ሰላም ጋይስ እንዴት ናችሁ፤ I hope ባለፈው በነበረን የቴክኒካል አናሊስስ ቆይታ ለማሳወቅ እንደሞከርኩት ገበያው በተለይ በአጭር ጊዜ እይታ የቢትኮይንን ጉዞ መሰረት ያደረገ እንደሚሆን በገመትነው መሰረት ከታሰበው በላይ ገበያው ደም በደም ሊሆን እንደቻለ አይተናል። የክሪፕቶ ዓለም እንግዲህ አንዱ ለየት የሚያደርገው ባህሪውም ይኸው የኢተገማችነት ባህሪውና አስከትሎ የሚመጣው ኪሳራ ነው። ለረዥም ጊዜ እቅድ የጠራሁላችሁ ካልሆኑ በቀር ሁሉንም ጥሪዎች በStoploss የታገዘ ግብይት እንዳደረጋችሁ ተስፋዬ ነው። በተረፈ ገበያው እስከመጨረሻው ወደታች የሚሄድ ባለመሆኑና ማደጉ ስለማይቀር አሁን የሰጠንን እድሎች የምንጠቀምበትን ታይሚንግ አይተን ወደገበያው የምንመለስ ይሆናል። ስንመለስ በተለይ በዚህ የደም ማእበል በጣሙን የተመቱን ነገር ግን ጥሩ እምቅ የማደግ እድል ያላቸውን ኮይኖች በይበልጥ ትኩረት ለመስጠት እንሞክራለን።