"ከሩሲያ እና ዩክሬን ድርድር ልንወጣ እንችላለን" አሜሪካ
:: :: :: :: :: :: :: :: ::
በሩሲያ እና ዩክሬን እየተደረገ ያለው የሰላም ድርድር ለውጥ የማያመጣ ከሆነ አሜሪካ ከድርድሩ ልትወጣ እንደምትችል የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ሩቢዮ ተናገሩ ፡፡
ማርክ ሩቢዮ ዋሽንግተን የሚጠበቅባትን አድርጋለች ከዚህ በኋላ ጦርነቱ የእኛ አይደለም (it’s not our war) ብለዋል፡፡
ሩቢዮ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አሜሪካ የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት በሰላም እንዲቋጭ እስካሁን ድረስ ያልተቋረጠ ድጋፍ ያደረገች ሲሆን፤ ከዚህ በኋላ ሀላፊነት አንወስድም፤ ጦርነቱን እኛ አልጀመርነውም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሞስኮ እና ኬቭን ጦርነት ለማስቆም ለ87 ቀናት ያህል ደክመዋል፤ ያሉት ሩቢዮ መጨረሻ ላይ የራሳችንን ውሳኔ ማስቀመጣችን አይቀርም ብለዋል፡፡
ሩቢዮ ከኬትኬሎግ እና ከመካከለኛው ምስራቅ መልዕከተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ፤ ከአውሮፓ ህብረት መሪዎች እና ከዩክሬን ባለስልጣናት ጋር በፓሪስ ቆይታ ካደረጉ በኋላ ነው ይህንን አስተያየት የሰጡት፡፡
ይህ የማርክ ሩቢዮ ንግግር አሜሪካ ጦርነቱ እንዲቆም በፑቲን ላይ ተጽዕኖ ትፈጥራለች ብለው ተስፋ አድርገው ለነበሩት፤ ለዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ከባድ ፈተና ሊሆንባቸው እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች ግምታቸውን አስቀምጠዋል ፡፡
አናዶሉ፤ ታምስ ኦፍ ኢንዲያ እና ዘ ኢኮኖሚክ ታይምስ አስነብበዋል ፡፡
@Zena_Adis_Ethiopia