ድሬዳዋ እና ጅቡቲ ተከማችተው የሚገኙ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ተፈቀደ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ክልከላ ከተጣለ ወዲህ በጅቡቲ እና ድሬዳዋ ተከማችተው የሚገኙ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ መመርያ መተላለፉን ከአንድ የገንዘብ ሚኒስቴር ደብዳቤ ተመልክተናል።
ከየካቲት 26/2016 ዓ/ም በፊት ግዢ የተፈፀመባቸው ተሽከርካሪዎች ወደ ድሬዳዋ ተጓጉዘው የመንግስትን ውሳኔ ሲጠባበቁ ነበር።
ይህ ከትናንት በስቲያ፣ ሀሙስ እለት በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ የተፈረመ ደብዳቤ በድሬዳዋ እና ጅቡቲ የሚገኙት እነዚህ ተሽከርካሪዎች "ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ መረጃቸው ተይዞ ሀገር ውስጥ እንዲገቡና የጉምሩክ ስነስርዐት እንዲፈፀምባቸው በመንግስት ውሳኔ ተሰጥቷል" ብሏል።
ደብዳቤው አክሎም የጉምሩክ ዲክላራሲዮን ተቀባይነት በሚያገኝበት ቀን በሚኖረው የምንዛሬ ተመን መሰረት ቀረጥ እና ታክስ ተከፍሎባቸው እንዲገቡ መወሰኑን ይገልፃል።
contact us
Email :- tradeuptrading@gmail.com
Phone :- +251973028888
Tg :-
@export7For more 👇👇 click the link
https://t.me/+SjcIYocNGQSfeI3c