◁የሀገሬ ወጎች▷


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Kitoblar


📖እንኳን በደህና መጡ📖
➥ እዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ታሪኮች ፣ ልቦለዶች ፣ የአማርኛ መፅሀፍትን በ📙Pdf ፣ መሳጭ ግጥሞችን ፣ ትረካዎችን እና ሌሎችም ጠቃሚ ነገሮችን ያገኛሉ።

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri




⬜️#ነጫጭ_ጥቁረቶች⬛️
ክፍል አንድ
(by @Eyos18)
.
.
ይገርማል ወደዚህች ምድር ከመጣሁ አስራዘጠኝ ዓመታቶች
ነጎዱ ማለት ነዉ? እዚህች ምድር ከመጣሁ በልጅነት እንደ ልጅ
ከልጆች ጋር የተጫወትኩበት ፣ የእሳቱ እድሜ ደርሶ ልቤ አብጦ
ቤት ማንንም አልታዘዝም ያልኩበት እና ህይወትን ለመረዳት
የሚያስፈልጉ ወሳኝ ነጥቦችን የተረዳሁበት እድሜ ነጎደ። አሁን
ወደ ሀያኛ አመት ሩጫዉን ተያይዤዋለሁ።
በነዚህ ዓመታት ዉስጥ በህይወቴ ዉስጥ ብዙ ሰዎች አልፈዋል።
ብዙ የማይረሱ ተወዳጅ እና አናዳጅ ሰዎችን አዉቄያለሁ። አስራ
አምስት ዓመታትን መጨረሻዬን በመናፈቅ በትምህርት
አሳልፌያለሁ።
.
አሁን የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነኝ። ስሜ ፈዉዛን ይባላል። ጠይም እና
ተጫዋች ነኝ። ቁምነገር ላይ ቁምነገረኛ ፣ ቀልድ ላይ ደግሞ
ምርጥ ቀልደኛ ነኝ። በራሴ በጣም እተማመናለሁ። ብዙ ሰዎች
ጢባራም ነህ ይሉኛል። ከሩቅ ሲያዩኝ የሚጠሉኝ ቀርበዉ
የሚያዉቁኝ ደግሞ የሚወዱኝ አይነት ሰዉ ነኝ። ስለራሴ
እንደዚህ በድፍረት የማወራዉ ብዙዎች ከቀረቡኝ በኋላ ምን
ያህል ከሩቅ ሲያዉቁኝ ይጠሉኝ እንደነበር እና ሲቀርቡኝ እና
ሲያዉቁኝ በጣም እንደወደዱኝ በተደጋጋሚ ስለሚነግሩኝ ነዉ።
ለራሳችን ያለን አመለካከት ከሚገነቡበት መንገዶች አንዱ ሰዎች
ስለኛ በሚነግሩን ነገር ላይ የተመሰረተ መሆኑ እዉን ነዉ። ለዛ
እኮ ነዉ ቤተሰብ እምነት የሚጥልባቸዉ ልጆች ፣ ሁሌም
ጀግንነታቸዉን የሚነግራቸዉ ታዳጊዎች ከከፍታ መሰላል ላይ
ቆመዉ የምናየዉ። በአንፃሩ ደግሞ አታዉቅም እየተባሉና
ትንሽነታቸዉ እየተነገራቸዉ ያደጉ ልጆች ትንሽ እንደሆኑ ይቀራሉ።
በእርግጥ እየተሞገሱ የሚቀሽሙ እንደሚኖሩት ሁላ ከዚህ
የትንሽነት ቀንበር አምልጠዉ ታላቅ የሚሆኑ ጥቂቶችም
አይጠፉም።
.
እኔ ፈዉዛን ካመንኩበት ነገር ላይ ወደኋላ ዝንፍ አላዉቅም።
እንደወራጅ ዉሀ በተቀደደላቸዉ እንደሚፈሱ ከንቱ ሰዎች አሊያም
ወደነፈሰበት እንደሚነፍሱ ገለባዎች አይነት አይደለሁም። ሰዉ
ነኝ!! እንቢ የማለት አቅም አለኝ። ከአስተሳሰቤ እና ከማንነቴ ጋር
የሚጣረስን ነገር እምቢ ከማለት ወደኋላ አልልም። ሁሌም ቃሙ
ሲሏቸዉ ገረባ ሳይቀር የሚያኝኩ ፣ ጠጡ ሲሏቸዉ ፋራ
ላለመባል አተላ የሚጋቱ ፣ አጭሱ ሲሏቸዉ ከማን አንሼ ብለዉ
ኦ በጭስ ለመስራት አይናቸዉ ተጎልጉሎ እስከሚወጣ
የሚያጨሱ ምስኪን፣ እንቢ የማለት ወኔያቸዉ የተሰለበ ፣
የመጣዉ ጎርፍ ሁሉ እያላጋ የሚወስዳቸዉ፣ የማንነታቸዉን
ልዕልና ያላከበሩ ሰዎች ያሳዝኑኛል። በእንደዚህ አይነት ሰዎች
መካከልም ተከብቤ እነሱ የመጣዉ ጎርፍ ሁላ ሲያላጋቸዉ እኔ
በፅናት ቆሜ አዉቃለሁ። ለዛ ነዉ በድፍረት እንቢ የማለት አቅም
አለኝ የምለዉ።
.
በተማርኩባቸዉ ትምህርት ቤቶች ዉስጥ ሁሉ ዝነኛ ነበርኩ።
የትምህርት ቤት ክበባት ውስጥ መሳተፍ አዘወትር ነበር።
ስነፅሁፍ እወዳለሁ። አንዳንዴ እሞነጫጭራለሁ ብዙ ጊዜ ግን
የሌሎችን የስነ ፅሁፍ ስራዎች መድረክ ላይ ማቅረብ ይዋጣልኝ
ነበር። እናም ከዚህ ስብዕናዬ ጋር ብዙ ጓደኞችን አፍርቻለሁ።
ብሩክ እና ሄኖክ የልጅነት ጓደኞቼ ናቸዉ። ከብሩክ እና ሄኖክ ጋር
የተዋወቅነዉ የአምስተኛ ክፍል ተማሪዎች ሆነን ነዉ። አንድ
ትምህርት ቤት ከመማራችን በዘለለ ሰፈራችንም አንድ ነበር።
ብሩክ በአቋራጭ የሚከብርበትን መንገድ ዘወትር የሚያስብ
አይነት ሰዉ ነዉ። የሰዉ ታሪክ ማዳመጥ ይወዳል በተለይ የፍቅር
ታሪክ። አንድ ሰዉ የፍቅር ግንኙነት ዉስጥ ገብቶ ካገኘዉ ልምድ
ሊያወራ ከሚችለዉ በላይ ብሩክ የፍቅር ግንኙነት ዉስጥ
ለመግባት ከመፈለጉ የተነሳ ብዙ ይቀባጥራል። እኔ ከብሩክ ጋር
የምካፈለዉ የህይወቴ ጎን የፍቅር ህይወቴን ነዉ። ማዳመጥ
ስለሚፈልግ እነግረዋለሁ።
ሄኖክ ደግሞ ቀላ ያለ አጭር ቁመት ያለዉ ሚስኪን ልጅ ነዉ።
መልካም ልብ አለዉ። ወደ መልካም ነገር የሚጠራዉ ሰዉ ካለ
ሁሌም መልካም ለማድረግ ዝግጁ ነዉ። ነገር ግን የኔ የሚለዉ
አቋም የለዉም። እኔ ጋር ሲመጣ ከኔ ጋር ያነባል ፣ ከብሩክ ጋር
ሲሆን ደግሞ ከሱ ጋር ለመመሳሰል ይሞክራል። ከጊዜያት በኋላ
ሄኖክ ሰፈር ቀይሮ ከኛ ሰፈር ትንሽ ራቅ ወዳለ ቦታ ስለሄደ
ግንኙነታችን እየቀዘቀዘ መጣ። በአንፃሩ ደግሞ ከብሩክ ጋር
በጣም እየተቀራረብን ሄድን። ቀናት ቀናትን እየወለዱ ወራት
ከወራት ጋር እየተጋቡ ይኸዉ አስራ ዘጠኝ አመት አልፎኝ ወደ
ሀያ ሩጫዉን ተያያዝኩት።
.
ዛሬ ዉስጤ ላይ የመሰበር ስሜት ይሰማኛል። ሁሌም ጠንካራ
ነበርኩ ፣ ዛሬ ግን በህይወቴ ዉስጥ በፍፁም ሊከሰት ይችላል
ብዬ የማልጠብቀዉ ነገር ተከስቷል። ዉስጤ የመሰበር ስሜት
ይሰማኛል። ለካ የኛ ያልናቸዉ ሰዎች የእምነት ባንዲራችንን
ቀድደዉ በተቃራኒ ወገን በኩል ሲሰለፉ ፣ ያመናቸዉን ልባችንን
ፊት ሲነሱ ፣ ያጎረሷቸዉን እጆቻችንን ሲነክሱ በጣም ያማል።
ህመሙ የልብ ምታችንን ከወትሮዉ በተለየ እንዲመታ
ሲያስገድደዉ ፣ አይናችንን ከእንቅልፍ ጋር ሲያጣላዉ ፣ ስሜቱን
መግለፅ ሲከብደን ፣ በደፈናዉ ስብራት እንለዋለን። አዎን ሁሉም
ቀጥ ብሎ የቆመዉ የህይወት መዘዉራችን ሲናጋ ፣ ምንም
ባይገልፀዉም እንኳ መሰበር እንለዋለን። አዎ ዛሬ እኔም
ተሰብሬያለሁ። የስብራቴ ሁሉ ምንጭ ደግሞ ከክብር ዙፋኔ
ወርጄ አብሬያት የተጫወትኩት ፣ ለማንም ያላረከስኩትን እኔነቴን
ያረከስኩላት የህይወቴ ትልቋ ደስታ፣ ስህተት እና ስብራት
ኢክራም ናት።
ኢክራም ቆንጆዋ!! ኢክራም ሀዘንተኛዋ!! ኢክራም አፍቃሪዋ!!
.
ይቀጥላል...

SHARE @Ye_Hagere_Wegoch
SHARE @Ye_Hagere_Wegoch


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ኤሊያስ ሽታሁን

SHARE @Ye_Hagere_Wegoc
SHARE @Ye_Hagere_Wegoch


ሰው ልክ እንደ ወተት
"""""""""""""" """"""""""""""


ንፁህ እንደሆነ ከእናት ሆድ ሲወጣ ፣
እንባ እያፈሰሰ ምድር እንደ መጣ ፣
ትንሽ ሲድህ ሲቆም ደሞ ሲወድቅ ሲጋጥ ፣
ሲቦርቅ ሲጫወት እንደ ወተት ሲናጥ ።

እርጎ መሆን ሲመኝ ወጣትነት ሲሻ ፣
ራሱን ደብቆ መኖር ባሉት ዋሻ ፣
ከእሳት ተጥዶ ሆኖ እንደ አሬራ ፣
እየፈላ ያልፋል በሀዘን መከራ ።

ጉርምስናን አልፎ ፍላጎቱን ሲያህል ፣
እየተላመደው የመኖርን ትግል ፣
አካሉ ሲረጋ በእድሜ ጎልምሶ ፣
ያንን ልጅነቱን ይመኛል መልሶ ።

ሰው
እንደ እርጎ ይሰክናል እንደ ወተት ፈሶ ፣
ሁሉንም ይሆናል ጊዜን ተንተርሶ ፣
ሰው ኑሮውን ቢፅፍ
በጊዜ ሰሌዳ በምግባሩ ጠመን ፣
የሰው መጨረሻ
ቂቤ ሆኖ መቅለጥ አጓት ሆኖ መቅጠን ።


#በረከትዘውዱ

@ye_hagere_wegoch
@Ye_hegere_wegoch


#ንብ+#ሰው+#ሴት

ደከመኝ
ኪሳራ ነው ትርፉ
አልፎ አንቺን መመኘት
ከእሾሽ ተመልጦ ወለላሽን ማግኘት...

ንብ ናት ያንቺ ፍጥረት
በሩቅ እያየሁሽ
ፈራሁኝ ለመቅረብ
አልቻልኩም ለመቅረት
አቤት...የኔ....እፍረት
ማሩም ያንቺ አካል
እሾሽ ያንቺ ፍጥረት።

ከወለላሽ አልቀመስኩኝ
ነድፈሽኝ አላረፍኩኝ
ልቤን ብቻ አስደንግጠሽ
ምነው መሰወርሽ
ምነው ማስፈራትሽ...

ማሩ ያንቺ አካል
እሾሽ መች ያስነካል።



ዮኒ
ኣታን @yonatoz

Share @Ye_Hagere_Wegoch
Share @Ye_Hagere_Wegoch


አንችን ሆንኩኝ እኔ
ስሜን ብዘነጋ ቢረሳኝ እኔነት
ማንነቴ ጠፍቶ ባጣም እንኳ እምነት።
ግድ የለም አንች አለሽ :
በስምሽ ልጠራ ለብቻ ተፈጥረሽ፣
የሰውነት ወዝሽን ለኔነት ገብረሽ፣
እኔን ሰው ለማድረግ ከሰውነት ወተሽ
እኔም ቃል ገባሁኝ መልሼ ልከፍልሽ።
ላንች ብቻ ልኖር ቃል ያለኝ ላምላኬ
ባንች ተለክቶ የተገኜ ልኬ
እኔ ማለት አንች አንች ማለት እኔ
በስምሽ ምዬበት የገባሁ ምናኔ
ፈጣሪ የሰጠኝ ለክቶ ለጎኔ
ዛሬ ያበራሁኝ የታየ እኔነቴ
በሌላ እንኳ አይደለም :
ከፈጣሪ በታች ባንች ነው እናቴ ።
📝የእምዬ ልጅ


ደግሞ እንደ ትላንቱ ልክ እንደበፊቱ
ልትናፍቀኝ መጣህ ይሀዉ በክረምቱ

ከሰማዩ ጥጋት ደመናዉ ጨግጓል
በመብረቅ አስታኮ ሰማዩ ይጮኃል
እንጃ ምን እንደሚል
ንፋስ እያፏጨ በጀርባዬ ያልፋል

አንተ ነህ መሠለኝ.....
........................
........................
✍በትዝታ ወልዴ

JOIN👉 @Tizita_wolde

━━━━━━━◇የሀገሬ◇━━━━━━━
SHARE @Ye_Hagere_Wegoch
SHARE @Ye_Hagere_Wegoch
━━━━━━━◇ወጎች◇━━━━━━━━


የሷን
""""""""


በተስፋ ጭላንጭል በ ፍንጣቂ ብርሀን ፣
በጨለመው ለሊት አያታለሁ እሷን ፣
በብዙ ጫጫታ ከሺ ሰዎች መሀል ፣
ከሁሉም ለይቼ እሰማለሁ ድምጿን ፣
( የሷን )
ስንት ዜማ ሰበርኩ ፣
ስንት ስንኝ አፈረስኩ ፣
እኔ ግጥም ስፅፍ ፊደል ቀረ እርቃን ፣
ምንድነው ሚገልፀው የሚተካው ስሟን ፣
( የሷን )
የምድርን ምትሀት አስማትና ጠልሰም ፣
ሰው ተጠቅሞ እንደ እሷ ሰው አላፈዘዘም ፣
የአዳምን ዘር ሙሉ አሳጣችው እርባን ፣
ተዐምር አላት መሰል የሚያስወድድ ቀልቧን ፣
የደግነት ገዳም ማደሪያ አርጎት ልቧን ።
( የሷን )


#በረከትዘውዱ


@Ye_hagere_wegoch
@Ye_hagere_wegoch


እንዲያው ያለወትሮው
ልቤን ጭንቅ አለው

የረሳኝ ሰው አስታወሰኝ
የበደልኩት በይቅር ካሰኝ
ሆድ ያባስኩት ሆድ አባሰኝ
ያስነባሁት አስለቀሰኝ
የገፋሁት መቶ አቀፈኝ
ያወረድኩት አነገሰኝ

የሰው ልጅ ነብይ ነው አላወቀም እንጂ
ፍቅር ያሳይሃል ሞት ሲደርስ ከደጅህ

ሰከንድ
ደቂቅ
ሰዓት
ቀናት
ጊዜያት አለፉ ልቤ ሲብሰለሰል
እንጃ ብቻ....ሐሙስ ቀረኝ መሰል።

@yonatoz

Share @Ye_Hagere_Wegoch
Share @Ye_Hagere_Wegoch


መጀመሪያ ብቻ
""""""""""""" """"""""

ምንም ሚሆን የለም እንደ መጀመሪያው ፣
ሁሉም ይቀየራል ይሆናል በተራው ፣
መኖር ይቀጥላል ጊዜ ከቶ አይቆምም ፣
ሰው አመት ቢጨነቅ ሰአት አይቀይርም ።

አሮጌው በአዲሱ ወራትም በአመታት ፣
ትውልድ እየተኩ በሞትና ውልደት ፣
ሁሉም ተለውጦ ሲገኝለት አቻ ፣
መጀመሪያ ያለው መጀመሪያ ብቻ ።


#በረከትዘውዱ


@Ye_hagere_wegoch
@Ye_hagere_wegoch


(ምፅ!) ከንፈር ይመጠጣል
ከአባቱ ወንበር ልጁ ይቀመጣል
ጊዜ እንደው ሞኝ ነው
አርፎ አይቀመጥም ስንት ጊዜ ይሮጣል
ደግ ነው ስንለው ዳግም አይን ያወጣል

አይ ጊዜ
አይ ዘመን....

ዘመኑ ተረግሞ በዘመን ተቀጣ
በጊዜ ተሳቦ ጥጃም ቀንድ አወጣ

ያነ ጊዜ ደጉ ሸፍኖ ይወጋል
ይሄም ጊዜ ደጉ(ወይ ደጉ) በደን ይሸፍናል
ከተደፋ ፀጉር ምልጥና ይበጀን
ምን ፀሃይ ቢያቃጥል
ኮፍያ ልብስ ነው በገሃድ አልፈጀን

ጊዜውም አይደል

ተገላበጠ እና ዘመን በዘመን
ፀጉር እያበቀለ ፀሃይ አቃጠለን

(ምን ለማለት ፈልጌ ነው ራስህ ላይ ፀጉር ቢኖር ከፀሃይ አያስጠልልህም!)

ዮኒ
ኣታን @yonatoz

Share @Ye_Hagere_Wegoch
Share @Ye_Hagere_Wegoch


ሳታነሺው ሲቀር...

ፈገግታ ሳቅሽን ለመስማት ወድጄ
ከአንደበቴ ላይ የያዝኩት ሸምድጄ
ቀልድ አዘጋጅቼ ሳቅሽን ልገራ
ሳታነሺወሸ ሲቀር ስልኩ እየጠራ
ለራሴ ደግሜው ራሴው ሳኩበት
ብቻዬን ስስቅም እብድ ተባልኩበት
(ይሆን እንዴ እብደት?)

ድምፅሽን ለመስማት ላወራሽ ጓጉቼ
ዝርዝር ለቃቅሜ ካርዱንም ሞልቼ
ሳተነሺው ሲቀር ለብዙ አዋልኩት
ከጓደኞቼ ጋር እልፍ አወጋሁበት
ከዛም አልፎ ተርፎ ለሌላ ሰው ላኩኝ
ምስጋና፣ ምርቃት በብዙ አተረፍኩኝ!

በድምፅ ሳንረበሽ በምንም ሳንገታ
ላንቺ ለመደወል ከመረጥኩት ቦታ
ሳታነሺው ሲቀር ስልክሽ ተዘግቶ
አስተውል ጀመርኩ ያልታየኝን ከቶ
ፀጥታው ቢመቸኝ ግጥም ፃፍኩበት
የጥበብን ባህር በብዕር ቀዘፍኩበት!

ሳታነሺው ሲቀር ስልኩ ተከርችሞ
ንዴት ሊያበግነኝ ፊቴ ሳለ ቆሞ
ትርፌን አሰላሁት ካገኘሁት ጥቅም
በኢምንት ጊዜ ውስጥ ያለኝን አቅም

እናምልሽ ውዴ...

ሳታነሺው ሲቀር ልቤ ይህን አመነ
አንዳንዴም መገፋት ለራስ እነደሆነ።

✍Erma

Share @Ye_Hagere_Wegoch
Share @Ye_Hagere_Wegoch


ርዕስ አውጪለት
''''''''''''''''**'''''''''''''''''''''''''''''


ስስቅም ስጫወት ሳዝንና ስደሰት ፣
እንቅልፍም ስተኛ በህልምና ቅዠት ፣
ምስልና ሳቅሽ ይመጣል በአይኔ ፣
አልቻልኩኝም በቃ ናፍቀሽኛል እኔ ፣
ያንቺን ፍቅር ህመም ስያሜ አጣሁለት ፣
ላሸካሚ አይከብድም ርዕስ አውጪለት ።

ርዕስ አውጪለት የፍቅርሽን ስቃይ ፣
ራሴን አገኛለሁ ፎቶዎችሽን ሳይ ፣
ሺ ጊዜ እንዳየሁሽ አንዴ ሳትደርሺ ፣
በሀሳቤ መሀል ስትመላለሺ ፣
ሞኝ ነህ እያልኩት ያፈቀረሽ ልቤን ፣
ይብቃህ ተዋት እያልኩ ስገስፅ ራሴን ፣
ፍቅርሽን እያሰብኩ ለፃፍኩትኝ ግጥም ፣
ርዕስ አውጪለት ለጫንሽብኝ ሸክም ።

#በረከትዘውዱ

@yegtm_hywet
@yegtm_hywet


አንዳንድ ትዝታ አለ
-ዝምታችን -ከዝምታ ገዝፎ በአርምሞ በተዘጋንበት ጊዜ :በዕዝነ ልቡናችን በኩል ብሎ የሚጮህ ፡፡ በለሆሳስ ÷በዝግታ ካሳለፍነዉ የእድሜ ዘመን፡ ቅፅበቶቻችንን ከሽርፍራፊ የልጅነት ምስላችን በልጦ ፡በልቦቻችን ጥጋጥግ ካንጠለጠልነዉ ፡ ተናፋቂ ትዝታወች መሀል ፡ ምናለ በደገምነዉ እያልን የምንመኘዉ፡፡
ከትላንት ትዝታወቻችን ጋር ፡ ባንቀላፋን ቁጥር ሳንሰለች ደጋግመን የምንኖረዉ፡፡ አንዳንድ ትዝታ አለ ፡ እንደወይን እያደር ጣዕሙ የሚጨምር ፡ በእምባ በተምሸርንበት ጊዜ እንኳ ÷ በሐዘን ወህኒ ተወርዉረን ፡ መረሳት ክፋ እድል ፊት ለፊታችን ሲጋረጥ፡ የመኖር ጣዕም ሲጎመዝዝ ÷በእቅፋ ሚያስጠልለን፡፡ አንዳንድ ትዝታ አለ በዘመን መጎስቆል ባረመምንበት ጊዜ እንደ አዲስ የሚወልደን ፡ የማያረጅ የእድሜያችን ሞቃት ምዕራፍ ፡፡ አነዳንድ ትዝታ አለ --- አየ ጉድ - ትዝ አለችኝ መሰል፡፡

ያብስራ እዮብ(ደብተራዉ)፡፡

SHARE @Ye_Hagere_Wegoch
SHARE @Ye_Hagere_Wegoch


በዚች አለም ጭንቀት
በዚች አለም ውጥረት
ግራ ከቀኙ ጋር
ቀኝ ከግራው ጋር ፤ ግራ ተጋብቶበት
አቅሉን ሲያታልላት
ራሱን ሲዋሻት
ደህና ነኝ በሚል ቃል አለምን ሲቃዣት
እየኖረ ሳለ ፤ እየተንጓለለ
የህይወቱን ክፍል
#ደህና በምትል ቃል እየተዘለለ
የማስመሰል ህልምን ለራሱ አተረፈ
ሞት አይቀርምና ኑሮ ኑሮ አረፈ።

ዮኒ
ኣታን @yonatoz

Share @Ye_Hagere_Wegoch
Share @Ye_Hagere_Wegoch


😂 #የማጄላን_ግጥም_ከሚለው 😂

አንቺ የኔ ጨረቃ - እኔ ያንቺ ጨለማ
አንቺ የኔ ባህር - እኔ ያንቺ ዳርቻ
አንቺ የኔ አበባ - እኔ ያንቺ አፈር «ጭቃ»
አንቺ የኔ በቆሎ - እኔ ያንቺ ቆሮቆንዳ
አንቺ የኔ እንጀራ -እኔ ያንቺ ሊጥ
አንቺ የኔ ወተት - እኔ ያንቺ ስልባቦት
አንቺ የኔ ቡና - እኔ ግን አተላ
አንቺ የኔ በሶ - እኔ ኮስማና ጭብጦ
አንቺ የኔ ቀማሪ - እኔ ምርጥ አፍቃሪ !
አንድ ቀን ትወጂኛለሽ አልጠራጠርም ሲደርሰኝ ሎተሪ

አንቺ ፦
ያኔ አበባዬ ብለሽ እንዳላቆላመጥሽኝ
ዛሬ ማጣት ነክሶኝ እንደ ሎሚ ልጣጭ ጣል ጣል አረግሽኝ 😂

━━━━━━━◇የሀገሬ◇━━━━━━━
SHARE @Ye_Hagere_Wegoch
SHARE @Ye_Hagere_Wegoch
━━━━━━━◇ወጎች◇━━━━━━━━


የዘራኸውን እጨድ

ክፉ ነህ ማሪያምን ለሰው የማታዝን
እንደሾህ ለመውጋት መቼም የማትቦዝን
ምነው አይኔ ባያይ ገላህን ባላየው
ጆሮየም ቢደፈን ድምጽህን ባልሰማው
ከንፈርሰ ባይኖረኝ ጣአሙን ባልቀምሰው

አልገኝም ነበር ስምህን ስጠራ
ግን አንተ ክፉ ነህ ስሜት ማትጋራ
ላንተ ፍቅረ ማለት ላንተ መውደድ ማለት
ቃላት በመደደር ልዩነሽ እያሉ የዘወትር ስብከት
ለኔ ፍቅር ማለት በፍቅር እፍ ብሎ ለወደዱት መሞት

ከ ወወድሽኝ እያልክ ያለኝን ሰጥቼ
ሳስገባህ ከቤቴ በሮቼን ከፍቼ
መጥፊያ እንደሆን ልቤ ፈፅሞ ሳይገባው
ነይ ባልከኝ ቁጥር በርሬ እየመጣው
የኔነት ክብሬ ሰውነቴን አጣሁ
ተወው እድሌ ነው እኔ አላዝንብህም
የዘራኸውን እጨድ ሌላስ አልልህም

እምባየ ቢፈስም በመውደድ ተገዶ
ተዋት ታልቅስ ይላል አይቶት እንደመርዶ
እኔ ግን ማለቅሰው አዝኜብህ ሳይሆን ክፉ ተመኝቼ
አዝኜ ነው ላንተ ነገህን ፈርቼ
ጎርፍ ሆኖ ይውሰደኝ ያልከው የኔ እንባ
ደራሽ ሆኖ መጦ ቤትህ እንዳይገባ

እምባየን አርግፌ አልቅሼ አልሸኝህም
የዘረኸውን እጨድ ሌላስ አልልህም

✍ንፁህ

JOIN ➺ @simeten_begitm

━━━━━━━◇የሀገሬ◇━━━━━━━
SHARE @Ye_Hagere_Wegoch
SHARE @Ye_Hagere_Wegoch
━━━━━━━◇ወጎች◇━━━━━━━━


ከልብ ውስጥ አይርቅም
ምን ገደብ ቢኖረው
ምን መንገድ ቢረዝም
ወንድም በወንድም በክፉ አይታዘዝም
በቢሮክራሲ ስልት ጦር አንማዘዝም።

ዮኒ
ኣታን @yonatoz

Share @Ye_Hagere_Wegoch
Share @Ye_Hagere_Wegoch


ያው ክረምትም አይደል
++++++++++++++++



ያ ፀሀይ አለፈ ጋረደው ደመና ፣
ብርድ ይመጣ ጀመር ፀሀይ አለፈና ፣
በየጎዳናው ሰርጥ ሲያወርደው ዝናቡን ፣
ተጠሎ ያሳልፋል ሁሉም ይዞ ጥጉን ፣
አንዳንድም አይጠፋም ዝናብ የናፈቀው ፣
መጠለል ሳይፈልግ የሚበሰብስ ሰው ።

ያው ክረምትም አይደል

ጥንዶች ጎዳናው ላይ
ዣንጥላውን ጥለው በዝናብ ሲመቱ ፣
እዚ ደሞ ሴቷ
በመከዳቷ ላይ ሲደረብ ክረምቱ ፣
ከአልጋዋ ሳትወጣ
ቀኑን እንዳመሸች ሲነጋባት ሌቱ ፣
በነጎድጓዱ ድምፅ ብልጭ ሲል ብርሀኑ ፣
መብረቅ አስደንግጦት ሲደበቅ ህፃኑ ።

ያገላጣ ሜዳ በሳር ተሸፍኖ ፣
አፈሩ ለምልሞ አረንጓዴ ሆኖ ፣
ተፈጥሮ ተውባ በአበቦች ደምቃ ፣
ለአይን ስታሰማው መሳጩን ሙዚቃ ፣
የጋጣው እንስሳት አልፎላቸው ምጡ ፣
የደረቀን ትተው ለምለም ሳር ሲግጡ ፣
ዋሽንቱን ሲጫወት እረኛው በመስኩ ፣
የተፈጥሮ ዳራ ያምርበታል ልኩ ።

ያው ክረምትም አይደል

ገበሬው ሲዘራ አፈር ለም ሆኖለት ፣
እሱም እንዳመነው አምላክ ጠብቆለት ፣
በእርሻ እንዲያባርረው የህዝቦቹን ርሀብ ፣
ዘመኑ የሰላም እንዲሆን የጥጋብ ፣
መጣለት ክረምቱ ይዘራል ሊያርሰው ፣
ሰው ጦም እንዳያድር አጥቶ የሚቀምሰው ።

ደሞ መሸት ሲል በየጎዳናው ዳር ፣
ሆድን ሞቅ የሚያደርግ በቆሎ ይሸጣል ፣
ያሻው አስጠብሶ ያሻው አስቀቅሎ ፣
ሲጣፍጥ ብትቀምሺው ከወክ ጋ በቆሎ ፣
ስንቱ በዛው ቀረ አስጠልይኝ ብሎ ።

ያው ክረምትም አይደል

ትምህርት ይዘጋል
ሀገሩ በሙሉ በህፃናት ይሞላል ፣
መቦረቅ ያማረው እልሁን ይወጣል ፣
በልጆች ጫጫታ መንደር ይቀወጣል ፣
ቤት የሚያፈስበት ባልዲ ይደቅናል ፣
ጭጋግ በከደነው በቀዝቃዛው አየር ፣
አሎሎ የሚያህል በረዶ ይዘንባል ።

ከተሜው ከገጠር ገጠር ያለው ሸገር ፣
በዘመድ ጥየቃ ይጎበኛል ሀገር ፣
ሰካራም መጠጡን ትዳር ያለው ሚስቱን ፣
ጎኑ ሸጎጥ አርጎ እየሞቀ እሳቱን ፣
እንዲ እያዘናጋ ያልፈዋል ክረምቱን ፣
እጀ ጉርዱ ቀረ መልበስ የለም ቁምጣ ፣
ብርድ ነው ምግቡ ሳይደርብ ለወጣ ፣
ደረብ ደረብረብ ቁምሳጥን አስንቆ ፣
ክረምት እንዲህ ያልፋል በሀበሻ ደምቆ ።

#በረከትዘውዱ
SHARE @Ye_Hagere_Wegoch
SHARE @Ye_Hagere_Wegoch


አቅራቢ: ትዝታ ወልዴ
እና
መሳይ

ገጣሚያን: ትዝታ ወልዴ
እና
ዮኒ
ኣታን
Share @Ye_Hagere_Wegoch
Share @Ye_Hagere_Wegoch

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

12 674

obunachilar
Kanal statistikasi