ሰዋስው/@zsewasw


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


ሰዋስው

# ሰዋስው ማለት መሰላል ነው።
መሰላል የማይደርሱበት ነገር ተጠቅመው እንዲቻል እንደሚያደርጉት ሁሉ በዚህም ቻናል ችግር የሚባል ነገርን አስወግዳችሁ ወደ መልካም ነገር የምትወጡበትን ትምህርት ታገኛላችሁ።
እኔን ለማግኘት የሚፈልግ ሁሉ
+251934636523

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


ሐሜት👀

⚡️ሐሜት የሰይጣን ነው።

⚡️ ሰውን የሚያማ በገዛ ፈቃዱ አንደበቱን ለሰይጣን አሳልፎ የሰጠ ነው።

☄️ማማት በቤተ ክርስቲያን መለያየትን ያመጣል፣ ቤተሰብ ይበትናል፣ ወንድሞችን ያጣላል።

☄️ብንችል ስለ ሰው የምናውቀውን ጥሩውን እናውራ። የምናወራው ጥሩነት ከሌለው ደግሞ ቢያንስ ምንም አንበል።

⚡️ሔዋን ልክ እንደ አዳም እባብን "ሂጅልኝ" ብላ ብታባራት ኖሮ እነርሱም ከፈጣሪ ባልተጣሉ ሐሜትም ወደ ዓለም ባልገባ ነበር።

⚡️ ሐሜትን ማጥፋት ከፈለግን ሐሜተኛን እሺ አንበል። ማር ይስሐቅም "ወዳጁን በፊትህ የሚያንኳስሰውን ሰው አፉን መዝጋት ባትችል እንኳን ቢያንስ ሐሜቱን ከመስማት ተቆጠብ" ይላል። ሐሜትን ደስ ብሎህ ካልሰማኸው ደስ ብሎት የሚያማን ሰው ልትፈጥር አትችልም።

@Zsewasw/#ዘሰዋስው


👀 ዓቢይ ጾም

⚡️እንኳን ለዓቢይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ ።

⚡️የሰላም የበረከት የፍቅር ያድርግልን

@zsewasw/#ዘሰዋስው


👀 እግዚአብሔር ቢፈቅድና ቢወድ ዛሬ ማታ በዚህ ርዕስ የእዚአብሔርን ቃል እንማማራለን

⚡️ማታ 2:00 ላይ

⚡️በTikTok ማለት ነው

☄️Adress tiktok.com/@zsewasw


❄️“ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።”
— ሉቃስ 2፥11


🔔"ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ቃል እንሆነ ያስረዳ ዘንድ ከቅድት ድንግል ማርያም ሰው ሆኖ ተወለደ" 🏡ቅዱስ ኤፍሬም🏡


⭐️እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ


#ዘሰዋስው


❤️የሌለ ነገር መጠበቅ

➡️ዓለም የጥበቃ ስፍራ ናት። ጥበቃም ለአንድ ቀን ቆሞ አያውቅም። ይመጣል የሚሉትን ነገር ግለሰቦች፣ መንግሥታት ይጠብቃሉ። ጥበቃ ባይኖርም ሕይወት ብዙ ጣዕም አይኖራትም ነበር ። 5500 ዘመን የሰው ልጆች ቡሩኩን መሢሕ ሲጠብቁ ነበር ። እርሱ ቀጥሮ አይቀርምና የማርያምን ሥጋ ለብሶ ተገለጠ።

➡️የመጀመሪያ ምጽአቱን አጠናቅቆ ሲሄድ በዚያው ሰዓት እመጣለሁ ጠብቁ ብሎ አሁንም ለጥበቃ አስገዛን (የሐዋ. 1:11)። ላለፉት ሁለት ሺህ ዓመታት ቤተ ክርስቲያን ሙሽራዋን የምትጠብቅ ሙሽራይት ናት።

➡️ጥበቃ አያልቅም። በጥበቃና በፍጻሜው መካከል ብዙ ዓይነት ነገሮች ይከሰታሉ። ብዙ ጨለማ ፣ ብዙ ኀዘን፣ ብዙ ሰቆቃ ይኖራል። መጠበቅ ዋጋ ያስከፍላል። ፍሬው ግን ጣዕም አለው

🔂ላይሰጥ ጠይቁ ያላለ እርሱ ላይመጣ አያስጠብቅም



#ዘሰዋስው


❤️“ዛሬ ብላቴናዎችን ጎበዝ ተማሪ እንጂ ጎበዝ ክርስቲያን እንዲሆኑ ወላጆች እየተመኙ አይደለም ፡፡

👀ክርስቶስ የሌለበት ጉብዝና ወንዝ አያሻግርም።”


#ዘሰዋስው


✔️ከእራስ ጋር ማውራት

⏺ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ነው
⏺የመንፈሳዊነት እድገት ማሳያ ነው

#ዘሰዋስው


➕የማርታ ጸሎት➕

ማርያም: ትእዛዙን ሰሚ
ማርታ: የማይታዘዘውን አምላክ አዛዥ፣ "ንገራት" ባይ። (ሉቃ 10፥40)

➕እኛስ የእርሱን ትእዛዝ በትሕትና እንሰማለን ወይስ እንደ ማርታ "እንዲህ አድርግ? እንዲህ ተናገር?" ብለን የምንፈልገውን እናዘዋለን?

እስኪ ጸሎታችንን እናስተውል!

➕ዘሰዋስው


⏺ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር ተፈጸመ ናሁ ፤
አስምኪ ቦቱ አስምኪ ቦቱ ንግስተ ሰማያት
እንኳን ፡ አደረሳችሁ🔴


❗️ንጽሕና

✔️በንጽሕና ለመኖር እየታገለ የሚወድቅን እግዚአብሔር አያዝንበትም። ድካሙን እና ያልተቋረጠ ጥረቱን አይቶ ድል የሚነሣበትን መንፈሳዊ ጸጋ ይሰጠዋል እንጂ።

✔️ እንድትኖር በታዘዝከው ልክ ለመኖር ሞክረህ ስላልሆነልህ በራስህ ተስፋ አትቁረጥ።

✔️መሆንህን ብቻ ሳይሆን ፈልገህ መሞከርህን እግዚአብሔር ይጽፍልሃል። ሰይጣን አቁስሎህ ስለሻረው ጠባሳህ አትቆጭ።

✔️ ብዙ ጠባሳ እኮ  ለሚዋደቅ ጀግና ወታደር የክብር ምልክቱ ነው። አፈ ወርቅ ዮሐንስ እንደሚለው የማይቆስለው የማይዋጋ ብቻ ነው።

#ዘሰዋስው

@zsewasw


⭐ፍቅር እንደሞት የጸናች ናት

⏺አጥብቆ የወደደ ሰው በትንሽ ነገርም አጥብቆ ሊጠላ ይችላል
መጠንቀቅ አለብን!

⏺ለፍቅሩ ዋጋ ካልተሰጠው ፍቅር መች ነው የሚከፍለው ከተባለ ለፍቅሩ ዋጋ ሳይሰጠው ሲቀር ነው።

⏺ፍቅር ክብር ካልተሰጠው ይጠፋል።
⏺ፍቅር ክብርን መንካት የለበት።

⏺ክብርም ፍቅር ማስቀረት የለበትም።

⏺በመዋደድ የሚጠፋ ክብር መኖር የለበትም።

⏺እግዚአብሔር ያን ያህል የከበረ አምላክ ሲሆን ዝቅ ብሎ ነው የሚወደን።

⏺ከድሃ ቤት የሚገባ፣ እኛን የመሰለ፣የእኛን ስጋ ለበሰ፣በእኛ ቃል የተናገረ፣በእኛ የተመላለሰ የእኛን ውሃ የለመነ።

⏺ዝቅ ብሎ ነው የሚወደን።

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን

#ዘሰዋስው

@Zsewasw


ሰው ራሱን ሳያውቅ የሚቀረው ስላልቻለ ብቻ አይደለም፡፡ ራሱን ማወቅ ስለማይፈልግም ጭምር ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም ‹ራስን ማወቅ› ይዞ የሚያመጣው ጊዜያዊ ሕመም ወይም ትንሽ ስቃይ አለ፡፡ ወደ ራሳችን መመልከት ስንጀምር የማንፈልገውን ‹‹እኛነት›› በውስጣችን ልናገኘው እንችላለን፡፡ በዚህም መረበሽ፣ መቆጨት፣ ኃፍረት ይሰማን ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ስሜት ለማምለጥ ብለን ወደ ቅዠታዊ ዓለም ይሄድ ዘንድ ለራሳችን ልንፈቅድለት አይገባም፡፡ ለእኛ ከማንም በላይ ጠላት የሚሆንብን ይህ በውስጣችን የተደበቀውና ማወቅ የማንፈልገው ‹‹ስውር እኛነታችን›› ነው፡፡ ስለዚህም በጊዜ ራስን መርምሮ አፋጣኝ መልስ መስጠት ያስፈልጋል፡፡


#ዘሰዋስው

@Zsewasw


ፈቃደ እግዚአብሔር



ፈቃዱ ነገሮችን ሁሉ የመቆጣጠር አቅም አለው:- ፈቃዱ በአስር፣ በበሽታ፣ በምርኮ፣ በስደት ማለፍ ቢሆን እንኳ ይህን የመቆጣጠር _ አቅም አለው:: ችግሮችን የእግዚአብሔር ፈቃድ ባይቆጣጠር ኖሮ ማንም አይኖርም ነበር፡፡ የሰው ፈቃድ ግን ፈቅዶ አንድ ነገር ማድረግ ቢችልም የነገሩን ሂደት ግን መቆጣጠር አይችልም፡፡ ነገሩ ራሱ ሰውዬውን መቆጣጠር ይጀምራል፡፡

ፈቃዱ በመጨረሻ ይፀናል፡- ጠቢባን በጥበባቸው፣ ኃያላን በኃይላቸው ይጓዛሉ፡፡

በመጨረሻ የምታሸንፈው የእግዚአብሔር ፈቃድ ናት፡፡ በዚህ ዓለም ላይ የምንኖረው እንደምንፈልገው ሳይሆን እንደ ተፈቀደልን ነው፡፡ እንደ ፈቃዳችን እዚህ አገር፣ በዚህ የኑሮ ደረጃ አልነበርንም፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ ግን ትገድባናለች፡፡ ይህ መልካም ነው፡፡

እግዚአብሔር ከፈቀደው ውስጥ ምንም ክፉ የለም፡፡ «የጌታ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም አልን» (የሐዋ.ሥራ 21÷14)። ምንም አስተያየት ሳንሰጥ እንዲህና እንዲያ የሚሉ ግምቶችን ሳንሰነዝር በፈቃዱ ተስማምተን ማረፍ ይገባናል፡፡ «ሰው ዝም ብሎ የእግዚአብሔርን ማዳን ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው» (ሰቆ.ኤር 3፣26):

#ዘሰዋሰው


@zsewasw
@zsewasw




ወዳጄ ሆይ!
ላይህ እያለቀሰ ውስጥህ የሚጽናና ከሆነ እግዚአብሔር እየደገፈህ ነው። ማልቀስህ ሩኅሩኅነትህን፣ መጽናናትህ መንፈስ ቅዱስ ካንተ ጋር መሆኑን ያሳያል።

✍ዘሰዋስው


19

እንኳን ለኃያሉ መልአክ ለቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

#ዘሰዋስው


ወዳጄ ሆይ!
ትዕግሥት ልብን ከመድማት ይጠብቃል፣ የደማ ልብም በትዕግሥት ይፈወሳል። ነገርን በልኩ፣ ምድርን በማለፉ ለካው፣ የሚያስጨንቅህን አንሶ ታገኘዋለህ።

ዘሰዋስው

https://t.me/ZSewasw


ወዳጄ ሆይ!
በሁለት ዓይንህ ካለቀስህ መንገዱ ይጨልምብሃል፣ በአንድ ዓይንህ ስታለቅስ በአንድ ዓይንህ ክርስቶስን ተመልከት። ሁለት እጅህን ካጠፍህ ሚዛንህን መጠበቅ ያቅትሃል፣ አንዱ እጅህ ሲታጠፍ በአንዱ መሥራት ቀጥል። ልብህ መንታ ሁኖ ሲያስቸግርህ ነፍስህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ።

ዲን ዘሰዋስው

https://t.me/ZSewasw


ኃጢአት ጸሎት የማቋረጥ ውጤት ነው። እውነተኛ ጸሎት ኃጢአትን የማቆም ምልክት ነው። ሰው ኃጢአትን ልምዱ ካላደረገ በቀር እየጸለየ የሚበድል፣ ከአምላኩ ጋር እየተነጋገረ የሚያምጽ የለም። አዳም እጸ በለስን የቆረጠው ከአምላኩ ጋር የነበረውን ንግግር (ጸሎቱን) በማቋረጡ ነው። ይኸውም አዳምን ጠርቶ "ወዴት ነህ?" ባለው በፈላጊው ድምጽ ተረጋግጧል።

ዘሰዋስው


https://t.me/ZSewasw


ኦርቶዶክሳዊ አገልግሎት

ሰው ብቻውን አይሆንም ። ወይ ከእግዚአብሔር አሊያም ከራሱ ጋር ያወጋል ። ሰው ካገኘም ከሰው ጋር ያወራል ። ትዝታም እንደ አሁን ትኩስና ወቅታዊ ሁኖ ያነጋግረዋል ። የመምህር ቃልም ከሚኖረው ኑሮ ጋር ሲገጣጠም እንደ ገና አዲስ ፍንዳታ ሁኖ በውስጡ ይጮኻል ። መስፈርት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ቅዱስ ጳውሎስ የነገረኝን ከኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ጋር ማነጻጸር የጀመርኩት አሁን ነው ። ቤተ ክርስቲያን በእምነት የምትቀበል ፣ በፈሪሀ እግዚአብሔር መስፈርት የምትሾም ናት ። የአገልግሎት የመጀመሪያው መስፈርት ፍላጎት ነው ። አገልግሎት ጊዜን ሳይሆን ሕይወትን ሰጥተው የሚገቡበት ነው ። አገልግሎት የፍትፍት ሰደቃ ሳይሆን የመስቀል ጉዞ  ነው ። ገሀነምን ከሚያህል የእሳት ዓለም ነፍስ ሲያወጡ ወላፈኑ አይንካኝ ማለት ሞኝነት ነው ። የአገልግሎት ጉዞ ራስን መካድ ያለበት ነው ። ራሴን ከዛሬ ጀምሮ ያለ ክርስቶስ አላውቀውም ብሎ መማል ይጠይቃል ። ይልቁንም ኦርቶዶክሳዊው/ቀጥተኛው ጎዳና ብዙ እንግልት ከውስጥና ከውጭ ያለበት ነው ። ከክርስቶስ ጋር ያልሞተ ፣ ገና ውዳሴና ክብርን ነቅዐ ሐሰት ከሆነው ከሰው ልጅ የሚናፍቅ ጉዞው ይከብደዋል ። ኦርቶዶክሳዊው አገልግሎት በመከራ እድናለሁ ሳይሆን በመከራ የድኅነት ጉዞዬን እፈጽማለሁ ብሎ የሚያምን ነው ።


https://t.me/ZSewasw

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.