ማንም ይሁን ማን ማስረጃ በሌለው ነገር ላይ ከተናገረ ውሸትን ቀጥፏል። ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ውሸት ወደ አመፅ ወደ… ጀሀነም እንደሚመራ ነገረውናል።
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ኩራተኛ ማለት ሐቅን የማይቀበል ነው ብለዋል። አንድን ነገር በስማ በለው ውሸት መሆኑን ሳያውቅ ያስተላለፈ እና ያሰራጨ ሰው፣ ያ ወሬ ውሸት መሆኑ ሲነገረው "ተሳስቻለሁ፣ እውነት መስሎኝ ነው ያሰራጨሁት፣ ስህተት መሆኑን ስለተረዳሁ ላሰራጨሁት እና ለደረሳችሁ በጠቅላላ ተሳስቼ ለዋሸሁበትም ይቅርታ ሁላችሁንም እጠይቃለሁ" ነው ሊል የሚገባው አላህን ፈሪ የሆነ ሰው። ይሄ አጥፊውን አላህም ዘንድ ሰዎችም ዘንድ ያስከብረዋል።
አለበለዚያ በኩራት ጥፋቱን የማይቀበል፣ ሆን ብሎ የሚዋሽ፣ ትእቢተኛ፣ አመፀኛ ይሆናል። ይህን ስራ አንድ ሰው ሰራው፣ ተደራጅተው ሰዎች ሰሩት፣ በድርጅት ስም ሰሩት ወንጀል፣ ውሸት ከመሆን አይወገድም።
አላህን እንፍራ ሐቅ አለኝ ያለ ሰው አይዋሽም። ውሸት የአመፀኞች መንገድ ነው። ጀሀነም ያደርሳል።
https://t.me/SadatTextPosts