Yop Poem ️


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Kitoblar


፨Yop Poem
አዳዲስ እና የቆዩ ግጥሞችና ወጎችን በቀላሉ ያገኙበታል። 🤲
እርስዎም የግጥም ተሰጥዖ ካልዎት መልቀቅ ይችላሉ።👐
Our main channale :- @Utophiainfo
ቻናላችንን #share ያድርጉ👍
for promo & cross 👉 @Yared642

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


£€¥¢$ dan repost
እኔ በየቀኑ ገንዘብ እየሰራሁበት ነው 😱😱💵💵💵‼‼
እናንተም አሁኑኑ ጀምራችሁ ገንዘብ መስራት ጀምሩ 💸💸💸‼‼‼‼
በየቀኑኑ ከ1000-15,000 ብር ገንዘብ መስራት ጀምሩሩ‼‼💸💸

ስራውን ለመጀመር ከስር ያለውን BUTTON ተጫኑ ‼‼


BEST ቪዲዮ dan repost
ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል

የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ  ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ
Add your channelAbove 1k+
@AB_WAVER


ምርጦቹ🥰🧡✨ dan repost
ፍቅረኛ አለህ እና ለሷ መልእክት ለመላክ ወይም እሷን ለማናገር ታግለህ ታቃለህ?


መልስክ አዎ ከሆነ ከአሁን በኋላ መታገል የለብህም🥰✨
የሁሉም ጊዜ ምርጥ የጽሑፍ ምክሮች🙌

የጽሑፍ ጠቃሚ ምክሮችን ይቀላቀሉ💫
              የጽሑፍ ምክሮች🖤




እነዚህ ቻናሎች ከ18 አመት በላይ ለሆናችሁ ብቻ ነው 🔞

if you like watching 18+ videos #Join የሚለውን ይጫኑ 🫦❤️🔞

» https://t.me/+cwDZLLGL9DtkNTFk

» https://t.me/+cwDZLLGL9DtkNTFk


BEST ቪዲዮ dan repost
ስለ ቴክኖሎጂው አለም ትኩስ ትኩስ መረጃ ከፈለጉ /join የምትለዋን Button በመጫን ወደ ቴክኖሎጂ አለም ይቀላቀሉ




ምርጦቹ🥰🧡✨ dan repost
የምስራች አሁን online ላላችሁ ብቻ ጥያቄ ና መልስ ልንጀምር ነው

1️⃣ ለወጣ 500 ብር ካርድ
2️⃣ ለወጣ  250 ብር ካርድ
3️⃣ ለወጣ  100 ብር ካርድ

👉 ዝግጁ ከሆናችሁ ጀምር የሚለውን ይጫኑ


𝐵𝑙𝑢𝑒 𝑑𝑒𝑣𝑖𝑙 𝑤𝑎𝑣𝑒 ✨ dan repost
🔥WAVE TIME 🖤 የቻናል ባለቤቶች ቶሎ በሉ Wave መግባት የምትፈልጉ .•°
      
• 💫ʙʟᴜᴇ ᴅᴇᴠɪʟ ᴡᴀᴠᴇ💫 •



🎤 1k+ subscribers  💎
🎤 10k+ subscribers  💎
🎤 15k+ subscribers  💎
🎤 20k+ subscribers  💎
🎤 50k+ subscribers  💎
🎤 100k+ subscribers  💎


ሁለተኛ ፎልደር ተዘጋጅቷል 5k+ ያላቹ ሰዎች ጥሩ አጋጣሚ ነው ኑ!🥰


□■□■□■□■□■□

"⛔️እባካቹ ከ 1k በታች ያላቹ እንዳትመጡ 🏴‍☠️


Inbox ✉️ ◇  ✈️@Infinity_0A




ኧረ በቃኝ ይሄስ ዓለም
ቀኔ ጎድሏል ሙሉ አይደለም።
ልሂድ ልግዛ ፣ አንዲት ገመድ
ልጓዝ ልብረር ፣ በሙት መንገድ።
ያስከፋኛል አገዛዙ ፣
ዙሪያው ገባው አያያዙ
የሰው ክፋት ጉድ ፣ መዘዙ
አላፈራም … ከምዘራው
እንባዬን ነው የማዘራው።
:
ልሂድ በቃ ልሰናበት…
ዘመኔ ላይ ልፍረድበት …
አንዲት ገመድ ላንዲት አንገት
በሽንቁሯ ልለፍበት ፤
ብዬ ጀመርኩ የሙት ጉዞ
ልቤ ቀልቤ ተመርዞ … ።
:
ግና ከንቱ…
ምን ዋጋ አለው?
:
አገኘኋት ስረማመድ
ያቺን ሸጋ ልጃገረድ
ገለጠችው ያንን ከንፈር
ይኸው ሳቀች ለክፋቱ
ልኑር በቃ ምናባቱ!



@Yoppoem


Utopia ዩቶጵያ dan repost
ምስጢራዊው የአፍጋኒስታኗ #ካንዳሃር_ግዙፍ_ኔፍሊምና የአሜሪካ #ወታደሮች_ያደረጉት_ትንቅንቅ
(ቱካ ማቲዎስ)

ይኽ እጅግ አስገራሚ ታሪክ የተፈፀመው ጥንት በድሮ ዘመን ሳይሆን አሁን ባለንበት 21ኛው ክፍለ ዘመን በ2002 እ.ኤ.አ እስካሁን ባላለቀው የአፍጋን-አሜሪካ ጦርነት ወቅት ነው።

ጉዳዩ በአሜሪካ መንግሥት #classified (ለብሔራዊ ደኽንነት ሲባል የሚጠበቅ ምስጢር) ከሚባሉ እጅግ ጥብቅና ድብቅ ወታደራዊ ምስጢራቶች አንዱ ቢሆንም ምንም ነገር ተደብቆ ስለማይቆይ ማፈትለኩ አልቀረም።

በተራራማዋና በረሃማዋ እጅግ ፈታኝ መልክዓ-ምድር ያላት አፍጋኒስታን የአሜሪካ ወታደሮች አንድ ሙሉ ብድን (squad) ደብዛው ይጠፋል።

ይኽን ክስተት ተከትሎ ልዩ ኦፕሬሽን አሳሽ ቡድን የጠፉ ወታደሮችን ፍለጋ ይሠማራሉ።

በፍለጋቸው ተራራማ ቦታዎችን አልፈው ወታደሮች ጠፉበት ከተባለው ግምታዊ የተራራ አምባ ላይ ወጥተው ከአንድ ትልቅ ዋሻ አቅራቢያ ይደርሳሉ።

ወደ ተልእኮው ሲያመሩ በጠፋው ቡድን ላይ የሆነው ነገር ሳያሳስባቸው አልቀረም፣ ያው እንደተለመደው ambush (የደፈጣ ጥቃት) መስሏቸው የነበረ ቢሆንም በደፈጣ ጥቃት ወቅት ሁሌም "የድረሱልን ጥሪ" እንደሚኖር አሁን ግን ምንም አይነት መልእክት ሆነ ጥሪ አለመደረጉ ግራ አጋብቷቸዋል።

ይኽ አሳሽ ቡድን በመሬት ላይ የመኪናና የእግር ዱካ መከተል አማራጭ አድርጎ አሰሳ ፍለጋ ጀመረ። ይኽም ክትትል ነው ወደዚኽ ትልቅና ጥልቅ ዋሻ ያደረሳቸው።

ዋሻ ማግኘታቸው ሳይሆን ትኩረታቸውን የሳበው ምስክርነት የሰጡ ወታደሮች ሲናገሩ "የተሰባበሩ የአሜሪካ ወታደራዊ እቃዎችና መገልገያዎች የተሰባበሩ ምንነታቸው መለየት አዳጋች የሆኑ ቅሪተ አጥንቶች፣ድንጋዮች፣የራድዮ መገናኛዎች በዋሻው መግቢያ ተበታትነው ማየታቸውና " የደፈጣ ወይም አንድ የሆነ የዱር እንስሳ ጥቃት እንደሆነ መገመታቸውን ያስረዳሉ።

የዋሻው መግቢያ እጅግ ሠፊና ጥልቅ በመሆኑ ቡድኑን በሙሉ አፋፉ በአንድ ላይ ለማስገባት ቢቻለውም ከመግቢያው ፈንጠር ብሎ ያለ ድንጋይ ወደ ውስጥ እይታቸውን ጋርዶታል።

ከውስጥ በሚሰሙትና እየቀረባቸው በመጣው ድምፅ ምክንያት ፀረ-ደፈጣ ጥቃት ለመፈፀም ከዋሻው መግቢያ ፈቀቅ ብለው ቦታ ቦታቸውን ይዘው መጠባበቅ ጀመሩ ግርምትን በፈጠረባቸው ፍጥነት ግን ከዋቻው ውስጥ፣ ከ 13-15 ጫማ (ከ4 ሜትር በላይ) ቁመት፣ ባለ ቀይ ረዥም ትካሻዎቹን የሸፈነ ፀጉርና ፂም፣ #ሥድስት_ጣቶችና ተደራራቢ ጥርሶች ያሉት ሰው መሰል (humanoid) ፍጡር በድንገት ከዋሻው በመውጣት ጥቃት ይፈፅምባቸዋል።

ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ እንሂድ:-
2ኛ ሳሙኤል 20 "ደግሞም፡በጌት፡ላይ፡ሰልፍ ኾነ፤በዚያም፡በእጁና፡በእግሩ፡ስድስት፡ስድስት፡ዅላዅሉ፡ኻያ፡አራት፡ጣቶች፡የነበሩት፡አንድ፡ረዥም፡ሰው፡ነበረ፤ርሱ፡ደግሞ፡ከራፋይም፡የተወለደ፡ነበረ።"

#ማስገንዘቢያ:- ይኽ #ራፋይ የተባለው የግዙፋኑ ኔፍሊምስ አባትና አስገኚ እንደሆነ ብዙ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሰ ነው።

{ ከታች በምስሉ ላይ ያያዝኩላችሁ ወታደሮች ከበውት ያለው የግዙፉ ገላጭ ምስልም ላይ 6 ጣቶችን መቁጠር ይቻላል።}

አፍጋኒስታን እንመለሥ:-

ከወታደሮቹ አንዱ ወደ ፍጡሩ በመሮጥ ይተኩስበታል፣ "በዚኽ ጊዜ ሁላችንም ከከባዱ እውነት ጋር ተፋጠጥን
ከዚኽ ቀደም ከነበረን ወታደራዊ ሥልጠናና ልምድ ውጪ በ adrenaline: (adrenaline (n) = በንዴት ወይም በፍርሀት ጊዜ ከኩላሊት በላይ ያሉ ዕጢዎች የሚያመነጩት ኬሚካል) በመታገዝ ሁላችንም መተኮስ ጀመርን" ይላል እማኝ ወታደሩ።


https://t.me/utophiainfo

Join us

@utophiainfo


ላገባሽ ነው እንዳታገቢኝ
'
'

አመጣጤ እንዳየሽው
ሚያምር መስሎሽ አትሸወጅ
ምላስ ስንት ያሳልማል
ወንድ እስኪዝ በእጅ

አልጋየ ላይ እትት ስልሽ
ስታለፊኝ ከሌት አዳር
የሴት ልብ ሞኝ ነው
ከተወራ ስለትዳር

ላግባሽ ግን አታግቢኝ
ላግባሽስ አልፈልግም
ካልጋ ቤት ካልሆን በቀር
በቀለበት አንሰርግም

/ ላገባሽ ግን አልፈልግም.../

የሴት ጫካ ገብቼ
ሳድን ሳካልል
አንቺን ድንግል ህፃን
ጣለሽ ከመሃል

እንደው ላልጋ አስቤሽ
ላግባሽ ላግባሽ ስልሽ
ጠዋት ልፈታሽ ነው
አትመኝኝ ባክሽ

አግባኝ አግባኝ አትበይ
አፈቀርኩህ ፍቅር
ምናምንቴ ትዳር ፥
ኩችኩች ሆታሄ
ምናምንቴ ቁማር ፣
እኔ አልታመንም
እሽ ካልሽ ግን
ላግባሽ ከአንሶላየ ጋር ፥

አንሶላ ውስጥ ገብተሽ
" ልስጥህ ሴትነቴን "
ጠዋት እንለያይ
መልሽ ቀለበቴን

ቢጃማ አወላልቀሽ
ፊቴ ስትቆሚ
በራቁት ሰመመን
ወንድ ልጅ ዝም ካለ
ይቅርብሽ ማመን

ማፍቀሬን ሳስመስል
አይደለም የሴት
የአጋንንት ልብ ሸውዶ ይገዛል
ተይ አትመኝኝ
ወንድ ልጅ ሲያሸንፍ
ዝምታ ያበዛል

ላገባሽ ነው አልጋዬ ውስጥ
ልጥልሽ ነው ጥሎሽ ዕንባ
ላንድ ቀን ከሆነማ
ለአንድ አዳር እንጋባ


@Yoppoem


ኑ ፍረሱ dan repost
#ይህን_ያውቃሉ🧐 ለነገሩ_እርሶ_ምን_ያውቃሉ😜


😁 በ1950 ዎቹ  ሰዉ በአማካኝ 18 ደቅቃ በቀን ይስቃል ፤ በአሁኑ ዘመን ከ 4-6 ደቅቃ ብቻ በቀን ይስቃል።
🧡🧡💜💜🧡💜🧡💜🧡💜🧡💜

እና ምን ለማለት ነው የኛ ቻናል ይሄን ችግር ለመቅረፍ አካፋና ዶማውን⛏ ይዞ ተነስቷል😄😁


@Nufresu


#እሱ እና #እሷ

#እሱ .   .   .
ብትበዪ ፍርፍር
ሥጋሽ ቢወፍር
ብታደርጊ ወርቅ
አየሽኝ እንደ ጨርቅ

#እሷ .   .   .
ታድያ ምን ችግር?
አትበልብኝ ግርግር
ፍርፍር ብበላ  . . .
ሥጋዬ ወፍሮ ቢተላ
ቢኖረኝ ወርቅ
ባደርግህም ጨርቅ
አታስወራኝ ክፉ ክፉ
ትዝብት ነው ደግሞ ትርፉ

#እሱ .   .   .
"ምን ችግር" አትበዪኝ
በግራ ዓይን ተይ አትዪኝ
የኖርናቸው ጊዜያቶች
ያ'ረግናቸው ውብ ክስተቶች
አስቢያቸው ቆም ብለሽ
ከ'ኔ'ጋ' እኮ ትዝታ አለሽ

#እሷ .   .   .
አታስታውሰኝ ያንን ጊዜ
ያየሁበት ጠፍቶ ወዜ
መልኬ ጠፍቶ አንተን መሰልኩ
ከእሳት ከሰል እኔ ከሰልኩ
ያንን ጊዜ ተው አታንሣው
እባክህን ይሄን እርሳው

#እሱ .   .   .
በጊዜ ላይ ሰበብ - ለምን ታደርጊያለሽ?
ያንን ጊዜ ባይኖር መቼ ትኖሪያለሽ?
ይልቅስ ችግሩ ጊዜን አታድርጊ
ባይሆን ይኸው እንደዚህ አድርጊ
ዓይንሽን ልየው - ነይ ከቦታችን
እንግደለው ትዝታችን
ገጥመን አፍ ካ'ፋችን

#እሷ .   .   .
እባክህን ተወኝ ልቤ ልብ ገዝቷል
ያለፈውን ታሪክ በሙሉ ረስቷል
በጻፍክልኝ ቁጥር ድንግጥ ይላል ልቤ
በፈጠረህ ተወኝ ልኑረው ሐሳቤ

#እሱ .   .   . (ለራሱ)
ብትሄድ እኔን ጥላ
ብታለቅስ እሱን ብላ
ለምን ጨርቅ ልሁን - ለምንስ ልጠላ?
ብታንቋሽሸኝም ቅስሜን ብትሰብረው
ክፉ አይወጣኝም-እኔም ዝም ልበል ሐሳቤን ልኑረው!!


@Yoppoem


ምታሳሳ መኳንንት ዘር የነበረች
ለሚያያት በጭንቅ ሀሳብ የታጠረች ፤

እዝን ትክዝ ካለችበት ቀና ብላ
መቀነቷን እያሰረች እንዳይላላ
አፈር ስትጭር የያዘችውን አንድ ስንጥር
ከእጇ ላይ እየጣለች

እንዲህ አለች ...

«የመኖር ሰይፉ ይሰለቅጣል
የዛሬ ጅራፍ አርባ ይገርፋል
ሆኖም
“ሰለቸን” ብንል አይለወጥም
የመሰልቸት ስለት ተስፋ አይቆርጥም።

ብቻ
የዕድሜ ዛቻ
የጊዜ ጡጫ ፋታ ቢያሳጣም
ሕልም ሲቸክ ወልቆ አይሰጣም።

አንዳንዴ ፣ የተስፋ ጡንቻ እየፈረጠመ
ሌላ ጊዜ ፣ የተስፋ መቁረጫዉ እየዶለዶመ
የመቁረጥ አቅሙ ስለደከመ

መቁረጥ ሲቃጣን
ሠይፉን ስላጣን
እናልማለን።

ልኩን ማየት እያባባን
እምቢኝ ስለን እያነባን
ተስፋ እናደርጋለን።

ተስፋ ለመተው ምን አቅም አለን?!
በሕይወት እስካለን ፣
ምርጫ ስሌለን እንበረታለን ።


@Yoppoem


'ግራ የተጋቡ ዕለት'

ከዕለታት አንድ ቀን ከእንቅልፌ ስነሣ
ወደ ውጭ ልወጣ ጫማዬን ሳነሣ
ሸተተኝ ... 'ሳምቡሳ ... ሳምቡሳ'
ወዲያው ወጣኹና ሻይ ቤት ገሰገስኩኝ
ገብቼ ስቀመጥ ብርጭቆ ሰበርኩኝ
ለማንሣት ሲሯሯጥ ደግ አስተናጋጁ
ከአፈር ደባልቄ አቆምኩበት በእጁ
የተሰበረውን ከመሬት ሲያነሣ
እኔም አልኩት . . .
አምጣልኝ አንድ 'ሳምቡሳ'
"አኹን አታገኝም ማታ ተመለሳ!?"
አለኝ . . .

እኔም ተመዘግዝጌ ስወጣ ከቤቱ
ከጓሮ መጣና ጠራኝ ባለቤቱ
"በጠዋቱ መጥተህ ልባችንን ሰበርከው
ና ክፈል ለሰበርከው"
አለኝ . . .

ሳየው ዓይኑ ሲንፈራፈር
አጎንብሼ ወደ አፈር . . .
አረመምኩ . . . ቻልኩት
'ለዚች ጥቂት ነገር ልባችሁን ሰበርኩት?!'
እያልኩኝ በውስጤ ...
ጠፋኝ መላቅጤ

ምክንያቱም ...
ብርጭቆውን ከመስበሬ የተነሣ
ሳልበላ ላድር ነው ያማረኝን 'ሳምቡሳ'😁


እንግዲህ ወዳጄ ሕይወት እንዲህ ናት፥ አትማረር!!


@Yoppoem


""
ተወው አትጨነቅ
ለአለም እልፍ ጓዝ፣
ይልቁን ተጠንቀቅ
ለራስህ ስትጓዝ፣

አይተህ ስትዝናና
የምድርን ስፋት፣
ችላ ያልከው ጠጠር
እንዳይሆን እንቅፋት!


@Yoppoem


እንደ ሰርከስ
(በእውቀቱ ስዩም)

መኖር በሀገርህ
የሰርከስ ትርኢት እንደማሳየት ነው
ስልጠናው ሳይኖርህ ::

በሚያድጥ ዳገት ላይ ፥በብጤህ መጋለብ
በሁለት መዳፎች፥ ሳይፎርሹ መቅለብ
-ደርዘን ሙሉ አሎሎ፥
አሎሎ ቢጠፋ ፥እሾህ ተደብልብሎ
በሳት ቀለበት ውስጥ ፥ማለፍ ሹልክ ብሎ፤

እንደ ህልም እሪታ፥ በሰለለ ገመድ
ባንድ እግር መራመድ፤

ይሄን ሁሉ አድርገህ፤ ትርኢቱም አልቆ
ካጥንቶችህ መሀል፥ አንዱ ተሰንጥቆ
አንደኛው ደንድኖ
እጅህ ወንፊት ሆኖ፤

ምንም ባትታደል፥ አንቱ የሚባል ስም
አሞጋሽ ለክብርህ፥ ነጋሪት ባይጎስም
ምናልባት ካተረፍክ-
ያልተራገፈ ጥርስ ፥ያልተሰበረ ቅስም  
የድል ሳቅህን ሳቅ፥  በተረፈው ጥርስህ
በወንፊት መዳፍህ፥ አጨብጭብ ለራስህ::


@Yoppoem


የቱ ጋር መሰለህ…
(ሚካኤል አ)

መባቻ ጅምርህ
የነፍስህ ድባቴ
ውድቀት እንግልትህ
ያኔ …
ባሽትሪ መያዣ ፣ በሲጋራ ብናኝ
በርጋፊ ቅጠል ፣ ድባቧ የሚቃኝ
በዛች ጠባብ ክፍል
ምጥን መሰብሰቢያ
ዙሪያህን ሰው ሞልቶህ
ቀንህን ማጣፊያ
ለአፕላይ ግብዣ የተዘረጋች ጣት
በሚግተለተል ጢስ ፣ ሰንቃልህ እሳት
እሷን ለመቀበል ስትፈግግ ባ’ክብሮት
የሰበብ አስባብ ጢስ
ቀረ ቤትህን ወርሶት።
የቱ ጋር መሰለህ?
በቀይ መብራት ፍካት
በቅልቅል ሽቶ አዲስ አይነት ክርፋት
በጭላጭ ብርጭቆ ተላኮበት ድራፍት
ከስፒከር ማህፀን ሙዚቃ ተለቆ
ጭፈራ እና ዳንሱ አንድ ላይ ተዛንቆ
የቀይ ሴት ታፋ ዓይንህ በስስ ሰርቆ
በምራቅህ ድርቀት ጉሮሮህ ተጨንቆ
ጠቅሰህ ስትጠራት
ያቺን የሞት ብልቃጥ
ከባቷ ፈልቅቀህ ዕፅዋን ስትቀምሳት
በገላህ ፍሰሀ መቅደስህን ናድካት ።
የቱ ጋር መሰለህ?
የልጅነት ልምድህ
ከሰንበት ቤት ገዳም
ምልልስ ብርታትህ
በሀይኪንግ ሲቀየር
የያሬዱ ወረብ
በእስክስታ ሲዛወር
ሳትቆም ለፀሎት
ሳይንስ ከእምነት ልቆት
ኒቼ ቦታ ሲወርስ የየኔታን መንበር
የነፍስህ ቁዘማ መንደርደሪያ ነበር።
ትዝ አለህ?
ዘር መራጭ ስትሆን
የደም ሴል መንጣሪ
ጆሮህ ዳባ ሲለብስ
ለፍጥረት እንግልት
ለህፃናት ጥሪ…
መንገድህ ሲሳለጥ
በ V 8 መኪና
ዝርግ አስፓልት ሲመስልህ
ጉርብጥብጥ ጎዳና ፤
ስቆልኛል ስትል ጥርሱን የነከሰ
እንባው አንሸራሽሮህ ጌታ ዘንድ ደረሰ።
ምላሹስ የከፋው መቼ ላይ ሆነና?
ጥሬ እየቆረጥክ ሆድህ ሲመረመር
እስቲም ሳውና ገብተህ ፊትህ ሲጭበረበር
በድሎትህ መኃል
ገላን የሚያኮስስ የእሾህ ስንጥር ነበር።
ትዝ አለህ?
መኝታህ በምቾት ተሞልቶ በአጀብ
እንቅልፍህ ሲናጠብ?
ትዝ አለህ?
በውድ ቀለም ቤቶች ልጆችህ ሲማሩ
ከግብረገብ ታዛ ተናንሰው ሲቀሩ?
ትዝ አለህ?
የጉያህ መልካም ሴት
የአጥንትህ ፍላጭ
አሁን ከምን ጊዜው
ሆነችብኝ ምላጭ?
ብለህ ስትቆዝም …
እንዲያ ነው አይዋ
ግፍ ፅዋው ሲሞላ
በትሩን አይመርጥም።
ትዝ አለህ?
ታወሰህ?
የቱ ጋር መሰለህ?
የተፈታው ውሉ
የጎደልክ ከሙሉ
ኧረ ስከን ሲሉ
ከዕድሜ የተማሩ
የጋሽ ውቤን ምክር
የእመት ጉሌን ዝክር
ረግጠህ ስትበር…
ስትሻገር ፣ ስጥስ
የምስኪናን ድንበር
የዛሬ ውድቀትህ ፣ በግጥም ሊነገር
ክንፍህ የተመታው ይሄን ጊዜ ነበር።
ትዝ አለህ?

አዎን እሱ ጋር ነው!


@Yoppoem

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.