የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
ኅዳር 12/2017 (አዲስ ዋልታ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 40ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
1. በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው የመካከለኛ ዘመን (2017-2021) የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊስካል ማዕቀፍ ላይ ነው፡፡ ማዕቀፉ በሁለተኛው ምዕራፍ ሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ የሚከናወኑ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎችንና የመንግስት የፊስካል ፖሊሲ ማሻሻያዎችን ተግባራዊ ለማድረግ እና ለ2017 የፌዴራል መንግስት ተጨማሪ በጀትና የወጪ አሸፋፈን ማስተካከያ መነሻ ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ተቃኝቶና ተሻሽሎ የቀረበ ነው፡፡ ምክር ቤቱም በማዕቀፉ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው በፌዴራል መንግስት የተጨማሪ በጀት እና የወጪ አሸፋፈን ማስተካከያ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የተጨማሪ በጀት እና የወጪ አሸፋፈን ማስተካከያው የተሻሻለውን የ2017-2021 የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊስካል ማዕቀፍ ማስፈጸም በሚያስችል መልኩ የመንግስት የፋይናንስ አቅምና ተጠባቂ ገቢዎችን ታሳቢ በማድረግ፣ የተጨማሪ በጀት ታሳቢዎችንና የወጭ ታሳቢዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት ተዘጋጅቷል፡፡
👇👇
https://web.facebook.com/share/p/19aLseVgip/