እውቀትና የእውቀት ባለቤቶች ደረጃ ክፍል - 22 በዱንያ መጠመድ ለእውቀት እንቅፈት ይሆናል ገንዘብ በራሱ የሚወገዝ አይደለም። ገንዘብም ይሁን ሌሎችን ጉዳዮችን አስመልክቶ ኢስላም የማይናወጥ ፣ ለሂዎት ቀላልና ምቹ ፣ መልካም የተባለን ሁሉ የሰበሰበ ፣ ጉዳትን የሚከላከል ስርአትና ህግ አስቀምጧል።
ረሱል ﷺ ለአምር ብን አልዓስ የሚከተለውን ብለውታል ፡
"يا عمرو نعم المال الصالح للرجل الصالح" “አምር ሆይ! መልካም ገንዘብ ፣ ለመልካም ሰው ምን ያማረ ነው!” ለገንዘብ የተቀመጠለት ሚዛን ዲንን ፣ ሶላትን ፣ ኢልምን በማይጋፋ ፣ ሀላል በሆነ መልኩ በሀጃው ልክ ሰርቶ ማግኘትን ነው። ከዚያም ለተፈቀዱና አሏህ ለሚወዳቸው ነገሮች ማዋል ነው። ድንበር ማለፉ ፣ እርሱን በመሰብሰብ አብዛኛውን ወቅቱን ማባከኑ ግን ለጥፋት ይዳርጋል።
የቁርኣንን መረጃዎች ፣ የነብዩን ሱና ላስተዋለ የሸሪአው ትኩረቱና ቅስቀሳው በዙህድ (ለዱንያ ብዙም ትኩረት አለመስጠት) እና በተሰጠው መብቃቃት ላይ ነው፡፡ ብልጭልጭ እና ውብ የሆነችውን ዱንያ ለማግኘት ሸሪአዊ የሆነውን ፍኖት በመልቀቅ በሀራም ገንዘብ መሰብሰብን በማውገዝ ላይ ነው፡፡ የሰው ልጅ የገንዘብ ስግብግብነቱ መነሻ ምንጩ ምን ይሆን? ከተባለ ሁለት ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል፡
አንደኛው ፡ ነፍሶች - አሏህ ያዘነላቸው ካልሆኑ በቀር - በማንኛው ሁኔታ ገንዘብን በመፈለግ ፣ እርሱን ለማግኘት በመፎካከር ላይ የተፈጠሩ መሆናቸው ነው :
አላህ ﷻ እንደነገረን ፡ زُيِّنَ لِلنَّاسِ حُبُّ الشَّهَوَاتِ مِنَ النِّسَاءِ وَالْبَنِينَ وَالْقَنَاطِيرِ الْمُقَنطَرَةِ مِنَ الذَّهَبِ وَالْفِضَّةِ وَالْخَيْلِ الْمُسَوَّمَةِ وَالْأَنْعَامِ وَالْحَرْثِ ۗ ذَٰلِكَ مَتَاعُ الْحَيَاةِ الدُّنْيَا ۖ وَاللَّهُ عِندَهُ حُسْنُ الْمَآبِ
"ከሴቶች፣ ከወንዶች ልጆችም፣ ከወርቅና ከብር፣ ከተከማቹ ገንዘቦችም፣ ከተሰማሩ ፈረሶችም፣ ከግመል ከከብትና ከፍየልም፣ ከአዝመራም የሆኑ ፍላጎቶችን መውደድ ለሰዎች ተሸለመ፡፡ ይህ ሁሉ የቅርቢቱ ሕይወት መጠቀሚያ ነው፡፡ አላህም እርሱ ዘንድ መልካም መመለሻ (ጀነት) አለ፡፡" (አልኢምራን ፡ 14)
الْمَالُ وَالْبَنُونَ زِينَةُ الْحَيَاةِ الدُّنْيَا ۖ وَالْبَاقِيَاتُ الصَّالِحَاتُ خَيْرٌ عِندَ رَبِّكَ ثَوَابًا وَخَيْرٌ أَمَلًا
"ገንዘብና ወንዶች ልጆች የቅርቢቱ ሕይወት ጌጦች ናቸው፡፡ መልካሞቹም ቀሪዎች (ሥራዎች) ከጌታህ ዘንድ በምንዳ በላጭ ናቸው፡፡ በተስፋም በላጭ ናቸው።" (ከህፍ ፡ 46)
ሁለተኛው ፡ ከሀቅ እንዲወጣ ፣ ለገንዘብ ያለው ፍላጎት ወሰን እንዲያልፍ የሰይጣን ቅስቀሳ ነው።
አላህ ﷻ የሚከተለውን ተናግሯል ፡
أَلْهَاكُمُ التَّكَاثُرُ
حَتَّىٰ زُرْتُمُ الْمَقَابِرَ
"በብዛት መፎካከር (ጌታችሁን ከመገዛት) አዘነጋችሁ፡፡ መቃብሮችን እስከምትጎበኙ ድረስ፡፡" (ተካሱር ፡ 1-2)
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ ሁለት ምክንያቶች በኡመቱ ላይ ተሰባስበው ከተገኙ በገንዘብ ላይ ያለው እሽቅድድም እና ፉክክር እየጨመረ ይሄዳል ፤ በእርሱም መፈተን ይኖራል፡፡ ገንዘብ በርካታውን ሙስሊም ህብረተሰብ ከመልካም ተግባር አዘናግቶት ይገኛል። ማህበረሰቡ ከተዘናጋባቸው መልካም ተግባራት መካከል አንዱ ሸሪዓዊ እውቀትን መፈለግ ነው፡፡ ስለዚህ ገንዘብን ለማግኘት በጉልበትም በጊዜም ከፍተኛ መስዋእትነት እንደምንከፍል ሁሉ እውቀትን ለመሰብሰብና ለማካበትም ከፍተኛ ትግል ማድረግ ይጠበቅብናል።
አንደኛ ፡ ገንዘብን መሰብሰብ ፈተና መሆኑን ማስታወስ ፡
ኢማም አህመድ እና ቲርሚዝይ በዘገቡት ኢያድ ብን ከእብ የሚከተለውን ሀዲስ አስተላልፏል ፡
"إن لكل أمة فتنة ، وفتنة أمتي المال" "ለእያንዳንዱ ኡመት ፈተና አለው ፤ የእኔ ኡመቶች ፈተና ገንዘብ ነው።" የገንዘብ አጠቃቀሙን ያሳመረ ፣ ከዋጅባት ያላዘናጋው ፤ ሀራም ነገር ላይ ያልጣለው ይህ ተመስጋኝ ፣ ከአሏህ ዘንድ ከፍተኛ ምንዳ የሚያገኘው እርሱ ነው። ከሶላት ፣ ከዘካ ሸሪዓዊ እውቀትን ከመፈለግ ያዘናጋው ይህ ከአሏህ ዘንድ ተቀጭ ነው።
ኢማም አህመድ በዘገቡት ሐዲስ አቡ ዋቂድ አልለይሲይ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፈዋል ፡
አላህ ﷻ የሚከተለውን ተናገረ :
“እኛ ገንዘብን ያወረድነው ሶላትን ደንቡን ጠብቆ እንዲሰገድ ፣ ዘካ እንዲሰጥ ነው፡፡ ለአደም ልጅ አንድ ሸለቆ ቢኖረው ሁለተኛ ሸለቆ እንዲኖረው ይመኛል ፣ ሁለት ሸለቆ ቢኖረው ደግሞ ሶስተኛ ሸለቆ እንዲኖረው ይመኛል፡፡ የሰውን ልጅ ሆድ አፈር እንጅ ሌላ የሚሞላው የለም፣ ከዚያም በቶበተ ሰው ላይ አላህ ተውበቱን ይቀበለዋል፡፡” ሀሰን አልበስርይ የሚከተለውን ተናገሩ ፡ "إن لكل أمة وثنا يعبد ، ووثن هذه الأمة الدرهم والدينار" “ለእያንዳንዱ ማህበረሰብ የሚያመልከው ጣኦት አለው ፤ የዚህ ማህበረሰብ ጣኦት ዲርሃም እና ዲናር ነው፡፡” ስንቶች ናቸው ለገንዘብ ብለው ከሶላት የሚዘናጉ? ለገንዘብ ብለው ዝምድናን የሚቆርጡ? ለገንዘብ ብለው ሀራም የሚበሉ? በገንዘብ ምክንያት ስንቶች ናቸው ከጎረቤት ፣ ከዘመዶቻቸው ጋር የተቆራረጡ?ስንቶች ናቸው ቁርዓንን የተው? ፣ እውቀትን የተው? ፣ አላህን ከማስታወስ የተው?
አላህ ﷻ የሚከተለውን ተናግሯል ፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تُلْهِكُمْ أَمْوَالُكُمْ وَلَا أَوْلَادُكُمْ عَن ذِكْرِ اللَّهِ ۚ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْخَاسِرُونَ
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁ አላህን ከማስታወስ አያታሏችሁ፡፡ ይህንንም የሚሠሩ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎች ናቸው፡፡" (ሙናፊቁን ፡ 9)
በአብዛኛው ሙናፊቆች በገንዘብ በመጠመዳቸው ምክንያት ከረሱል ﷺ ጋር ጅሀድ አይወጡም። ከጅሀዱ ትልቁ ጅሀድ ደግሞ ለኢልም የሚደረገው ጅሀድ ነው። ሙናፊቆችን ከኢልም እንዲያፈገፍጉ የሚያደርጋቸው ለዱንያ ያላቸው ከፍተኛ ፍላጎት ፣ ለአኼራ ያላቸው ፍላጎትና ስሜት የቀዘቀዘ በመሆኑ ነው።
አላህ ﷻ የሚከተለውን ተናግሯል ፡