አስገራሚ እውነታዎች


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Siyosat


ያልተሰማ እንጂ ያልተደረገ ነገር የለም

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Siyosat
Statistika
Postlar filtri


Zemen Promotion dan repost
የቴሌግራም Profile ማን እንዳየ ለማወቅ አሪፍ ቦት 2025 ላይ በTelegram Created የተደረገ ቦት ነው

ሁላቹም ተጠቀሙበት ትደሰቱበታላቹ

ቦቱን የማግኝት Start ወይም 🤖 BOT 🤖 የሚለውን ይንኩ ይደሰቱበታል


ᥲძძ ᥡ᥆ᥙr ᥴһᥲᥒᥒᥱᥣ

☑️ 𝑺𝒑𝒐𝒏𝒔𝒐𝒓𝒆𝒅 𝒃𝒚: LOVE & POEM


የ1000 ብር ካርድ ሊለቀቅ ነው 9 ደቂቃ ብቻ ነው የቀረው። ቶሎ ከስር JOIN ሚለውን ነክታቹ JOIN REQUEST ላኩ 🏃‍♀️🏃‍♂️

https://t.me/+e8G4cdr5hv1hNTE8
https://t.me/+e8G4cdr5hv1hNTE8


አሳዛኙ የብራዚላዊ ታዳጊ ተጫዋች ክስተት!

የዛሬ አመት በብራዚል ከሚገኙ ኮከብ ወጣት ተጫዋቾች ውስጥ አንዱ የሆነው ዲያጎ ፈርናንዶ በትልቅ ደረጃ እየተጠበቀ ዘግናኝ አደጋ አጋጠመው

ከጓደኛው ጋር በሞተር ሳይክል እየተጓዘ ከፍተኛ አደጋ አጋጠመው የጓደኛው ህይወት ሲያልፍ ባለተሰጦኦ የእግርኳስ ተስፈኛ ዲያጎ በአደጋዉ አንድ እግሩን አጣ ረዘም ላለ ጊዜ የማገገም ሂደት ውስጥ ገባ

ከአንድ አመት የማገገም ሂደት ቡሃላ ዲያጎ ፈርናዶ በአካል ጉዳተኞች ውድድር የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች በመባል የዋንጫ አሸናፊ ሆነ ነገሮች ባልፈለገው መንገድ ቢሄዱም የዲያጎ ተስፋ አለመቁረጥ እጅ የሚያስደንቅ ነበር

ህይወት በየት አቅጣጫ እንደምትወስድ አይታወቅም የዛሬ አመት በትልቅ ደረጃ የሚጠበቅ ልጅ ነበር እኛ ባቀድነው ሳይሆን በተፃፈልን መሰረት ነው የምንጓዘው እግሩን ቢያጣም በህይወት ተርፎ እዚህ ላይ ደርሷል ዲያጎ ፈርናንዶ




Zemen Promotion dan repost
🌄 ለሁሉም እምነት ተከታዮች በሙሉ አሪፍ ዜና ይዘንላችሁ መተናል ለሁሉም እምነት ተከታዮች የሚሆኑ አሪፍ አሪፍ ፕሮፋይል ይዘን መተናል መርጣችሁ ተቀላቀሉን 🌄

☑️ 𝑺𝒑𝒐𝒏𝒔𝒐𝒓𝒆𝒅 𝒃𝒚: LOVE & POEM


Zemen Promotion dan repost
🫀የፍቅር ቀጠሮ ለመያዝ 10 ወርቃማ ህጎች !!


Zemen Promotion dan repost
🌹 ወንድሜ ፍቅረኛህን ትወዳታለህ
እህቴስ ፍቅረኛሽን ምን ያክል ትወጂዋለሽ ❤️ ምርጥ ምርጥ የፍቅር ጥቅሶች እና የፍቅር ታሪኮች የሚቀርቡበት ቻናል ይዘንላችሁ መተናል ቤተሰብ ይሁኑ🌹👇

𝑺𝒑𝒐𝒏𝒔𝒐𝒓𝒆𝒅 𝒃𝒚: ፍቅር እና ግጥም


Zemen Promotion dan repost
ስለ ፍቅር ብቻ የሚወራበት ቻናል....❤❤❤
https://t.me/+PTClkgVZ-MI2MDc0
https://t.me/+PTClkgVZ-MI2MDc0


Zemen Promotion dan repost
❤️በሶስት ቀን ውስጥ ፍቅር ለማስያዝ የሚጠቅሙ ስነልቦናዊ ወሬዎች❤️

❤️የፍቅረኛዎን ዘፈን ለመጋበዝ ይፈልጋሉ
ዝም ብለው  join  ይጫኑ❤️

❤️የፍቅር አጋርዎን ለማስደሰት ይፈልጋሉ
እንግዲያውስ join የሚለውን ተጫኑት

https://t.me/+PTClkgVZ-MI2MDc0
https://t.me/+PTClkgVZ-MI2MDc0


Zemen Promotion dan repost
🎬🍿 ፊልም የሚመቻችሁ ከሆነ አሁኑኑ JOIN አርጋቸው እነዚህ ቻናሎች ምርጥ ምርጥ የጦርነት እና የጫካ የአክሽን ፊልሞችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያሉ መርጣችሁ ተቀላቀሉ ⬇️

☑️ 𝑺𝒑𝒐𝒏𝒔𝒐𝒓𝒆𝒅 𝒃𝒚: LOVE & POEM


ዋሽንግተኒያን መፅሄት በባለፈው እትሙ ‹‹አንድ ሳምንት የዘለቀው ድንቅ ሠርግ›› በሚል አንድ ዘገባ አቅርቧል፡፡ እንደዘገባው ኤለን የጥርስ ሀኪም የሆነ ህንዳዊ ነው፡፡ አሜት ደግሞ በቨርጂኒያ ነዋሪ የሆነችና የአይቲ ኢንጂነር የሆነች ኤርትራዊት ናት፡፡

✅ የሁለቱም የጋራ ጓደኛ የሆነ ልደት በዋሽንግተን ዲሲ በሚከበርበት ወቅት ትውውቃቸው መጀመሩን አስረድቷል፡፡ ከዚያም በጆርጅ ታውን ራት ተቀጣጥረው ከተገናኙ በኋላ ግንኙነታቸውን ማጠናከራቸውን ገልጿል፡፡ ይህ ከሆነ ከአምስት አመት በኋላ በአሊንግተን ውስጥ ኤለን ተንበርክኮ ታገቢኛለሽ የሚል ጥያቄ ሊያቀርባለት ችሏል፡፡ ጥያቄው ተቀባይነት ካገኘ በኋላ ሁለቱ ጥንዶች ስለሰርጋቸው ማሰብና ማቀድ ይጀምራሉ፡፡ ውጥናቸው ተሳክቶም አንድ ሳምንት የፈጀ ልዩና ድንቅ ሠርግ ለማድረግ እንደቻሉ ዘገባው አስረድቷል፡፡

✅ ይህ ሠርግ አንድ ሳምንት ሊዘልቅ የቻለው የህንድና የኤርትራ ባህል በሙሉ መካተት ስለነበረበት ነው፡፡ በመሆኑም ከህንድና ከኤርትራ ድምፃዊያን ተጠርተውና ዘመድ ወዳጆቻቸው ተገኝተው የሠርግ ስነስርአቱ ሊከናወን እንደቻለ ዘገባው አስታውቋል፡፡ ጥንዶቹ ለሳምንት በዘለቀለው በዚህ ሠርግ ደስታቸውን ካጣጣሙ በኋላ ከድካማቸው ለማረፍና ለጫጉላ ሽርሽር ወደኢንዶኔዥያ ባሊ ሄደዋል ብሏል ዘገባው
፡፡


እባብ🐍 በህይወት እያለ ጉንዳንን🐜 ይበላል፡፡ እባብ ሲሞት ጉንዳኖች ይበሉታል፡፡ ጊዜ በማንኛውም ሰዓት⏰ ይለወጣል በህይወትህ የማንንም ዋጋ አታሳንስ ምን አልባት አንተ ሀይለኛ ትሆን ይሆናል ጊዜ ግን ካንተ የበለጠ ጉልበተኛ ነው አስብ አንድ ዛፍ መቶ ሺ ክብሪቶችን ሲሰራ አንድ ክብሪት ግን መቶ ሺ ዛፎችን ታቃጥላለች፡፡አንድ መጥፎ ስራም ብዙ #መልካምነገሮችን ታጠፋለች፡፡ ወናው ነገር በአስተሳሰብ መልካም ሁን ረጋ ብለህ አስብ ለሁሉም ጊዜ አለው #አትጨነቅ
             
              🌤 መልካም
ቀን⛅️


የአሳ ነባሪን የልብ ምት ከ 3ኪሜ ርቀት መስማት ይቻላል ።


Lifestyle
አንዱ ኪሎ ከ1,800 የአሜሪካን ዶላር በላይ የሚሸጠውን የሻይ ቅጠል ጣእም ለማወቅ ፡ ኒታ አምባኒን መሆን ያስፈልጋል ።

Silver tips Imperial የሚባለው ይህ አንደኛ ደረጃ የሻይ ቅጠል በህንድ ከምትገኘው Darjeeling ግዛት ከሚገኙ ኮረብታማ ስፍራዎች ላይ ይበቅላል ። እናም ምርቱ ሲደርስ ፡ ይህን የሻይ ቅጠል በመልቀም ሙያ በሰለጠኑ ባለሙያዎች ፡ የምሽቷ ጨረቃ ሙሉ በሆነችበት እለት ብቻ በጥንቃቄ ተለቅሞ ። በንፅህና ተጠብቆና ታሽጎ ፡ በህንድና ከህንድ ውጭ ላሉ ባለሃብቶች በአድራሻቸው ይላካል ። በጥቂት መጠንም ፡ ለመደብሮች ይከፋፈላል ።
..............
የኒታ አምባኒ ብሩህ ቀን የሚጀምረው ይህን ውድ ሻይ በመጠጣት ነው ። አስገራሚ ቀለም እና ማራኪ አሮማ ያለው ይህ የሻይ ቅጠል ፡ ጣእሙን የቀመሱ ሰወች እንደሚሉት የማንጎና የfrangipani አይነት የሚመስል ውስብስብ እና ቀምሶ ለማጣጣም እንጂ ለመግለፅ የሚያስቸግር የሚማርክ ጣእም አለው ።
................

ዛሬ በዚህ ፅሁፍ አብረን የምንቆየው ከህንዳዊቷን ቢሊየነር ከወ/ሮ ኒታ አምባኒ ጋር ነው ። እናም እሷ ፡ ጨረቃ ሙሉ በሆነበት ምሽት ብቻ የሚለቀመውን ውዱን እና ውስብስብ ጣእም ያለውን ሻይ ጠጥታ እስክትጨርስ እኛ መልበሻ ክፍሏ፡እንገባና ቅንጦት የሚባለውን ነገር ፡ ከነነብሱ እያየን እንቆያለን ።
.............................

በዚህ የወ/ሮ ኒታ አምባኒ መልበሻ ክፍል ውስጥ ከሚገኙት በሺህ የሚቆጠሩ አልባሳት መሀከል ፡ በጊነስ መፅሀፍ የተመዘገበው ፡ የአለም ውዱ ሳሪ ( የህንድ ባህላዊ ቀሚስ ) ይገኝበታል ፡ ይህ ባህላዊ ቀሚስ ፡ እጅግ ጥራት ባለው ሀር የተሰራ ሲሆን ፡ ዲዛይን ለማድረግ ፡ በሴት አልባሳት ዲዛይነርነት የታወቁ ፡ 25 ሴት ዲዛይነሮች ተሳትፈውበታል ፡ ከዚህ ቀሚስ ጀርባ ያለውን የክሪሽና ምስል የተሳለውም በህንድ እጅግ ታዋቂ በሆነ ዲዛይነር ነው ።
የዚህ ልብስ ጥለቶች የተሰሩት ፡ እጅግ ስስ እና ጠንካራ በሆኑ ፡ ከንፁህ ወርቅ እና ከንጹህ ብር በተሰሩ ቀጫጭን ክሮች የተሸመነ ሲሆን ፡ እንደፈርጥ ሆነው የሚያብረቀርቁት ደግሞ ፡ ሩቢ ፡ ኤመራልድ እና የአልማዝ ነጠብጣቦች ናቸው ። ይህን በአለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ የሰፈረውን ውድ ልብስ በዋናነት አነሳን እንጂ ፡ የወይዘሮዋ አልባሳት ፡ በተለይ የህንድ ባህላዊ አልባሳቶቹ ፡ ባብዛኛው በወርቅ ክሮች የተጌጡ ናቸው ።
...........
በነገራችን ላይ የኒታ አምባኒ አልባሳትን ያህል ባይሆንም በህንድ ውስጥ ከወርቅ ክር ልብሶችን መሸመን ፡ ሺህ ዘመናትን ያስቆጠረ የልብስ መስሪያ አንድ አካል ነው
............................
..............

በሂማልያ ብቻ ከሚገኝ የሚያምር ቆዳ ያለው አዞ የሚሰሩት ቦርሳዎች ።
.......

ሄርሜስ ፡ ዋና መደብሩ በፈረንሳይ ሀገር የሚገኝ ፡ የቅንጦት መደብር ነው ። በ1830ዎቹ የተቋቋመው ይህ ካምፓኒ ትኩረቱን በአብዛኛው ከቆዳ በሚሰሩ የሴት ቦርሳዎችና ተያያዥ የሆኑ ቁሶችን በማምረት የሚታወቅ ሲሆን ፡ ታርጌት አድርጎ የሚሰራው ከፍተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ነው ። እናም በዚህ ካምፓኒ ከሚሰሩት የቅንጦት ቦርሳዎች መሀከል በሂማልያ ከሚገኝ የአዞ ቆዳ የሚሰራው ቦርሳ ነው ።

እነዚህን ሄርሜስ ካምፓኒ ደረቱን ነፍቶ እስከ 150 ሺህ የአሜሪካን ዶላር የሚሸጣቸውን ቦርሳዎች የሚገዙት እጅግ ጥቂት የሆኑ ሰወች ሲሆኑ ፡ ከነዚህ መሀከል ወ/ኒታ አንዷ ናት ። ስለሆነም በመልበሻ ክፍሏ ውስጥ ለቁጥር የሚያዳግቱ በሂማልያ የአዞ ቆዳ ፡ በአንድ ባለሙያ ብቻ ማሽን ሳይነካቸው ፡ በእጅ ብቻ የተሰሩ ቦርሳዎችን ማየት ወይም የአለማችን ቁጥር አንድ የጫማ ዲዛይነር የሆነው የጂሚ ቾ ምርቶች የሆኑ hand made ጫማዎችን ማየት የሚገርም አይደለም ።
.................

ሌላው አስገራሚ ነገር የኒታ አምባኒ ሊፒስቲክ ነው ። ኒታ ፡ የሊፒስቲክ አድናቂ ናት ፡ የሊፒስቲክ ስብስቦቿ በመቶሺዎች ዶላር የሚገመቱ ሲሆን ፡ አንድም ሊፒስቲክ የላስቲክ ወይም የብረት መያዣ የለውም ፡ ሁሉም ሊፒስቲኮች የተሰሩት ወይ ከወርቅ ነው ፡ ካልሆነም እጅግ ጥራት ካለው ንፁህ ብር የተሰሩ ናቸው ።
..............
የማይኮፈስ ስብእና ባለቤት

በህንድ ውስጥ ፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ፡ በአለም ካሉት ቢሊየነሮች መሀከል ዋንኛ የሆነው ፡ የሙኬሽ አምባኒ ባለቤት የሆነችው ኒታ አምባኒ ፡ ህይወት ለሷ እንዲህ ናት ፡ የምትኖርበት ቤት በድፍን አለማችን ተወዳዳሪ የለውም ሆኖም ይህን መሰል እጅግ የቅንጦት ህይወት ውስጥ የምትኖር ሴት ብትሆንም ፡ ልክ እንደ ቢሊየነሩ ባለቤቷ ፡ እሷም እጅግ ተግባቢ ፡ አዛኝ እና ትሁት ወይም down to earth person የሚሏት አይነት ሴት ነች ። በዚህ ተወዳዳሪ በሌለው መኖሪያ ቤቷ ውስጥ የሚያገለግሉ ፡ በመቶ የሚቆጠሩ ሰራተኞች ያሉ ሲሆን ሁሉም ፡ እሷን ማዳም ባለቤቷን ደግሞ ሚስተር አምባኒ ብለው መጥራት አይችሉም ። ይህ የቤቱ ህግ ነው ፡ ሁሉም ሰራተኞች ፡ ባልየው ወንድሜ እሷን ደግሞ እህቴ በማለት በወንድምና በቤተሰብ ስሜት እንዲጠሩ እንጂ ፡ ቅጥ ባጣ አክብሮት እንዲያሳዩ አይጠበቅባቸውም ።
..................

እነዚህ ባልና ሚስቶች ቀኑን በሙሉ በየተከፋፈሉት የስራ መስክ ቢዚ ሆነው ስለሚውሉ ፡ የምሳ ሰአታቸውን በአብዛኛው አብሮ ለማሳለፍ አይችሉም ፡ ነገር ግን በእራት ሰአት ላይ ኒታ አምባኒ ቀድማ ብትገባ እንኳን ባለቤቷ ሳይመጣ ፈፅሞ ራት አትበላም ። በስራ ምክንያት ቢያመሽም እስኪመጣ ትጠብቀዋለች ። እናም እንደመጣ ከአለም ዙሪያ የተሰበሰቡ ቅጠላ ቅጠል የሚበዛባቸውን ምርጥ ምግቦችን እየተመገቡ የቀን ውሏቸውን ያወራሉ ። እርሱም ለሚስቱ ያለው ፍቅር ልዩ ከመሆኑ የተነሳ የልደት በአሏን ሰርፕራይዝ የሚያደርጋት በልዩ ሁኔታ ፈርኒሽድ የተደረገ የግል ጄት በመስጠት ነው ።
............

ኒታ አምባኒ በአለም ላይ ውስን ቁጥር ያለውን Audi A9 chameleon ን ጨምሮ በልዩ ትእዛዝ የተሰሩ መርሰዲሶችና ውድ መኪኖች ቢኖሯትም አንዳንዴ ነሸጥ ሲያደርጋት በተለይ ልጆቿ ታዳጊ በነበሩበት ወቅት ፡ በህዝብ አውቶብስ ወደ ትምህርት ቤት ይዛቸው ትሄድ ነበር ። በሀብት በተከለለ አለም ውስጥ ብቻ ተከልለው መኖር የለባቸውም ፡ የህብረተሰቡ አካል በመሆናቸው ፡ ኑሮውን በቅርብ ማወቅ አለባቸው የሚል መርህ አላት ።
.............

ህይወቷን በዚህ አይነት መልኩ የምትመራው ኒታ አምባኒ ፡ እና ቤተሰቧ ሰርተው ያገኙትን ገንዘብ ከግል መጠቀሚያ ባለፈ ፡ በበጎ አድራጎት ስራዎችም በህንድ ውስጥ የሚስተካከላቸው የለም ፡ በዚህም በ2020 የአለም አቀፍ የበጎ አድራጊ ግለሰቦች ሽልማትን አግኝታለች ። የኮቪድ ወረርሽኝ በተከሰተ ጊዜ በህንድ ውስጥ የመጀመሪያውን የኮቪድ ማገገሚያ ትልቅ ሆስፒታል ያሰራውም ይሄ ቤተሰብ ነው


በዋሲሁን ተስፋዬ


ዓለምን እያነጋገረ ያለው ፎቶግራፍ
--------
በሀገረ ሊባኖስ፣ ቤይሩት ከተማ በሚገኝ አንድ ሰፈር ውስጥ ነው። በፎቶው ላይ የምትመለከቱት የአስር ዓመት ሶሪያዊ ልጅ ሑሴን ይባላል። ሑሴን ቆሻሻ ከሚጠራቀምባቸው ገንዳዎች እየሄደ ሰዎች ተጠቅመውባቸው የጠሏቸውን የፕላስቲክ ኮዳዎች በመሰብሰብ በትንንሽ ሳንቲም የመሸጥ ልማድ አለው። ባለፈው ሰኞ ቀን ይህንኑ ሊፈጽም ሄዶ ሳለ ግን በገንዳው ውስጥ መጽሐፍ ያገኛል። እርሱም ኮዳዎችን መፈለጉን ትቶ መጽሐፉን እያገላበጠ ማየትና መፈተሽ ጀመረ።
ሶሪያዊው ልጅ ይህንን ሲያደርግ "ሮድሪግ ማግሐሚዝ" የሚባል ኢንጂነር ከቢሮው ሆኖ በርቀት አየው። በሁኔታው ስለተገረመ ከቢሮው ወጥቶ በመምጣት ሑሴንን ፎቶግራፍ አነሳው። ከዚያም ተጠግቶት "ምን እያደረግክ ነው?" በማለት ጠየቀው።
ሶሪያው ሑሴንም "ለህፃናት የሚሆን መጽሐፍ መሆኑን እየፈተሽኩ ነው" አለ
"ለትልቅ ሰው የተዘጋጀ መጽሐፍ ከሆነ ጥለኸው ትሄዳለህ?" ሲል ደግሞ ጠየቀው
"አልጥለውም። ወስጄው ለታላላቆቼ እሰጣለሁ። የትልቅ ሰው መጽሐፍ ቢሆንም መጣል የለበትም። እንዴት መጽሐፍን የመሰለ ነገር ከቆሻሻ ጋር ይጣላል?"
"መጽሐፍ ማንበብ ትወዳለህ ማለት ነው?"
"በጣም እወዳለሁ"
"ትማራለህ?"
"እማር ነበር። በችግር ምክንያት አቋርጫለሁ"
ኢንጂነር ሮድሪግ ሶሪያዊው ህፃን ሑሴን መጽሐፉን የሚያነብበትን ተመስጦ ሲያስረዳ "በመጽሐፉ ውስጥ ለእርሱ የተዘጋጀለትን ልዩ ቦታ የሚፈልግ ነበር የሚመስለው" በማለት ነው የገለጸው።
---------
ሊባኖሳዊው ኢንጂነር የሶሪያዊውን ልጅ ፎቶ በካሜራው ቀርጾት በዚያው ዝም አላለም። በቲውተር፣ በፌስቡክ እና በሌሎች የሶሻል ሚዲያ ፕላትፎርሞች ላይ በመለጠፍ ለጓደኞቹ አጋርቷል። ፎቶው በአጭር ጊዜ ውስጥ ከዐረቡ ዓለም እና ከምዕራባዊያን ሚዲያዎች እና የሶሻል ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ በመድረስ መነጋገሪያ ሆኗል።
በአሁኑ ወቅትም በቤይሩት የሚገኙ ታዋቂ ትምህርት ቤቶች ህጻን ሑሴንን ተቀብለውት በነፃ ሊያስተምሩት እየጠየቁት ነው። በርካታ ባለሀብቶችም እርሱና ወላጆቹ የተሻለ
ኑሮ እንዲኖሩ ለማስቻል እና በሊባኖስ የሚኖሩ የሶሪያ ስደተኞችን ህይወት ለመለወጥ ቃል ገብተዋል። የሊባኖስ መንግሥትም ለህፃን ሑሴን ሙሉ ዜግነት ለመስጠት ወስኗል።
---------
ጭብጥ....ሶሻል ሚዲያ በትክክል ከተጠቀሙበት ብዙ አዎንታዊ ለውጦችን ሊያመጣ የሚችል ትልቅ መሳሪያ ነው።
-------
(ምንጮች፣ የአህላም ሙስተጋነሚ ፌስቡክ ገጽ፣ አል-ጀዚራ፣ አል-ዐረቢያ፣ Middle East Eye
)
------


እግር ጥሏችሁ ጃፓን ቶኪዮ ከተማ ብትደርሱ የዚህን ውሻ ሀውልት በአንድ ባቡር ጣቢያ ውስጥ ታገኙታላችሁ፡፡ ይህ ውሻ ለ10 አመታት ፍቅርን የሰበከ ታማኝነትን ያወጀ በመሆኑ ጃፓናውያን ይኮሩበታል ይወዱታል፡፡ በነገራችን ላይ የዚህ ውሻ ታሪክ ፊልም ሆኖ ተሰርቷል፡፡ "Hachi: a dogs tale" በ2009 የተሰራው ፊልም ነው።

ይህ ውሻ ስሙ ሀቺኮ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን የፕሮፌሰር ኢዛቡሮን ውሻ ነበር፡፡ ፕሮፌሰሩ ውሻውን በፍቅር አሳደጉት፡፡ ሁሌም ውሻው ጠዋት አብሮ ባቡር ጣቢያ ሄዶ ፕሮፌሰሩን ሸኝቶ ይመለሳል ማታ 11 ሰዓት ባቡር ጣቢያ ሄዶ ይቀበለውና ቤት ድረስ አብሮ ይመጣል፡፡

ታድያ ከእለታት ሁሉ በአንዱ ከፉ ቀን በግንቦት 21 - 1923 ዓ.ም ውሻው ፕሮፌሰሩን ሸኝቶ ማታ እንደልማዱ ሊቀበላቸው ባቡር ጣቢያ ቢጠብቃቸው ሰውዬው ለካ በልብ ድካም ሞተው ኖሯል ሳይመጡ ቀሩ፡፡

ውሻው ግን ይመጣሉ ብሎ ፕሮፌሰሩን ጠበቀ 1 ቀን ብቻ አደለም ጥቂት ወራትም አደለም ድፍን 10 አመት እንጂ እሳቸውን ጥበቃ እዛችው ባቡር ጣቢያው ጋር 10 አመት ጠብቆ እዛው ሞተ፡፡ እናም ሀቺኮ ወዳጁን 10 አመት በፅናት መጠበቁ አያስደንቅም
?


በዙምባቤው ምድር እንዲህ ሆነ…የሀገሪትዋ መሪ ጋብሬል ሮበርት ሙጋቤ ሀገራዊ ምርጫ ቢደርስም እስከመጨረሻዋ ቀን ድረስ ምንም ቅስቀሳ አላደረጉም ነበር። ለተቀናቃኛቸው ስልጣኑን አሳልፈው ሊሰጡ መስሏቸው የዙምባቤ ህዝብ በግምቱ ተደሰተ።

በምርጫው ዋዜማ እለት ግን "ሙጋቤ ንግግር ሊያደርጉ ነው ሁላችሁም በስታዲየም ተገኝታችሁ ንግግራቸውን መስማት ትችላላቹ"ተባለና ህዝቡ ስታዲየሙን አጥለቀለቀው።ስልጣን የሚያስረክቡ መስሎዋቸው በሀሳባቸው ለማን ይሰጡ ይሆን? እያሉ ስታዲየሙን ከአፍ እስከ ገደፉሞሉት።

ከአፍታ ቆይታ በኋላ ሙጋቤ ከስታዲየሙ ደረሱ።መርፌ ቢወድቅ ይሰማል።ንግግራቸውን ለመስማት ስታዲየሙ ፀጥ ረጭ አለ።"የዙምባቤ ህዝብ ሆይ…!እኔን ልትሰማ እዚህ ድረስ በመምጣትህ አመሰግናለው"ብለው ንግግራቸውን ጀመሩ።

"ቅድሚያ በመጀመሪያ ስትመርጠኝ ።

ለሁለተኛ ግዜ ስትመርጠኝ ከበሩ።

እንግዲ እኔም ከብሬያለው ፤ቤተሰብ ዘመድ አዝማዶቼንም እንዲከብሩ አድርጌያለው...

ነገ በሚደረገው ምርጫ ለ ሶስተኛ ግዜ ከመረጥከኝ ግን ለህዝብ ነው የምሰራው።ለናንተ ነው የምሰራው።ይህግልፅ ነው……

ነገር ግን ሌላን ሰው ብትመርጡ ግን መጀመሪያ ለራሱ ይሰራል።ይከብራል።ከዚያም ለሁለተኛ ግዜ እድል ከሰጠኸው ለዘመድ አዝማዶቹ ይሰራል።ለህዝቡ የሚሰራው ለሶስተኛ ግዜ ከመረጥከው ነው…

ታዲያ በዚህ ወቅት እናንተን ለማገልገል የሚቀርበው ማን ነው?……እኔ ነኝ። ስሜም ለሶስተኛ ግዜ የምመረጠው ጋብሬል ሮበርት ሙጋቤ እባላለው……ጨርሻለው።ነገ በምርጫ ወቅት እንገናኝ"ብለው ንግግራቸውን አበቁ...

የዙምባቤ ህዝብ ለሊቱን በጭንቀት ያለ እንቅልፍ አሳለፈ።በነጋታውም ራሳቸው ተመረጡ። ምርጫ ማጭበርበር ኮሮጆ መገልበጥ ብቻ አይደለም…አሳምኖ ድምፅን መዝረፍም ነው
😍


✍ ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ስእል በአውሮፓ በተካሄደ ጨረታ በ46.8 ሚልየን የአሜሪካን ዶላር ለአንድ ባለ ሀብት ተሽጧል
     


አሊባባ በኢትዮጵያ በብር ክፍያ ከነገ ጀምሮ መቀበል ሊጀም መሆኑን አሳወቀ

አለም አቀፉ ግዙፍ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ተቋም አሊባባ፣ ከሰኞ የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ በብር ክፍያ መቀበል እንደሚጀመር አሳዉቋል።

ይህ እርምጃ ኢትዮጵያውያን በአሊ ኤክስፕረስ ላይ በቀላሉና በአገር ውስጥ ገንዘባቸው እንዲገበያዩ ያስችላቸዋል።

አሊባባ ይህን ውሳኔ የወሰነው ለአፍሪካ ተጠቃሚዎች ይበልጥ ተደራሽ ለመሆንና በዓለም አቀፍ የክሬዲት ካርዶችና የውጭ ምንዛሬ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ በማሰብ ነው ተብሏል። ይህ እርምጃ በአለም አቀፍ የክፍያ ስርዓት ምክንያት ለአፍሪካውያን ትልቅ እንቅፋት የነበረውን ችግር ለመቅረፍ ያለመ መሆኑም ተሰምቷል።

ይህም ማለት አሁን ኢትዮጵያውያን በአሊ ኤክስፕረስ ላይ የተለያዩ እቃዎችን ሲገዙ በብር ገንዘባቸው ክፍያ መፈጸም ይችላሉ። አሊባባ ይህን ለማሳካት በኢትዮጵያ ካሉ የዲጂታል ክፍያ አገልግሎት ሰጪዎች ጋር ትብብር መፍጠሩን አስታውቋል


Via CapitalNews


🏛ማታ ከመተኛታችን በፊት 1 የብርጭቆ ውሃ እና ጠዋት ከመኝታ ከተነሳን በኋላ ግማሽ ብርጭቆ ውሃ መጠጣት በህልም ያየነውን ነገሮች ሙሉ በሙሉ እንድናስታውስ ይረዳናል።

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.