"አምላካችን አንድ ነው" የእየሱስ አስተምህሮ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው ፡፡
ሱረቱ መረየም 36
وَإِنَّ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبُّكُمْ فَٱعْبُدُوهُ هَٰذَا صِرَٰطٌ مُّسْتَقِيمٌ
(ዒሳ አለ) «አላህም ጌታዬ ጌታችሁም ነውና ተገዙት፡፡ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው፡፡»
በማርቆስ ወንጌል ላይ ትኩረትን ሊሻ ግን ትኩረት የተነፈገ አንኳር የሆነን ክስተት ገጠመኝ እናገኛለን፡፡ እየሱስ የብሉይ ኪዳኑን የአንድ አምላክ እምነት (monotheism) ያፀደቀበት፡፡ ከአይሁድ ህግን የተማረ ያወቀ ለእየሱስ ጥያቄ ያቀርባል "ከህግ ሁላ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ትዕዛዝ የቱ ነው ይላል"
(የማርቆስ ወንጌል ምዕ. 12)
----------
28፤ ከጻፎችም አንዱ ቀርቦ ሲከራከሩ ሰማና መልካም አድርጎ እንደ መለሰላቸው አስተውሎ። ከሁሉ ፊተኛይቱ ትእዛዝ ማናቸይቱ ናት? ብሎ ጠየቀው።
29፤ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ። እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ *ጌታ #አምላካችን አንድ ጌታ ነው*፥
32፤ ጻፊውም። መልካም ነው፥ መምህር ሆይ፤ *#አንድ ነው ከእርሱም በቀር ሌላ የለም* ብለህ በእውነት ተናገርህ፤
34፤ ኢየሱስም በአእምሮ እንደ መለሰ አይቶ። *አንተ ከእግዚአብሔር መንግሥት የራቅህ አይደለህም* አለው። ከዚህም በኋላ ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም።
🎯 ይህ ገጠመኝ ታድያ እየሱስ አይሁዶች በአምላክ ዙሪያ ስላላቸው የተዛባ እምነት ግልፅ የሚያድርግበትና ስለ ስላሴ በመለኮት አንድ በአካል ሶስት ፣ሶስቱም እኩል ስልጣን እንዳላቸው የሚያብራራበት እድል ነበር
ከላይ እንዳየነው እየሱስ ከዚህ በተቃረነ መልኩ ከኦሪት ዘዳግም 6:4 ላይ ያለውን ህግ በመዝከር እንዲሁም ከአይሁድ አዋቂ ከነበረው ፃህፍት እሳቤ ጋር ሙሉ በሙሉ ተስማመተዋል
እየሱስ የስላሴን አስተምህሮ ሳይዘክር የአይሁዳውያኑን ስለ አንድ አምላክ እሳቤ በመደገፍ ብሎም ጠያቂውን አንተ ከእግዚአብሔር መንግስት የራክ አይደለህም ብሎ መሰክሮለት እናገኛለን
የአይሁድ ህዝብ በስላሴ በጭራሽ አያምኑም በነብያትም አልተስተማርንም በብሉይም አልተዘከረም ብለው የነሱ ሊቃውንት ይህን ያፀድቃሉ
አለቃ የነበሩን ነቢያቶች በአምላክ ትዕዛዝ መሰረት ያስተማሩን እርሱ አንድ እና ያለ አጋር መሆኑን ነው ፣ እነዚያ የጠመሙት የሚያቀርቧቸውን የተሳሳቱን አስተምህሮ ከልባችን ለማስወገድ ፈጣሪያችን [ዘዳ 6-4 (" እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው፤")] ይህንን መሰረታዊ ድንጋጌ አደረገው ፡፡ ነገር ግን ክርስቲያኖቹ አምላክ ከሦስቱ አንዱ ነው አምላካችን ፣ ጌታ ሶስት አካል ነው ፣ ሁሉም አንድ ናቸው የሚለውን ያስተምራሉ፡፡ባለማወቃቸው ከሚናገሩት ነገር ፈጣሪያችን የጠራ ነው ፡፡
Moshe ben Maimon, the Rambam or Maimonides, in his The Essay on Resurrection, trans. Abraham Halkin in The Epistles of Maimonides: crisis and leadership.
አምላክ ራሱን ግልፅ በሆነ መልኩ እርሱ አንድነቱን ገልጾል
★ኢሳይያስ 44:24 ሰማያትን ለብቻዬ የዘረጋሁ ምድርንም ያጸናሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ ከእኔ ጋር ማን ነበረ?
★ዘዳ.32:39፤ አሁንም እኔ ብቻዬን እኔ እንደ ሆንሁ፥ ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ እዩ፤
★ዘዳ 32:12 እግዚአብሔር ብቻውን መራው፤ ከእርሱም ጋር ሌላ አምላክ አልነበረም።
ነብያትም በብሉይ እንደ አብራሀም ኖህ ሙሴ (በእነርሱ ላይ ሰላም ይሁን) አንዳቸውም ስለ ስላሴ አልሰበኩም የነርሱ አንኳር ትምህርት አንድ አምላክ ከርሱ በቀር ሌላ የለም እርሱ ፍጡራኑን አይመስልም እርሱም ብቻ ነው አምልኮ የሚገባው ነው ፡፡
🎯 ታድያ አምላክ በቁጥር የማይዘለቁ ነቢያትን ልኮ እነሩሱም ስለ አምላክ አንድ መሆን ሲዘክሩ ቆየተው ከሺ ዘመናት በሇላ አልፎ ድንገት እርሱ መለኮት ስላሴ መሆናቸውን ቢገልጽ ይህ ትርጉም አለውን⁉️ ከዚህ ቀደም የነበሩትን የነብያቱንስ ትምህርት አይጣረስምን‼
ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ