Postlar filtri




የኦሮሞ ፖለቲከኛ ጃዋር መሐመድ በቅርቡ አሳትሞ ያሰራጨውን "አልጸጸትም" የተሰኘ መጽሐፉን PDF ሙሉውን በነጻ አሰራጭቶታል። የማንበብ ፍላጎቱ ላላችሁ ሼር አድርገነዋል። መልካም ንባብ።


#ኢትዮጵያ #ሶማሊያ

ኢትዩጲያ እና ሶማሊያ በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ መምከራቸውን አሳወቁ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ሞሃመድ ኦማር ጋር ስለመወያየታቸው ተሰምቷል፡፡

የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ማጠናከር እና የአንካራውን ስምምነት መተግበር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል ተብሏል፡፡

በአፍሪካ ቀንድ ሰላምን ለማስፈን እና ብልፅግናን ለማረጋገጥ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ማጠናከር ይገባልም ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጻል፡፡


ጀግናው አትሌት ስለሺ ስህን


መረጃ‼️

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌት ስለሺ ስህንን አዲስ ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾመ !

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ትላንት እና ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል አካሄዷል።

በጉባኤው ከሚጠበቁ ሁነቶች መካከል አንዱ የሆነው ቀጣዩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ምርጫ በዛሬው ዕለት ሲካሄድ ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን በአብላጫ ድምፅ አሸንፏል።

ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን በምርጫው 1️⃣1️⃣ ድምፆችን በማግኘት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በመሆን ማሸነፉ ታውቋል።

ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን በመተካት በሚቀጥሉት አራት አመታት ፌዴሬሽኑን በፕሬዝዳንትነት የሚመራ ይሆናል።


EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) dan repost
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ምርጫ እየተከናወነ ነው
*************

በ28ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ለቀጣይ አራት አመት ፌዴሬሽኑን በፕሬዝዳንት ለመምራት ምርጫ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ለፕሬዝደንትነት 6 እጩዎች የቀረቡ ሲሆን፤ ፕሮፋይላቸውም ለጉባኤው ቀርቧል፡፡

አስመራጭ ኮሚቴው ማብራሪያ እየሰጠ ነው፡፡

1.ገ/እግዚአብሄር ገ/ማርያም... ከትግራይ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

2.አቶ ያዬህ አዲስ.. ከአማራ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

3.ስለሺ ስህን... ከኦሮሚያ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

4.ሪሳል ኦፒዮ... ከጋምቤላ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

5.አቶ ዱቤ ጅሎ... ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንዲሁም፤

6. ኮ/ር ግርማ ዳባ... ከደቡብ ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ለመሆን እየተወዳደሩ ይገኛል፡፡

በምርጫው ሂደት 27 ድምጽ ሰጪዎች አሉ፡፡

በሃብታሙ ካሴ




በርካታ ኤርትራዊያን በህገወጥ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በህገወጥ ስራዎች ላይ ተሰማርተዋል !
--------

ከኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መግለጫ የተሰጠ መግለጫ 👇👇

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በኢትዮጵያ የሕግ ጥሰት የፈፀሙ የውጭ ዜጎችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥቷል የማብራሪያው ሙሉ ቃል ቀጥሎ ቀርቧል፡-

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ደህንነቱንና ጥራቱን የጠበቀ ዘመናዊ፣ ተደራሽ የውጭ ዜጎች አገልግሎት በመዘርጋት የሀገራችን የውጭ ኢንቨስትመንትና የቱሪዝም ፍስት በመጨመር የተጀመሩትን የልማትና የለውጥ ጉዞ በማፋጠን የሀገራችን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ እየተደረገ ባለው ሀገራዊ እንቅስቃሴ የበኩሉን ሚና ለመወጣት የሚያስችለውን የሪፎርምና ቀጣይነት ያለው ተቋማዊ ግንባታ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ ያሏት ተፈጥራዊና ታሪካዊ የቱሪዝም እምቅ ሀብቶች እና ኢንቨስትመንት ተጠቃሚ ለማድረግና የቱሪዝም መዳረሻ ማዕከል ለማድረግ በሀገር ደረጃ በሚደረግ ጥረት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የቱሪስት ቪዛ፣ ኮንፈረን ቪዛ ከዚህ በፊት ከነበረው የቪዛ ክፍያ ተመን ከ23 በመቶ በላይ እንዲቀንስ መደረጉን ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የክፍያ አገልግሎት ደንብ ቁጥር 550/2016 መገንዘብ ይቻላል።

መንግስት ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለው መልካም ጉርብትናና ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ካለው ቁርጠኛ አቋም በድንበር አካባቢ ከሚደረጉ ነጻ የሰዎች እንቅስቃሴ መፍቀድ በተጨማሪ መግቢያ ቪዛ ሳይጠየቁ በቀን ማህተም (ያለ ቪዛ ከፍያ) ገብተው ለ90 ቀናት እንዲቆዩ መፍቀዱ ይታወቃል።

በተለይ ከኤርትራ (አስመራ ወደ አዲስ ኣበባ ኢትዮጵያ) የሚመጡ ኤርትራዊያን ለ9ዐ ቀናት ያለ ቪዛ ክፍያ በቀን ማህተም ገብተው እንዲቆዩ ማድረጉ በሁለቱም ህዝቦች ያለው ግንኙነትና ወንድማማችነት ለማጠናከር ምን ያህል ቁርጠኛ አቋም እንዳለው ለመገንዘብ ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኤርትራዊያን ስደተኞች በጥገኝነት እንደሚኖሩ ይታወቃል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አንዳንድ ሚዲያዎች በተሳሳተ፣ ሚዛኑን ባልጠበቀ እና ኃላፊነት በጎደለው አግባብ ተቋማችን ኤርትራዊ ዜግነት ያላቸውን ሰዎች የተለየ በደል እና አድልዎ እየፈጸመባቸው እንደሆነ፣ ለመውጪያ ቪዛ የተጋነነ ክፍያ እንደሚጠየቁ፣ በስደተኝነት የተመዘገቡ ኤርትራዊያን ዲፖርት እየተደረጉ እንደሆነ አድርገው ሲዘግቡ ተስተውሏል።

በርካታ የውጭ ሀገር ሰዎች በህገወጥ መንገድ ድንበር ጥሰው ወደ ኢትዮጵያ በመግባትና ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ ሀገር ውስጥ ሲቆዩ የሚስተዋሉ ሲሆን፣ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የውጭ ሀገር ሰዎች የስራ ፈቃድና መኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸው ባልተፈቀደላቸው የሥራ መስክ ከመሰማራት ጀምሮ በህገወጥ የማዕድን ዝውውር፣ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ በአደገኛ እፅ ዝውውር፣ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ በኮንትሮባንድ፣ በሀሰተኛ ሰንዶች ዝግጅት ወዘተ የመሳሰሉ የሀገራችን ብሔራዊ ጥቅምና ደህንነት የሚጎዱ ተግባራት ላይ በመሰማራት ከባድ እና የተደራጁ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ሲፈፅሙ መገኘታቸውን ማርጋገጥ ችለናል።

በተለይ በርካታ ኤርትራዊያን በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር በመግባትና በህጋዊ መንገድ ገብተው ከተፈቀደላቸው የጊዜ ገደብ በላይ በመቆየት በህገ-ወጥ መንገድ እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ይታወቃል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እነዚህን አካላት ወደ ህጋዊ መንገድ ለማስገባትና ለመመዝገብ በተደጋጋሚ ጥሪ ማድርጉ የሚታወቅ ቢሆንም ተመዝግበው ወደ ህጋዊ ስርዓቱ የገቡ ግን በጣም ጥቂት ናቸው።

ስለሆነም የሀገርን ብሄራዊ ደህንነትና ጥቅም በሚጎዳ መልኩ ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የውጭ ሀገር ዜጎች በተመለከተ የሚከተሉትን ነጥቦች ማጉላት አስፈላጊ ነው።

ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድና የስራ ፈቃድ ሳይኖራቸው ሐሰተኛ ወይም የተጭበረበረ ማንነት በመያዝ ለውጭ ሀገር ዜጎች ባልተፈቀዱ የስራ መስኮች በመሰማራት በህገወጥ መንገድ ከትንሸ ሱቅ ችርቻሮ እስከ ያልተፈቀዱ ትላልቅ ስራዎች ተሰማርተው ተገኝተዋል።

በርካታ የኤርትራዊ ዜግነት ያላቸው ዘመድ ለመጠየቅ በማስመስል ከዱባይ፣ ከኤርትራ፣ ከኡጋንዳ በመመላለስ የተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጦች በሻንጣ በማስገባትና በማስወጣት የኮንትሮባንድ እና ሌሎች ህገወጥ ተግባራት ሲያከናውኑ ተገኝቷል።

በተለያዩ ሀገራት ከሚገኙ ሌሎች ህገ-ወጥ ደላሎች ጋር በመተሳሰር በርካታ ፍልሰተኞችን በህገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩና በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሲያከናውኑ ተገኝቷል።

ለተለያዩ ሕገወጥ ተግባራት የሚያገለገሉ ሐሰተኛና የተጭበረበሩ የጉዞና የይለፍ ሰነዶች፣ ማህተሞች፣ የባንክ ቡኮች በማዘጋጀትና በመጠቀም ህገ-ወጥ ተግባራት ሲፈጽሙ ተገኝተዋል።

የተለያዩ ሐሰተኛ ሰነድና ማንነት በመጠቀም ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ሲያከናውኑ እና ከህግ ውጭ ሰነዶችን ሲጠቀሙ መገኘታቸው።

ስለዚህ ማንኛውም የውጭ ሀገር ዜጋ የሀገራችንን ህግ ተላልፎ ከተገኘ በህግ ተጠያቂ እንደሚሆን ይታወቃል።

በመሆኑም ህጉ ተፈጻሚ የሚሆነው በሁሉም የሚመለከታቸው የውጭ ሀገር ሰዎች እንጂ በአንድ ሀገር ዜጋ ብቻ ተፈጻሚ የሚደርግ አሰራር ተደርጎ በአንድ አንድ ሚድያዎች መዘገቡ ስህተት ነው። ስለሆነም ለኤርትራዊያን ዜጎች እንደማንኛውም የጎረቤት ሀገር ዜጎች በቀን ማህተም ገብቶ በተፈቀደለት የጊዜ ገደብ (90) ቀናት ቆይቶ ለሚሔድ ሰው ምንም ዓይነት የቪዛ ክፍያ እንደማይጠየቅ ለመግለጽ እንወዳለን።

ከተፈቀደለት የጊዜ ገደብ ቆይተው የሚጣልባቸው ቅጣት ቢሆንም የኤርትራ ዜግነት ያላቸው ሰዎችን ጨምሮ ለጎረቤት ሀገራት እንዲከፍሉት የሚጠየቀው ክፍያ በእጅጉ (በ200 በመቶ) የቀነሰ ሆኖ እያለ ለኤርትራዊያን የተለየና የተጋነነ ክፍያ እንደሚጠየቁ ተደርጎ መዘገቡ ከእውነታ የራቀ ነው።

በተመሳሳይ መልኩ ኤርትራውያን ስደተኞችን በተመለከተም ኢትዮጵያ ስደተኞችን ተቀብላ ጥላ ከለላ መሆን የቆየ ታሪኳና ባህሏ እንደሆነና የኤርትራ ዜግነት ያላቸው ስደተኞችን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት ዜጎች በጥገኝነት እንድሚገኙ ይታወቃል።

በመሆኑም በስደተኝነት የተመዘገበ ማንኛውም የኤርትራዊ ዜግነት ያለው ሰው ያለ ፈቃዱ ከሀገር እንዲወጣ እና ተገቢነት የሌለው ክፍያ እንዲከፍል የተረገ ሰው የሌለ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

እውነታው ይህን ሆኖ እያለ በኤርትራዊያን ስደተኞች ላይ ያለ አግባብ ክፍያና ዲፖርቴሸን እንደሚፈጸምባቸው ተደርጎ መዘገቡ ከእውነት የራቀ ነው።

የሀገራችንን ብሔራዊ ደህንነትና ጥቅም በመጠበቅ ህጋዊ የውጭ ሀገር ሰዎች እንቅስቃሴን ለማረጋገጥ ለሚሰራው ስራ ላይ ሁሉም የሚመለከታቸው ባለድርሻና ተባባሪ አካላት ከጎናችን እንዲቆሙ ጥሪያችን እያቀረብን በተለይ ሚደያዎች ሚዛናዊ በመሆን የሀገራችንን ብሔራዊ ደህንነትና ጥቅም በጠበቀ መልኩ አወንታዊ ሚና እንዲወጡ እናሳስባለን።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት


ጥቆማ ❗️❗️
እንደወረደ 👇👇👇

አዲስ ነገር መረጃዎች ሠላም ከናንተጋ ይሁን
ኧረ ጅጅጋ 02ቀበሌ ነጋዴዎች በጣም እየተበደልን ነው የቀበሌ አመራሮች አማርኛ ተናጋሪ የሆነ እየመረጡ ቀበሌ እያሠሩ 2000እስከ5000 እያስከፈሉን ነው ክፍያውሰ ደረሠኝ የለውም በአካውንት አደለም የሚገባው በራሳቸው ስልክ ቁጥር ኢ-ብር ነው ሚገባው እና በየ ወሩ አንዴ ግዴታ አረጉት ምክንያት የለውም የነጋዴው ብዛት ከ150በላይ ነው በየመንገዱ ሚዛን ሚሠሩ ህፃናት እንኳን አይምሩም 500እያስከፈሏቸው ነው አማራ የተባለ ብቻ ላይ ነው ይሄን የሚያረጉት ነጋዴው ሠርቶ ለነሱ ነው ሠዉ ለማን እደሚናገር ግራb ገብቶናል እነዚ ሠዎች እንደዚህ  ያረጉት አንዴ አደለም ተደጋጋሚ በየወሩ ነው እነዚ ሠዎች በጣም የተደራጁ ናቸው ገቢያቸው 200ሺ በላይ ነው በየወሩ በምን መጡ ተብሎ ጭንቅ ነው አዘኔታ የላቸው ሴት ጭምር በጥፊ ነው የሚመቱት አማራ ከሆነች ምክንያት መጠየቅ አይቻልም ሀይ ሚላቸው ጠፋ በጣም ተማረናል
እባካችሁ የሚመለከተው አካል መፍትሄ ይስጠው 🙏🙏

#አዲስ_ነገር_መረጃ


የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ከዓለም አቀፍ ሕግ አንጻር …

አዲስ አበባ፣ ታሕሳሥ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ የኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት መነቃቃት ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ የራሷ ወደብ እንደሌላት ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ መሪዎች አንዳቸው የሌላኛቸውን ሉዓላዊነት፣ ነጻነት እና የግዛት አንድነት እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታት እና በአፍሪካ ሕብረት ደንቦች ላይ የሰፈሩ ዓለም አቀፍ ሕጎችን ለማክበር ተስማምተዋል።

ይህን የአንካራ ስምምነት ተከትሎ የሕግ ባለሙያው አንዷለም በእውቀቱ÷ ኢትዮጵያ ሰሞኑን ከሶማሊያ ጋር የተፈራረመችው ስምምነት የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ ከዓለም አቀፍ ሕግ አንጻር ወሳኝ ጠቀሜታ እንዳለው አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር በአፍሪካ የባሕር በር ከሌላቸው ሀገራት ሕዝብ 33 በመቶውን እንደሚሸፍን በተባበሩት መንግሥታት…

https://www.fanabc.com/archives/275233




በቱርክ ሲደረግ የነበረው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ድርድር በስምምነት ተጠናቀቀ 
** 

በቱርክ
ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን አደራዳሪነት በአንካራ ለሶስተኛ ጊዜ የተካሄደው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ድርድር ሁለቱንም አገራት በሚያግባባ ስምምነት ተጠናቅቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በቱርክ ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶጋን ግብዣ ዛሬ ምሽት በአንካራ ውይይት አድርገዋል፡፡

ሁለቱ መሪዎች ውይይቱን ካደረጉ በኋላም በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል። 

መሪዎቹ በመግለጫቸውም፤ ኢትዮጵያ በሶማሊያ የባሕር ዳርቻ በኩል ዘላቂ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ የወደብ አማራጭ በምታገኝበት አማራጭ ላይ የቴክኒክ ውይይቶችን ለመጀመር መስማማታቸውን ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመግለጫቸው፤ ቱርክ በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እንዲሰፍን ለምታደርገው ከፍተኛ አስታዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡  

የኢትዮጵያ የሶማሊያ ህዝቦች በቋንቋ፣ በባህል እና በደም የተሳሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለጋራ ሰላምና ልማት ከሶማሊያ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗንም ተናግረዋል፡፡
 
ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በበኩላቸው፤ የሶማሊያ መንግስት የኢትዮጵያ ወታደሮች ለሶማሊያ ሰላም የከፈሉትን መስዋዕትነት አይዘነጋም ሲሉ ገልፀዋል፡፡ 

ሁለቱ ሀገራት በቀጣይም ሰላምን ለማፅናት በሚያደረጉት ጥረት መንግስታቸው ቁርጠኛ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን በበኩላቸው፤ ሁለቱ ሃገራት የፈረሙት ሰነድ ትብብርን፣ የኢኮኖሚ እድገትን እና ብልጽግናን የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልፀዋል፡፡






በ170 ሚሊየን አሜሪካውያን ዘንድ ጥቅም ላይ የዋለው መተግበርያ ለአሜሪካ ኩባንያዎች ከመሸጥ ይልቅ መታገድ መምረጡን ተከትሎ በሚቀጥሉት 6 ሳምንታት ውስጥ በአሜሪካ መስራት ሊያቆም ይችላል ተብሏል፡፡

ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዓለ ሲመታቸው ከመከናወኑ አንድ ቀን በፊት ውሳኔውን ካላሳወቀ የእግድ አደጋ የተጋረጠበት ሲሆን በመጪዎቹ ቀናት ይግባኙን ለጠቅላይ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ አስታውቋል፡፡ 

በባይደን አስተዳደር ለቻይና መንግስት የአሜሪካውያን ግላዊ መረጃዎች አሳልፎ ይሰጣል በሚል ክስ የቀረበበት ቲክቶክ ምንም እንኳን ከቤጂንግ መንግስት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው እና የቀረበበት ክስም ሀሰተኛ መሆኑን በፍርድ ቤት ቢከራከርም ውሳኔውን ማስቀየር አልቻለም፡፡

ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሜሪክ ጋርላንድ ውሳኔው “የቻይና መንግስት ቲክቶክን በመሳርያነት እንዳይጠቀም ለማድረግ አስፈላጊ እርምጃ ነው” ሲሉ ጠርተውታል።

"አይን ያወጣ የንግድ ዘረፋ ነው" ሲል ውሳኔውን የተቃወመው በዋሽንግተን የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ በበኩሉ ፤በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የጋራ መተማመን እና የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዳይጎዳ አሜሪካ ይህን ጉዳይ በጥንቃቄ መያዝ አለባት ሲል አስጠንቅቋል።

የቲክ ቶክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሾው ዚ ቼው ለሮይተርስ በላኩት ኢሜል “የዛሬው ዜና ተስፋ አስቆራጭ ቢሆንም የመናገር ነፃነትን ለመጠበቅ ትግሉን እንደምንቀጥል ለማረጋገጥ እንወዳለን” ብለዋል በነጻነት የመናገር መብት አንቂዎች እና የሲቭል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ይህን ውሳኔ ከተቃወሙት መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

 “ቲክቶክን ማገድ ይህንን መተግበሪያ ሃሳባቸውን ለመግለጽ እና በአለም ዙሪያ ካሉ ሰዎች ጋር ለመግባባት የሚጠቀሙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አሜሪካውያን መብቶችን በግልፅ ይጥሳል” በሚል ተቃውመዋል፡፡

በቻይና ጉዳይ ከባይደን አስተዳደር በበለጠ ጠንካራ አቋም ያላቸው ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት የሚያሸንፉ ከሆነ ቲክቶክን ከመሸጥ እና ከመታገድ እንደሚታደጉት ተናግረው ነበር፡፡


የባይደን አስተዳደር ቲክቶክ ለአሜሪካ ኩባንያ እንዲሸጥ አልያም በሀገሪቱ አገልግሎት ከመስጠት እንዲታገድ የሚጠይቅ ህግ አውጥቷል

የአሜሪካ የፌደራል ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በቻይና የተመሰረተው ባይትዳንስ ኩባንያ ስር የሚገኘውን የአጫጭር ቪዲዮ ማጋርያ መተግበሪያ በሚቀጥለው ዓመት መጀመሪያ ላይ እንዲሸጥ ወይም እገዳ እንዲጣልበት የሚያስገድደውን ውሳኔ አፅድቋል።

የፍርድ ውሳኔው ለፍትህ ሚኒስቴር እና በቻይና ባለቤትነት ለተያዘው መተግበሪያ ተቃዋሚዎች ትልቅ ድል ሲሆን ለቲክቶክ ደግሞ ከፍተኛ ኪሳራን ሊያስከትል እንደሚችል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

የአሜሪካ ተወካዮች ምክርቤት ቲክቶክን በመላው ሀገሪቱ ሊያግድ የሚችል አዋጅ አጸደቀ የፍትህ ሚኒስቴሩ ሀላፊዎች “ውሳኔው ቻይና በአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነቶች ላይ የደቀነቻቸውን ስጋቶች ለመዋጋት ዴሞክራት እና ሪፐብሊካች ተመሳሳይ አቋም እንዳላቸው አመላካች ነው” ብለዋል፡፡


Addis Admass dan repost
አንጋፋዋ ሙዚቀኛ አስቴር አወቀ ከሜትሮፖሊታን
ሪል እስቴት ጋር ለመሥራት ተፈራረመች



የሶል ንግስቷ አርቲስት አስቴር አወቀ፣ ከሜትሮፖሊታን ሪል እስቴት ጋር በጋራ ለመሥራት የተስማማች ሲሆን፤ ስምምነቱ አምባሳደርነትን አያካትትም ተብሏል፡፡፡


ሜትሮፖሊታን ሪል ስቴት፣ ከአንጋፋዋ አቀንቃኝ ጋር የተፈራረመው ስምምነት በሙዚቃው ኢንዱስትሪ ወደፊት የምታወጣቸውን ሥራዎች እንዲሁም በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የምትሰራቸውን ሙዚቃዎች ማስተዋወቅን ያካትታል፡፡

የአርቲስቷ ማናጀር ወይዘሪት አዳነች ወርቁ እንደገለጹት፤ ድምፃዊጻዊት አስቴር አወቀ ከዛሬ ህዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከሜትሮፖሊታን ሪል እስቴት ጋር ሥራዋን ጀምራለች፡፡







20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.