የኮቪድ-19 ክትትል ሲደረግላቸው ቆይተው የበሽታው ምልክት ያልታየባቸው 2,090 ሰዎች ክትትላቸው እንዲቋረጥ መደረጉን የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ ከውጭ ወደ ሀገር የገቡ 636 መንገደኞች ተለይቶ እንዲቆይ በተወሰነው መሰረት እስካሁን ለ14 ቀናት ለይቶ ማቆያ ውስጥ ይገኛሉ ነው ያለው፡፡
መንገደኞቹ ባሉባቸው ሁሉም ሆቴሎች የጤና ባለሙያዎችን በመመደብ የጤና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
በሌላ በኩል ከላይ የተገለፀው ውሳኔ ከመተላለፉ በፊት ከተለያዩ ሀገራት ወደ ሀገር የገቡ 873 ሰዎች በቤታቸው ሆነው በስልክ ለ14 ቀን በጤና ባለሙያዎች የጤና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ይህ መረጃ እስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስ የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ያሳዩ ሰባ ዘጠኝ (79) ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን ሁሉም ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡
(የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት)
መጋቢት 19ቀን 2012 ዓ.ም
---------------------------------------------------
ክቡራን ቤተሰቦች ሀሳብ አስተያየታችሁን የዜና የመረጃ ጥቆማችሁን ከሰር ባለው ሊንክ አድርሱኝ:: አመሰግናለሁ
አቤል ብርሀኑ (የወይኗ ልጅ)
👉@abel21bot