሰሞኑን የማየው
እንጃ እኔን ዘንድሮ (፪)
የጥይት ዝናማት በኔ ባይዘንቡብኝ
ናፍቆትሽ ነው ቀድሞ አፈር የሚያለብሰኝ
ፍቅርሽ ጢያራ ነው ክንፍ አውጥቶ በሯል
ከጠላቴ በላይ ዙሪያዬን ከቦኛል
ናፍቆትሽ አዜብ ነው ያነጋግረኛል
በአድማስ ሹክሹክታ ድምፁን ያሰማኛል
ድምፁ ይሰማኛል
ድምፁ ይሰማኛል
በተራራው አናት በተኙ ጉሞች ላይ
እንደእኔ ሆድ ብሶት ከሚያለቅሰው ሰማይ
መሀከል ላይ ቆሜ ትዝታን ሳስታምም
ባክሽ ተሰቃየው ህይወት ሆናኝ አረም
እናልሽ አንቺዬ
#እኔ በሀገሬ ወቶአደር ነኝ አሉ
ለሀገራቸው ሲሉ ነፍሴን ከማይሉ
አጠገብ ምመደብ (፪ )
ስጋዬ ጦር ሜዳ ፍቅርሽን ያቀፈ
ልቤ ካንቺ ጋር ነው በናፍቆት ያደፈ
ልቤ ከኔ የለም ሆኗል ወጥቶ አዳሪ
ስጋ ብቻ ለጦር #ይህን_ጊዜ_ፍሪ_(፫)
✍️✍️ሲራክ
@ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹
@ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹
@ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹
ከአምባው ላይ ቆሜ
ከሰላሙ ፍቅርሽ ትዝታን ቀስሜ
በተራራው አናት በተኙ ጉሞች ላይ
እንደእኔ ሆድ ብሶት ከሚያለቅሰው ሰማይ
መሀከል ላይ ቆሜ ትዝታን ሳስታምም
አልታየኝ ይሆናል ፂሜም ሲያቀመቅም
ችግር በቆፈረው በቀበሮ ጉድጓድ
የአረሩን ፉጨት በጣቶቼ ሳግድ
በእንዲህ ያለ ኑረት ያ ልቤ ቢዛክር
አይቻለው ጎኔ ሳያስብሽ ሊያድር
ፈገግታሽን ቋጥረሽ ላኪልኝ በአህያ
ውብ አይንሽን ላኪው ይደር ከእኔ ጉያ
ፈገግታሽ በሶዬ ህይወቴን ማቆያ
ስንደዶ ፀጉርሽን ላኪልኝ እባክሽ
የጠላት መትረየስ ሲንደቀደቅ ቢያድር ተከልዬ ልሽሽ
ውብ ከንፈርሽ ይምጣ ባይኔ ይበል ውልብ
ጠላት ማርኮ ከቦኝ ይሰማኝ የልብ ልብ
ትንፋሽሽን ላኪው ህመሜን ማበሻ
ይሆነኛል እና ለቁስሌ ፋሻ
አንቺ የአይኔ አበባ
በኔ ስጋት ምድር ወዲያ ዳር ያልሽው
ቅዠት ብቻ ሆኗል ሰሞኑን የማየው
እንጃ እኔን ዘንድሮ (፪)
የጥይት ዝናማት በኔ ባይዘንቡብኝ
ናፍቆትሽ ነው ቀድሞ አፈር የሚያለብሰኝ
ፍቅርሽ ጢያራ ነው ክንፍ አውጥቶ በሯል
ከጠላቴ በላይ ዙሪያዬን ከቦኛል
ናፍቆትሽ አዜብ ነው ያነጋግረኛል
በአድማስ ሹክሹክታ ድምፁን ያሰማኛል
ድምፁ ይሰማኛል
ድምፁ ይሰማኛል
በተራራው አናት በተኙ ጉሞች ላይ
እንደእኔ ሆድ ብሶት ከሚያለቅሰው ሰማይ
መሀከል ላይ ቆሜ ትዝታን ሳስታምም
ባክሽ ተሰቃየው ህይወት ሆናኝ አረም
እናልሽ አንቺዬ
#እኔ በሀገሬ ወቶአደር ነኝ አሉ
ለሀገራቸው ሲሉ ነፍሴን ከማይሉ
አጠገብ ምመደብ (፪ )
ስጋዬ ጦር ሜዳ ፍቅርሽን ያቀፈ
ልቤ ካንቺ ጋር ነው በናፍቆት ያደፈ
ልቤ ከኔ የለም ሆኗል ወጥቶ አዳሪ
ስጋ ብቻ ለጦር #ይህን_ጊዜ_ፍሪ_(፫)
✍️✍️ሲራክ
@ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹
@ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹
@ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹