⚖️Shields Law🇪🇹 የህግ አገልግሎት / Legal service ⚖️


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Huquq


⚖️ Shields Law ⚖️.
ነፃ የህግ የማማከር አገልግሎት፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ የውል ፎርሞች፤ መፅሐፍቶች እዚሁ ያገኛሉ። Here on our channel, we provide Free legal Aid. You could alsk get access to laws, cassation decisions, job opportunity updates.
ለማስታወቂያ
👉@alexyoba21

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Huquq
Statistika
Postlar filtri


#የፌዴሬሺን_ምክር_ቤት_ውሳኔ_በዐይነ_ስውራን_ጉዳይ
ፌ/ም/መ/ቁ. 019/08

"የዳኝነት ሥራ ተፈጥሯዊ ባሕርይ  ማየት የተሳናቸው ሰዎችም ተመጣጣኝ ማመቻቸት ከተደረገላቸው ሊሠሩ የሚችሉት ሙያ ስለሆነ  'ማየት የተሳናቸው ሰዎች የዳኝነት ሥራን መሥራት አይችሉም' የሚል ልማዳዊ አሠራርን በመከተል ከዳኝነት ዕጣ ድልድል ውጭ በማድረግ በዐቃቤ ሕግነት የመመደብ ውሳኔ ማየት የተሳናቸው ሰዎች በመረጡት ሙያ የመሰማራት እንዲሁም ሕገ መንግሥታዊ የእኩልነት መብታቸውን የሚጋፋ ስለሆነ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 41(2)፣ 25 እና 9(1) መሠረት ተፈጻሚነት የለውም።" -የፌደሬሽን ም/ቤት የሕገ መንግሥት ትርጉም ውሳኔ ሰጥቷል።


የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ

አማራ ባንክ

1. የሥራ መደብ፡- Junior Attorney
የትምህርት ደረጃ፡- በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ
የሥራ ልምድ፡- አንድ ዓመት አግባብነት ያለው የሥራ ልምድ
የምዝገባ ጊዜ፡- እስከ ታኅሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም
የሥራ ቦታ፡- ባሕር ዳር፥ ደሴ፥ ጎንደር
የመመዝገቢያ መንገድ፡- የሚከተለውን ሊንክ ተጭነው ያመልክቱ 👉 https://vacancy.amharabank.com.et/

2. የሥራ መደብ፡- Senior Attorney
የትምህርት ደረጃ፡- በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ
የሥራ ልምድ፡- አምስት ዓመት አግባብነት ያለው የሥራ ልምድ
የምዝገባ ጊዜ፡- እስከ ታኅሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም
የሥራ ቦታ፡- አዲስ አበባ፥ ባሕር ዳር፥ ደሴ፥ ጎንደር
የመመዝገቢያ መንገድ፡- የሚከተለውን ሊንክ ተጭነው ያመልክቱ 👉 https://vacancy.amharabank.com.et/
https://t.me/ethio_Legal_Case


Vacancy Announcement for Fresh Graduates at Ethiopia Commodity Exchange (ECX)

Position: Junior Legal Service and Enforcement
Duty Station: Addis Ababa/Head Office

Job Requirements:
- Education: LLB (Bachelor of Laws)
- Experience: Not required

How to Apply:
All interested and qualified applicants are invited to submit a cover/application letter and an updated CV, along with relevant documents, via the link below.

https://docs.google.com/forms/d/13HoNSdoY4VYydv4LEO5dnTVk2G7sTZEyA2ytynjxOdI/edit

Deadline: On or before January 2, 2025.










Vacancy Announcement for Fresh Graduates

Ethiopia Commodity Exchange (ECX)

VACANCY ANNOUNCEMENT No. 08 – 2023/24 (External)

Position: Junior, Legal Service and Enforcement

Job Grade: 5

Duty Station: Addis Ababa/Head Office

Job Requirements:
Education: LLB
Experience: Not Required

How to Apply:
All interested and qualified applicants may send a cover/application letter and updated CV with relevant documents via in the below link

https://docs.google.com/forms/d/13HoNSdoY4VYydv4LEO5dnTVk2G7sTZEyA2ytynjxOdI/edit

Deadline: On or before January 02, 2025


https://t.me/ethio_Legal_Case


የፌደሬሽን_ምክር_ቤት_መዝገብ_ቁጥር_804_16.pdf
1.1Mb
“ጋብቻ በፍቺ ከፈረሰ በኋላ የቀድሞ ተጋቢዎች አብረው መኖር ከቀጠሉ በመካከላቸው ጋብቻ እንዳለ ይገመታል” የሚለው የሕግ ትርጉም በሕግ አውጭው የማይታወቅ አዲስ የጋብቻ አፈጻጸም ሥርዓትን የሚደነገግና በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 9(1) መሠረት ተፈጻሚነት የሌለው የሕግ ትርጉም ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፌደሬሽን ምክር ቤት በይ/መ/ቁጥር 804/16 ሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ.ም 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 3ኛ የሥራ ዓመት፣ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ የሰጠው ውሳኔ


ዋዜማ- በፍትሕ ሚንስቴር ከደምወዝ ጭማሪ፣ ከቤት፣ ከትራንስፖርትና ከተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች አለመሟላት ጋር ተያይዞ ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ ከ 3 መቶ በላይ ነባርና ልምድ ያላቸው ዓቃቤ ሕጎች ከመስሪያ ቤቱ በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ዋዜማ ከታማኝ ምንጮቿ ሰምታለች።

ዋዜማ ያነጋገረቻቸው በተቋሙ ከስምንት ዓመታት በላይ ያገለገሉ ከፍተኛ ዓቃቤ ሕጎች እንደገለጹት፣ በነዚህ ስምንት ዓመታት ውስጥ የደምወዝ ማስተካከያ የተደረገው አንድ ግዜ በ 2012 ዓ.ም ነው ብለዋል።

እየተከፈላቸው ያለው ክፍያ ከተሰጣቸው ተልዕኮ፣ ኃላፊነትና ከወቅታዊው የኑሮ ውድነት አንጻር እጅቅ ዝቅተኛ ነው ሲሉ ለዋዜማ የገለጹት ባለሙያዎቹ፣ በዚህም ምክንያት ሙያውን ወደው እና አክብረው እንዳይሰሩ “እንቅፋት ሆኖብናል” ሲሉ ገልጸዋል።

ከደምወዝ በተጨማሪ የቤት እና የትራንስፖርት ክፍያ ማስተካከያ ከተደረገላቸው ዓመታት መቆጠራቸውን ያነሱ ሲሆን፣ ባለሞያዎቹ በተደጋጋሚ አመልክተው መፍትሄ አለማግኘታቸውን አንስተዋል።

ዓቃቤ ሕጎቹ ለረጅም ዓመታት ሲጠይቁ የነበረው ሌላ ጥያቄ የቤት ጥያቄ መሆኑን ለዋዜማ ያስረዱ ሲሆን፣ ተቋሙን በሚንስትርነት ሲመሩ ከነበሩትና በቅርቡ ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሆነው ከተሾሙት ጌዴዎን ጢሞቴዎስ አንስቶ ከሳቸው በፊት ለነበሩት ሚንስትሮችም ጥያቄው ሲነሳላቸው ነበር ሲሉ አክለዋል። ሆኖም “ጥረት እያደረግን ነው፣ እየተነጋገርንበት ነው” ከሚሉ ማዘናጊያ ቃላት በዘለለ እስከ አሁን ድረስ ጥያቄያቸው መልስ አለማግኘቱን ተናግረዋል።

ዓቃቤ ሕጎቹ ለዋዜማ እንደገለጹት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ በፍትሕ ሚንስቴር ትይዩ ያለ ተቋም መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ ሆኖም በስሩ ላሉ ዳኞች በየካ ክፍለ ከተማ በተለምዶ መገናኛ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የመኖሪያ ቤት ገንብቶ ማስረከቡን ጠቁመዋል።

ሆኖም ፍትሕ ሚንስቴር ከላይ የተገለጹትን ጥያቄዎች ባለመመለሱ የተነሳ ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ ከ 3 መቶ በላይ ዓቃቤ ሕጎች በራሳቸው ፈቃድ ከሥራ መልቀቃቸውንና፣ አሁንም መልቀቂያ እያስገቡ ያሉ በርካታ ዓቃቤ ሕጎች መኖራቸውን ይናገራሉ።

ከሚንስቴር መስሪያ ቤቱ የለቀቁት ዓቃቤ ሕጎች በተቋሙ ውስጥ የረጅም ዓመታት ልምድ ያላቸው፣ ከባድ እና ውስብስብ የሚባሉ መዛግብት ሲሰሩ፣ ክርክር ሲያደርጉና ለውጤት ሲያበቁ የነበሩ ባለሙያዎች ናቸው ሲሉ ገልጸዋል።

ይህ ሁሉ ሲሆን በመስሪያ ቤቱ በኩል ልምድ ያለው ባለሙያ ለቀቀ ብሎ የመቆጨት፣ የመቆርቆርና የመጸጸት አዝማሚያ አለማየታቸው እንዳሳዘናቸው የሚገልጹት ዋዜማ ያነጋገረቻቸው ባለሙያዎች፣ ይህም በፍትሕ ስርዓቱ ላይ ሊያሳድር የሚችለውን አደጋ ቀላል አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።

ባለሙያዎቹ እንደገለጹት በርካታ የሚባሉ የወንጀል፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ይዘት ያላቸውን መዛግብት ላይ  ክርክር በማድረግ ከሥራ ሲወጡ ካለው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት የተነሳ በታክሲ መሳፈር ቅንጦት ስለሚሆን፣ እንደማንኛውን ዜጋ በከተማ አውቶቡሶች ተጋፍተን ነው የምንሄደው ሲሉ ለዋዜማ አስረድተዋል።

የእነሱ ሙያ ከሌላው የመንግሥት ሠራተኛ በብዙ ነገር እንደሚለይ የሚገልጹት ዓቃቤ ሕጎቹ፣ የጦር መሳሪያ ዝውውር፣ የግድያ፣ የስርቆት እና ሌሎችም የወንጀል መዛግብት ላይ እንደሚከራከሩ በመግለጽ፣ እነዚህ መዛግብትም በግል ሕይወታቸው ለጥቃት ሊዳርጓቸው የሚችሉና የደኅንነት አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ መሆናቸውን ያብራራሉ።

በጎረቤት አገራት ለዓቃቤ ሕጎች የሚከፈለው ክፍያና ጥቅማጥቅም እንዲሁም ለሙያው የሚሰጥው ክብር ከእኛ አገር ነባራዊ ሁኔታ ጋር ሲነጻጸር፣ ልዩነቱ የሰማይና የምድር ነው የሚሉት ባለሙያዎቹ፣ በዚህም ምክንያት ተቋሙ በርካታ ሠራተኞችን እያጣ እንደሆነ ገልፀዋል።

ምንጭ ዋዜማ ራድዮ


ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ መስከረም 12 ቀን 2017ዓ/ም ባወጣዉ የስራ ቅጥር ማስታወቂያ መሰረት የጽሁፍና የቃል ፈተና ወስዳችሁ የተወዳደራችሁ ከዚህ በታች ባለዉ ሰንጠረዥ መሰረት ዉጤቱን ስንገልፅ ለዜሮ ዓመት ከ1-15 ድረስ ያላችሁ የተመረጣችሁ መሆኑንና ከ16-20 ድረስ ያላችሁ ደግሞ ተጠባባቂዎች ሆናችሀኋል ፡፡ ከ5 ዓመት በላይ በስራ ልምድ የተወዳደራችሁ በቁጥር ከ1-10 ያላችሁ የተመረጣችሁ ሲሆን ከ11 -15 ድረስ የተዘረዘራችሁት ደግሞ ተጠባባቂ መሆናችሁን እንገልፃለን ፡፡
ለሁሉም የተመረጣችሁ ተቀጣሪዎች ከ15 /4/2017ዓ/ም ጀምሮ ፍትህ ቢሮ 5ኛ ፎቅ በአቃብያነ ህግ አስተዳደር ጉባኤ ፅ/ቤት ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን ፡፡

https://t.me/ethio_Legal_Case


የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅ-1.pdf
742.3Kb
የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅ ኢንግሊዘኛ-1.pdf
519.7Kb
የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅ ማብራሪያ -1.pdf
680.3Kb
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ4ተኛ ዓመት የስራ ዘመን በ11ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅን ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

በዚህም ረቂቁ አዋጅ ቁጥር 1360 /2017 በመሆን በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡



13 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.