🔈ገራሚ ሃሳበ፤ የቅዳሜ የንባብ እፍታ
ሰውዬው ስራ አጥ ነው
ከአንድ ድርጅት ዘንድ ሄዶ "ተላላኪም ቢሆን ቅጠሩኝ" ብሎ ይማፀናል
የድርጅቱ ቀጣሪ "ኢሜይልህን ስጠኝ እና ፎርም እልክልሃለሁ: እሱን ሞልተህ ይዘህ ትመጣለህ" ይለዋል
"ጌታዬ! እኔ ዘመናዊ ስልክ እና ኮምፒውተር የለኝም :ኢሜይልም አልጠቀምም:: ስራው ግን በጣም ያስፈልገኛል" ብሎ ይማፀናል
"ኢሜይል እንኳ ሳይኖርህ ነው እንዴ ስራ የምትጠይቀው!" ብሎ በግልምጫ ያሰናብተዋል
▶️ሰውዬው ወደ መንደሩ ተመለሰ
ስራ የማግኘት ተስፋው ሲደበዝዝ እጁ ላይ በሚገኘው ብር እንቁላል ቀቅሎ አካባቢው ለሚገኙ ተማሪዎች ማቅረብ ጀመረ: ትንሽ ቆይቶ ትርፉን በማጠራቀም ሌሎች ምግቦችን ጨመረ
እንዲህ እንዲህ እያለ ለትላልቅ ተቋማት እና ዩኒቨርስቲዎች ምግብ የሚያቀርብ ስኬታማ ሰው ሆነ
***
▶️ከአመታት በኃላ ላፈራው ንብረት ኢንሹራንስ ለመግባት ወደ አንድ ድርጅት ጎራ ብሎ ጉዳዩን አስረዳ
"የሚሞላ ፎርም ስላለ ኢሜይልህን ስጠኝ!" አለችው አስተናባሪዋ
"ኢሜይል የለኝም እመቤቴ"
"ኢሜይል ሳይኖርህ እንዲህ ስኬታማ የምግብ ኢንዱስትሪ ከገነባህ ኢሜይል ቢኖርህ ደግሞ ምን ልትሆን ትችል እንደነበር ታውቀዋለህ?"
ሰውዬው መለሰ
👇🏾
⬇️"አዎ አውቀዋለሁ: ተላላኪ ነበር የምሆነው"
ሰዎች በሚለጥፉባችሁ ስያሜ እና ስለ እናንተ ባላቸው አመለካከት አትገደቡ !!
🫴የቀኑ ጠቃሚ መልእክቶችን፣ መጽሐፍት በፒዲኤፍ መልክ፣ በነፃ አሪፍ የኮምፒውተር ሶፍትዌሮች፣ የቢዝነስ ሃሳቦች እና የገንዘብና የተለያዩ ሽልማቶችን ለማግኘት ገጾቻችንን ይቀላቀሉ። ☄️ Super Boost-up 📈
Digital marketing and consultancy
☎️0908 222223 / 0914 949494
📱ቴሌግራም👉
https://t.me/Superboostupp📱ፌስቡክ ገጽ👉
https://www.facebook.com/SuperBoostUp🌐ዌብሳይት 👉
https://superboostup.com/📱ቲክቶክ👉
@superboostup' rel='nofollow'>tiktok.com/
@superboostup