Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Siyosat


I didn't bit the land that feeds you!

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Siyosat
Statistika
Postlar filtri




ቢንጎ🤣

ለ Getnet Almaw Tiruneh ይህ የክብር ጥሪ በአማራ ክልል ከሚገኝ በመንግሥት ቁጥጥር ስር ከሚገኝ አካባቢ ስለደረሰው እስካሁን መደነቄን ላቆም አልቻልኩም። በክልሉ ደረጃ ራሱ በግለሰብ ካልሆነ በቡድን ከመከሩበት በፍጹም የሚጠበቅ አይደለም።እንዲሁም በዞን ደረጃም ቢሆን እንደ መዋቅር ሳይሆን እንደ ግለሰብ መደመር ገብቷቸውና ፈልገው ብአዴንን ከላያቸው ላይ በማራገፍ ለለውጥ የሚሰሩና ብልጽግና የሆኑ ግለሰቦች ጎልተው የማይባቸው ሁለት ዞኖች አሉ እንጅ ሌላው ለእንጀራ ለጥቅማጥቅም ለሌሎች ብሎ የሚሰራና የሚኖር ነው። በአጭሩ አብዛኛው የክልሉ አካባቢና የመዋቅር ሰንሰለት ለእንደ ጌትነት ላለ በመደመር መንገድ ለሚራመድና የወያኔ መሩ የሳልሳዊ ብአዴንን መንገድ ለሚቃወም የነቃና የበቃ ኤሊት የክብር ጥሪ አይደለም በሕይወት የመኖር መብት የሚፈቅድ አይደለም። ጫካ ገባን ካለው ፋኖ ተብዬ በላይ እንደዋና ጠላት ቆጥሮ የሚያሳደው ቆሞ ቀሩ መዋቅር የያዘው አመራርም ነው። ጫካ ያለው ፋኖ ለእነሱ የግል ጥቅም የተቋቋመና በእነሱ የሚመራም ነው። አማራ ክልል በነበረውና ባለው ሁኔታ በተለይም የዶ/ር ዐብይ ደጋፊ እና የመደመር መንገደኛ የሆነ አንድ የሆነ ሰው ተጠቃ ከተባለ የሚጠቃው በፋኖ ፍላጎትና ብቃት ሳይሆን መዋቅር ውስጥ ባሉ ብልጽግናን ብአዴን በሚሉ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ መቃብር ጠባቂ አመራሮች መሪነት ወይም ጠቋሚነት ነው።

ከእነሱ ቁጥጥር ውጭ የሆነ አንድም ፋኖ በየትኛውም አካባቢም የለም። ሁሉም ብልጽግና ውስጥ ብአዴንነቱን ያላወለቀ የጡት አባት አመራር አለው።

እና አስባችሁታል በዚህ መካከል ኢትዮጵያን ያስቀደመ የመደመር መንገድ አቀንቃኝ የዶ/ር ዐብይ ደጋፊ የሆነ ሰው ለክብር ለሽልማት ሲታጭ።እነዚህ በማንነታቸው አገው ጭምር ባይሆኑ ኖሮ እንደ አካባቢው መንግሥት በቡድን መክረው የክብር ጥሪም አያደርጉም ነበር። ይህን የምለው እንዲሁ አይደለም። ማን ምን እንደሚያወራ እንኳን ለእኛ ለአልፎ ሂያጁ ሁሉም ግልጽ የሆነ ጉዳይ በመሆኑና ነገሩ እንደዛ አይደለም ከተባለ ሰው ሟች አይደለም የሚያስብልም ስለሆነ ነው።

በአማራ ክልል ብልጽግና በብአዴን ላይ ገና ፖለቲካዊ ድል አልተቀዳጀም። በዚህ አያያዙም በቅርቡ ድል የሚቀዳጅ አይመስለኝም። የመደመር አቀንቃኙ ብልጽግና መዋቅሩን በተቆጣጠረውና ብልጽግናን ብአዴን በሚለው ብአዴናዊ እየተሳደደ እየተጠቃ ያለውንም እያጣ የሚቀጥል ይሆናል። ቢመረንም መሬት ላይ ያለው ሐቅ ከዚህ የተለዬ አይደለም። አስፈላጊ ከሆነ በዚህ ዙሪያ ሰፋ ያለ ነገር እያንዳንዱንም ነገር እየዘረዘሩ መጨመር ይቻላል።

የሆነው ሆኖ፣ ወንድም ጌች በአማራ ክልል በሚገኝ መዋቅር የክብር ጥሪ ስለመጣልህ እንኳን ደስ ያለህ። የምር ቢንጎ🤣




በሸዋ ቀጠና የሚገኙ አለሙ ይልማ እና ይገረመው የተባሉ የቡድኑ አመራሮች ቡድኑ ያገጠመውን የፍይናንስ እጥረት ለመቅረፍ በነዋሪዎች ላይ ግዳጅ ጥለው በማሰባሰብ ላይ እንደሚገኝ ሲገልፁ የሚያሳይ ንግግር


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
በጋሻውን አይቼው አላውቅም ነበር የት ጠፍቶ ነው?

በዚህ ደሞ ጥሩ መልዕክት አስተላልፏልና አድምጡት።


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ፌክ ኒውስ አጣራለሁ ፋክት ቸክር በሚል ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጨው ኤሊያስ መሰረት የተባለ የወያኔ አጀንዳ አራጋቢ ከረፈደም ቢሆን በጃውሳ መንደር የተነቃበት ይመስላል።ፌክ ኒውስ ብሎ በፋክት ቸክር የሚያጋራው ከእሱ ቡድን አንደኛው ሆንብሎ ያሰራጨውን ሀሰተኛ መረጃ ወይም በራሱ ፌክ አካውንት በኩል እንዲሰራጭ የተደረገን ሀሰተኛ መረጃን ወይም የTplf አስተሳሰብ ተቃዋሚ ኢትዮጵያኒስት የሆኑ ሰዎችን ነጥብ ያስጥላል ብሎ የሚያስባቸውን አካላት በማሳደድ ነው። በተደራጀና በተቀናጀ መንገድ ስለሆነ ይሰሩ የነበረው ትንሽ ነገር ይገባዋል ጥያቄ ያነሳል ተብሎ የሚታሰበው ሰው ሳይቀር እሱን ተአማኒነት ያለው የእውነት ሚዛን አድርጎ ሲቆጥረው ቆይቷል። የማይጠይቀውንና ሳያላምጥ እንደወረደ የሚውጠውን መንጋ ደግሞ እንደፈለገ ሲነዳውና ሲዝናናበት ከርሟል። አሁን አሁን ግን ያ መንዘባነን እየራቀው ብዙሃኑ እየነቃበት የመጣም ይመስላል።

የሆነው ሆኖ፣ ጃውሳ በጃውሳ ላይ የሚያደርገው ሁለንተናዊ የጦርነት ዘመቻ ተፏፉሞ ቀጥሏል።በማን አሸናፊነት ይጠናቀቃል የሚለውን አብረን የምናየው ይሆናል።


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ደረጃ ለመውጣትና ለመውረድ ለሚቸገሩ ወጣቶች ጭምር ስፖርት እንዲሰሩ መነሳሳቱን ቢፈጥርላቸው


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
የኢትዮጵያ በተለይም በተቃውሞ ፖለቲካ የሚሳተፉ ሰዎች ሐገርና ሕዝብ እንምራ ከማለታቸው በፊት ቅድሚያ ራሳቸውን ሊመሩ ይገባል። ዐብይ ሐገርና ሕዝብ የሚያስተዳድርበትን መንገድ ከሚተቹት መካከል አብዛኞቹ ራሳቸውን መምራት የማይችሉ ናቸው። አንዳንዶቹ ጭራሽ ዶ/ር ዐብይን ወልደው ማድረስ የሚችሉ ሰዎች ቢሆኑም ዛሬም ቤተሰብ መስርቶ ለመምራት ተቸግረው የሚታዩ ነገር ግን ለትችት ከማንም በላይ የሚሽቀዳደሙ ሆነው የሚታዩ ናቸው። እነዚህ ሰዎች ቤተሰብ መመስረት ያልቻሉት በዋናነት ግለኝነት የሚያጠቃቸው ኋላፊነት መውሰድ የማይችሉ ራስ ወዳድ ስለሆኑም ነው።

እናም ሐገርና ሕዝብን ለመምራት ከማሰብ በፊት ትንሿን ተቋም ቤተሰብን መምራት ግድ ይላል።


ይሄው የአባ ጅፋር ቤተ-መንግሥትም ታሪካዊነቱን ቅርስነቱን ጠብቆ እንዲታደስ ስላልተፈለገ ሆን-ተብሎ እንዲቀላ ተደርጓል።ቀድሞ የነበረው ቀለም እንዲህ አልነበረም።መሰል አስተያየቶችን ሁሉም የተሰራን ለማፍረስ ከሚጥሩና ሥራን ከሚያጣጥሉ፥ ለሐገር ቀርቶ ለራሳቸው አንድ ቁምነገር ያለው ሥራ ሰርተው ከማያውቁ፣ አይደለም ለቅርሱ ለሐገሩ ግድ ብሏቸው ከማያውቁ፣ ከሥራ ጠል የአሉባልታ ተንታኞች፣ የዋልጌዎች ማህበር እንጠብቃለን😎


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ጅማ ልጇን በፍቅር ለመቀበል እንዲህ ነው በነቂስ የወጣችው።


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ጧት በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ዳውሮ ዞን የተገኘው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በዛ የነበረውን መልካም ቆይታ አጠናቆ ከሰዓት ደግሞ ወደ ጅማ ከተማ ገብቷል።

እረፍት የለም። ለኢትዮጵያ ልዕልና ሲል ቀንና ሌት ነው የሚደክመው። ለነገ የሚለው ሥራ የሚቆጥበው ጉልበት እውቀትና ጊዜ የለም። በተቻለ አቅሞ ሁሉንም የሐገሪቱን አካባቢዎች ያላቸውን ፀጋ እየለዩ እንዲጠቀሙና እንዲቀየሩ እየተጋ ነው።
እንደ ዶ/ር ዐብይ አህመድ በ6 ዓመት ውስጥ ይቅርና በ20 30 40 የአገዛዝ ጊዜ የነበራቸው የቀደሙ የኢትዮጵያ መሪዎች ኢትዮጵያን በሥራ ለመቀየር አይደለም ሐገሪቱን በቅጡ ለማወቅ በየአካባቢው የወረዱ አይመስለኝም። ዐብቹ ይለያል!!

እያስዋባትና እያለማት የምትገኘው ጅማ ዐብቹን በፍቅር በስስት ለመቀበል የማንንም ጥሪ አልፈለገችም!!


የኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ታርጫ ከተማ የገቡ ሲሆን በእንግዳ ተቀባይነት የሚታወቀው የዳውሮ ህዝብም በነቂስ በመውጣት ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል። በቆይታቸውም ጠቅላይ ኢት-ማይኒንግ ከሰል ድንጋይ ፋብርካ ይመርቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።


ሕወሓት አላስፈላጊ ዋጋ ኢትዮጵያዊያንን ሊያስከፍል ይችላል። 1001% እርግጠኛ መሆን የምችለው ግን የቱንም ያህል በየሰፈሩ ነፃ አውጭ ነኝ ባይ ጃውሳዎችን እያደራጀ በፕሮፖጋንዳ በፋይናንስ በትጥቅ ቢያግዝና በእነሱ በኩል በብልጽግና ላይ ጊዜያዊ የበላይነት ሊይዝ የሚችልበት ሁኔታ እስከመፍጠር ይደርሳል ብዬ ለእነሱ ትርክት ብሸነፍ እንኳ ሕወሓት ስሙን ሳይቀር ሕወሓት ሆኖ በፍፁም አራት ኪሎ ሊገባ እንደማይችል ነው።በሆነ ግርግር የሚገባበት ዕድል ተፈጠረ ብንል እንኳ በፍፁን መንግሥት ሊሆን አለመቻሉ ነው። የአራት ኪሎ መንግሥት ለመሆን በአራት አቅጣጫ ያለውን ሕዝብ መያዝ የግድ ይላልና።

የሆነው ሆኖ በዚህ ሦስት ሺ ዓመት የኢትዮጵያም ሆነ የዓለም የመንግሥትነት ታሪክ ታይቶና ተሰምቶ የማያውቅ ነገር በወያኔ አማካኝነት መሆኑ ሊያስደንቀን ይችል ይሆናል። አማጺ ሽፍታ መንግሥት ሆኖ ከዛ በሕዝዞ አመጽ ከመንግሥትነት ወርዶ ወደ አማጺ ሽፍታነት በመቀየር መልሶ መንግሥት ለመሆን የሞከረ ሃይል በሚል። ነገር ግን ይህን ሃይል ያለ የሌለ ሃይሉን በወቅቱ ቢሞክርም በኢትዮጵያዊያን እርብርብ ያሰበው ሳይሳካ ከሽፏል። ወደፊትም ቢሆን ወያኔ አሁን የሆነውን ሆኖ መንግሥትን አዳክሞና አስወግዶ አገር ለማስተዳደር መንግሥት ሊሆንበት የሚችል መንገድ የለም።
Tplf ግን አሁንም አገሪቱን የሚመራው አስተሳሰብና መዋቅር እንዲሁም ኤሊት የወያኔ ምልምልና ቅጥቅጥ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ይህ ሃይል Tplf በሚል ሥም ሲመጣ የራሱ የትግራይ ቤተሰብም ይቀበለዋል ተብሎ አይታሰብም። ጦርነት ዳግሞ ቢከፍት አሁንም ከሽንፈት አይደንም። ምክንያቱም እሱ የፈጠረው ትውልድና ኤሊት እስከ ጦርነቱ መለኮስ ድረስ ደገፈው ብንል እንኳ ሕወሓት ጦርነት ውስጥ ገባ የተባለ ቀን መላ ነገሩ ይቀይራልና። በሁለት ምክንያት። አንደኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ስቴት ካልቸር ያለው ስለሆነ መንግሥት ክተት ሲያውጅ ከመቅጽበት የሚሰባሰብና ለዘመቻ የማያስቸግር በመሆኑ ሲሆን ሁለተኛውና ዋናው ደግሞ በአዘቦት ቀን ብዙሃኑ የTplfን ሀሳብ የሚያራምድ ወይም በእሱ mindset የሚያስብ መስሎ ቢታይ እንኳ tplf ዳግሞ ቃታ ሳበ ጦርነት ተከፈተ ሲባል አራት ኪሎ ይቅርና በሚባለው ልክ ሕልውና ዘርቶ ማየት የማይፈልገው ቁጥር የትየለሌ መሆኑ የማያጠራጥር ነውና። ስለሆነም የ Tplf ስሌት ዳግም ምስኪን የትግራይ ልጆችን አላስፈላጊ ዋጋ ሊያስከፍል ካልሆነ የሚያሳካው ድል መቼም ቢሆን አይኖርምና ሲሆን በፌኩ የፌደራሊስት ሃይሎች በኩል ያሉት ጭምር ካልሆነ የመጀመሪያው ገፈት ቀማሽ ሊሆን የሚችለው የትግራይ ተወላጅ የTplfን የጥፋት መንገድ ለማስቆም መረባረብ አለበት። ያልነው ሁሉ ሆነም አልሆነም ግን የአማራ ክልል ከመቼውም ጊዜ በላይ ልዩ ዝግጅትና ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። አላስፈላጊ ዋጋ መክፈል የለበትምና።

ሰላም ለሕዝባችን!
ትልማ ኢትዮጵያችን!


ታጋይ ታደሰ ወረደ ታጋይ ምግበ ታጋይ ፃድቃን ብልጽግናን ለማስወገድ ወደ አንድ ስለመጡ በጣም ደስ ይላል አይነት ቀደዳ ነው በአማራ ፋኖ ነኝ ባይ ወንበዴ ሌቦች በኩልም እየሰማን ያለነው አስደናቂው ጉዳይ።አይገርምም የታጋዮቹ ማንነት ግን?! ተንቀናል ተናንቀናልም አለ መንጌ።


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
የከርሞ ሰው ይበለን!!

የጥምቀት በዓል ማጠቃለያ

"..ቢፋቅ የማይለቅ ክብርሽ ትልቅ ነው!"

ኢትዮጵያዊነት በጎንደር!!

ሰላም ለሕዝባችን!
ትልማ ኢትዮጵያችን!


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
"ምንድነው እኛ ያለን ፖቴንሻል?"የብልጽግና ሥራ አስፈፃሚ አባልና የኢንደስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በመገኘት ስለአመራር፣ስለፈጠራ እና ስለኢንደስትሪ እድገት ከሰጡት ስልጠና ላይ የተወሰደ


ሽባ ሆኖ የፈረሰን የክልሉን የፀጥታ መዋቅር መልሶ በማደራጀትና በማጠናክር በክልሉ አንፃራዊ ሰላም እንዲሰፍን የጥምቀት በዓል በታሪካዊቷ ጎንደርና በሌሎቹ የክልሉ አካባቢዎችም ባማረ መልኩ በድምቀት ተጀምሮ በድምቀት እንዲጠናቀቅ በብቃት ለመሩት ለጀግኖቹ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኋላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ለክልሉ ፖሊስ ኮምሽን ኮምሽነር ደስዬ ደጀን እና ለሁሉም የፀጥታ አባላት ትልቅ ምስጋና ይገባል።

የጠላት ሟርትና እንቅስቃሴ ከሽፎ የአንዳንዶች ስጋት ተቀርፎ ሕዝቡ በነቂስ ወደ አደባባይ በመውጣት በዓሉን በነፃነት በሰላም በደመቀ ሁኔታ አክብሮ በሰላም መግባቱ የክልሉ የፀጥታ ሃይል የደረሰበትን ደረጃም የሚያሳይ ነው። ለጀግኖቹ ምስጋና ይገባቸዋል!!


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
የብልጽግና ሥራ አስፈፃሚ አባልና የኢንደስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በመገኘት ስለአመራር፣ስለፈጠራ እና ስለኢንደስትሪ እድገት በጥቅሉ ስለ ኢትዮጵያ የወደፊት መጻዒ ዕድል ዙሪያ ጥልቅ ሀሳባቸውን ያጋሩበት

18 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.