ደስታ ፣ እርካታ ለናንተ ምንድን ነው?
አንድ ወጣት ወደ ታላቁ ኢማም ሀሰን አል በስሪ ዘንድ ይመጣና እንዲህ ይላቸዋል፦
❝ከዚህ በፊት እርሶ ሲሉ እንደሰማሁት አንድ ሰው ሀጢያት መፈፀምን የሚያበዛ ከሆነ አላህ ብዙ ነገሮችን እንዳያገኝ ይከለክለዋል ብለዋል።❞
ኢማም ሀሰን አል በስሪ በትኩረት ያዳምጣሉ፣ ወጣቱም ንግግሩን ቀጠለ...
❝እኔ ማንኛውም አይነት ሀጢያት ፈፅሜአለሁ ፣ መልካም የሚባሉ ነገሮችን ደግሞ ሰርቼ አላውቅም።
ሆኖም ግን እኔ በጣም ቆንጆ ሚስት ፤ ደስ ደስ የሚሉ ልጆች እና በቂ መሬት ከብዙ ገንዘብ ጋር አለኝ ፣ ስኬታማም ነኝ። አላህ ምንም ነገር እንዳላገኝ አልከለከለኝም። እንዴት ብሎ ነው እርሶ እንዳሉት የሚሆነው?❞
ኢማም አል ሀሰን አል በስሪ እንዲህ ብለው መልስ ሰጡት፦ ❝ቂያመለይል ሰግደህ ታውቃለህ? ወደ አላህስ ዱዐ አድርገህ ታውቃለህ? በቃ ከዚህ የበለጠ ማጣት የለም…
አንድ ሰው ጌታውን የሚገናኝበት መንገድ ከተዘጋበት ትልቁን ማጣት አጥቷል። አንተንም እሱን ከመገናኘት አግዶሀል።❞ ሲሉ መለሱለት።
ምንኛ ያማረ መልስ ነው!
አላህ በቁርአኑ ያለውን አስታውስ...
የደስታ የእርካታ ምንጭ ፣ መገኛ አላህን ማውሳት ነው፣ ለሊትን በመስገድ ማሳለፍ ነው፣ እጆችን ወደ ላይ ከፍ አድርጎ ዱአ በማድረግ ነው።
❝ንቁ! አሏህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ❞
ሱረቱ ረዕድ 28
ያ አላህ!
ቀልባችንን አንተን በማስታወስ ላይ አበርታት! አንተን የምንገናኝበትን መንገድ ክፈትልን።
አሚን