በመዲናዋ የስድስተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ሰኔ 22 እና 23/2015 ዓ.ም ይሰጣል:-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን) ሚያዚያ 19/2015 ዓም
በመዲናዋ የስድስተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ሰኔ 22 እና 23 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገለጸ፡፡
በ2015 የትምህርት ዘመን ተግባራዊ በሆነው አዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት የስድስተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ፈተናውን ለመስጠት የሚያስችለውን ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልጿል፡፡
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ቢሮው ፈተናውን ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡
ተፈታኝ ተማሪዎችን በስነ-ልቦና ከማዘጋጀት ባሻገር በትምህርት ቤቶች ቅዳሜና ከመደበኛ ትምህርት ውጭ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም የተማሪዎችን ስነ-ልቦና ለማዘጋጀት የሚያግዝ የሞዴል ፈተና መሰጠቱን ጠቅሰው፤ በፈተናው አበረታች ውጤት ተገኝቷል ነው ያሉት፡፡
በቀጣይም ተጨማሪ የሞዴል ፈተና ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን ነው የተናገሩት፡፡
ይህን ተከትሎ ሰኔ 22 እና 23 ቀን 2015 ዓ.ም የስድስተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና እንደሚሰጥ ዶክተር ዘላለም የገለጹት።
የስድስተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ለመውሰድ 75ሺህ 102 ተማሪዎች የኦንላይን ምዝገባ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
በፈተና ወቅት ኩረጃ እንዳይኖር በቂ ዝግጅት መደረጉን ገልጸው በመጀመሪያ ዙር የሞዴል ፈተና ወቅት ኩረጃ እንዳይኖር የሚያስቸሉ ተግባራት መከናወናቸውን አስረድተዋል።
በተመሳሳይ የስምንተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ሰኔ 19 እና 20 ቀን 2015 ዓ.ም በከተማ ደረጃ የሚሰጥ ሲሆን፤ 78ሺህ 78 ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
@Timihirt_Minister