የተጀመሩ ምርምሮች ቀሪ ስራዎች ስላላቸው ህብረተሰቡ ራሱን ከኮሮናቫይረስ ለመከላከል ጥንቃቄ ከማድረግ መዘናጋት እንደሌለበት ተገለጸ
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክረታሪያት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት፤ የተጀመሩ የምርምር ስራዎች ተስፋ ያላቸው ቢሆንም ቀሪ ስራዎች አሉት።
ከውጭ አገር የሚመጡ ሰዎችን ለይቶ ለማቆየት የሚያስችሉ ተቋማት መዘጋጀታቸውንም ጠቁመዋል።
የሃይማኖት ተቋማት፣ ሆስፒታሎች፣ ግለሰቦችና ሌሎች ተቋማት በዚህ ረገድ ዝግጅት እንዳደረጉ ገልጸው፤ ተቋማቱ ያደረጉት ዝግጅት በኮሚቴ እየተገመገመ እንደሆነም ተናግረዋል።
እስካሁን ድረስ ከግለሰቦችና ከተቋማት 47 ሚሊዮን ብር መሰባሰቡን የገለጹት አቶ ንጉሱ፤ ድጋፉን በማዕከል ለማድረግና ለማቀናጀት የተዘጋጀው ኮሚቴ በአይነትም ሆነ በገንዘብ ተጨማሪ ገቢ ለማሰባሰብ በሚሌኒየም አዳራሽ ቦታ ማዘጋጀቱን ገልጸዋል።
(ኢዜአ)
መጋቢት 19ቀን 2012 ዓ.ም
---------------------------------------------------
ክቡራን ቤተሰቦች ሀሳብ አስተያየታችሁን የዜና የመረጃ ጥቆማችሁን ከሰር ባለው ሊንክ አድርሱኝ:: አመሰግናለሁ
አቤል ብርሀኑ (የወይኗ ልጅ)
👉@abel21bot