ዓለምን እያነጋገረ ያለው ፎቶግራፍ
--------
በሀገረ ሊባኖስ፣ ቤይሩት ከተማ በሚገኝ አንድ ሰፈር ውስጥ ነው። በፎቶው ላይ የምትመለከቱት የአስር ዓመት ሶሪያዊ ልጅ ሑሴን ይባላል። ሑሴን ቆሻሻ ከሚጠራቀምባቸው ገንዳዎች እየሄደ ሰዎች ተጠቅመውባቸው የጠሏቸውን የፕላስቲክ ኮዳዎች በመሰብሰብ በትንንሽ ሳንቲም የመሸጥ ልማድ አለው። ባለፈው ሰኞ ቀን ይህንኑ ሊፈጽም ሄዶ ሳለ ግን በገንዳው ውስጥ መጽሐፍ ያገኛል። እርሱም ኮዳዎችን መፈለጉን ትቶ መጽሐፉን እያገላበጠ ማየትና መፈተሽ ጀመረ።
ሶሪያዊው ልጅ ይህንን ሲያደርግ "ሮድሪግ ማግሐሚዝ" የሚባል ኢንጂነር ከቢሮው ሆኖ በርቀት አየው። በሁኔታው ስለተገረመ ከቢሮው ወጥቶ በመምጣት ሑሴንን ፎቶግራፍ አነሳው። ከዚያም ተጠግቶት "ምን እያደረግክ ነው?" በማለት ጠየቀው።
ሶሪያው ሑሴንም "ለህፃናት የሚሆን መጽሐፍ መሆኑን እየፈተሽኩ ነው" አለ
"ለትልቅ ሰው የተዘጋጀ መጽሐፍ ከሆነ ጥለኸው ትሄዳለህ?" ሲል ደግሞ ጠየቀው
"አልጥለውም። ወስጄው ለታላላቆቼ እሰጣለሁ። የትልቅ ሰው መጽሐፍ ቢሆንም መጣል የለበትም። እንዴት መጽሐፍን የመሰለ ነገር ከቆሻሻ ጋር ይጣላል?"
"መጽሐፍ ማንበብ ትወዳለህ ማለት ነው?"
"በጣም እወዳለሁ"
"ትማራለህ?"
"እማር ነበር። በችግር ምክንያት አቋርጫለሁ"
ኢንጂነር ሮድሪግ ሶሪያዊው ህፃን ሑሴን መጽሐፉን የሚያነብበትን ተመስጦ ሲያስረዳ "በመጽሐፉ ውስጥ ለእርሱ የተዘጋጀለትን ልዩ ቦታ የሚፈልግ ነበር የሚመስለው" በማለት ነው የገለጸው።
---------
ሊባኖሳዊው ኢንጂነር የሶሪያዊውን ልጅ ፎቶ በካሜራው ቀርጾት በዚያው ዝም አላለም። በቲውተር፣ በፌስቡክ እና በሌሎች የሶሻል ሚዲያ ፕላትፎርሞች ላይ በመለጠፍ ለጓደኞቹ አጋርቷል። ፎቶው በአጭር ጊዜ ውስጥ ከዐረቡ ዓለም እና ከምዕራባዊያን ሚዲያዎች እና የሶሻል ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ በመድረስ መነጋገሪያ ሆኗል።
በአሁኑ ወቅትም በቤይሩት የሚገኙ ታዋቂ ትምህርት ቤቶች ህጻን ሑሴንን ተቀብለውት በነፃ ሊያስተምሩት እየጠየቁት ነው። በርካታ ባለሀብቶችም እርሱና ወላጆቹ የተሻለ
ኑሮ እንዲኖሩ ለማስቻል እና በሊባኖስ የሚኖሩ የሶሪያ ስደተኞችን ህይወት ለመለወጥ ቃል ገብተዋል። የሊባኖስ መንግሥትም ለህፃን ሑሴን ሙሉ ዜግነት ለመስጠት ወስኗል።
---------
ጭብጥ....ሶሻል ሚዲያ በትክክል ከተጠቀሙበት ብዙ አዎንታዊ ለውጦችን ሊያመጣ የሚችል ትልቅ መሳሪያ ነው።
-------
(ምንጮች፣ የአህላም ሙስተጋነሚ ፌስቡክ ገጽ፣ አል-ጀዚራ፣ አል-ዐረቢያ፣ Middle East Eye )
------