Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
ስለዚህ በእንዲህ አይነት ከባድ ጉዳይ ላይ የታማኝ ዑለማዎችን ‘ተውጂሃት’ ከመከተል ባለፈ በግል ሃሳብ አጉል መኮፈስ፣ አለፍ ሲልም የቢድዐ አንጃዎችን አቋም ማራመድ፣ ከዚህም አልፎ የሱና ዑለማዎችን በነገር መውጋት የለየለት ብልግና ነው። ስሜት ልቡን ያወረው፣ አእምሮውን ያሰከረው፣ ብልሹ አካሄዱን እንደ ንቃት የሚቆጥር ‘ሩወይቢዻ’ (رويبضة) ካልሆነ በስተቀር እዚህ ሰፈር ሚንሀጁን የሚያከብር፣ ቀድሩን የሚያውቅ ሰለፊ አይልከሰከስም።