ግጥም በ ኤዶምገነት


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: San’at


ግጥም ብቻ ቤተሰብ ይሁኑ።
የቻናላችንን የመወያያ ግሩፕ ለማግኘት
https://t.me/slegtmenawga
tiktok.com/@edom_ge
ኤዶምገነት @Edom_Ge

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri




#ለምን_ግን_ፈጣሪ...?

ምድርን ባጀብ ሞላት ለዱር ለገደሉ አበባን ፈጠረ፣
ጥበቡን ለማወቅ ለኛኮ አንተን ማዬት ይበቃን ነበረ።

በሰው እንዲወደድ ሁሉን እንዲያስማማ፣
ሀሳብን እንዲሰርቅ ቀልብን እንዲቀማ፣
ሸፋች ብኩን ዐይን እንዲልብህ ሰከን፣
የሰራ አካልህን ፈጥሮታል ያለ እንከን።

ሞገስ የታደለ ትከሻህ የኮራ፣
ወንዳወንድነትህ ከሩቅ የሚያስፈራ፣
በጎ ምግባሮችህ ወላድ የሚያስመኩ፣
እንዳንተ አላየሁም የተጣጣሙለት ፀባይ እና መልኩ።

ደምግባትህ ሙሉ ወዝ ወዘናህ መልካም፣
ፈገግታህ ብቻውን ያሳርፍ የለም ወይ ካለም ከንቱ ድካም?

አንደበትህ ጨዋው ዝም ብሎ ያልፋል፣
መልክህ ባለጌ ነው ሁሉን ይላከፋል።
ስንት የሄዋን ዘሮች በጎንህ ያለፉ፣
አቅላቸውን ጥለው ባንተ ፀዳል ጠፉ?

ብርሀን የተሞሉ ድምቀት የለበሱ፣
የሂወትን ፅልመት ታይተው የሚያስረሱ፣
የተሰበረን ልብ ባንዴ 'ሚፈውሱ፣
ድንቅ ግሩም አይኖች አድሎሀል እሱ።

እናታዲያ ለምን...? ለክብሩ መለኪያ ጨረቃን ፈጠረ ኮከብን ፈጠረ፣
እኛኮ አንተን አይተን በእጆቹ ፀጋ ተገርመን ነበረ ተደንቀን ነበረ።

ለምን...?

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha






🇪🇹
.
አድዋ ዛሬናት፡ አድዋ ትናንት፣
መቼ ተነሱና፡ የወዳደቁት!!
.
.
#ጂጂ
💚💚💚💛💛💛❤️❤️❤️

@arifgtmbcha


.
አየሁ ሚዛን ደፍታ
ትንሿ ደግነት
ከብዙ በደሌ፣
ድሮም አውቀዋለው
ድንግልን ስጠጋ
ቀና ነው እድሌ!!

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha


#ፈራሁ

ብዙ ዛሬ እያለፈኝ
  ቀኑ ነግቶ እስኪጨልም፣
በውል ቀኑን ሳልረዳ
  ፊቱን ብቻ ነገን ሳልም፣

ከህልም ላይ ህልም ጭኜ
  ደራርቤ ሳንቀላፋ፣
ከፍራሼ ሳልነሳ
  አለም ቀድማኝ እንዳጠፋ!!

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbch


#አንድ_ሚስጥር_ላውጋህ
.
እንደንጹህ አየር ፡ እንደረጋ ንፋስ፣
ሁነኸኛል እና ፡ ለመኖሬ እስትንፋስ፣

ከጎኔ ስትሆን..
ሊቆምያለው ልቤ ፡ ያለቅጥ ይመታል፣
በድን ሰውነቴ ፡ ነብስ ይዘራበታል!!

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbch

1.1k 0 10 18 33

*
ስንቱ ቀን መሼብኝ
  ስንዴ አገኘሁ ብዬ
    እንክርዳድ ስለቅም፣
ልክ ይመስላል እንጂ
  አንዳንዱ ስህተት
    ለካ አያስታውቅም።

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha


#ለምን_በሌት_ብቻ
.
ቀኑንም ጨምሬ
አንተኑ ለማለም፣
ምነው ቀሪ እድሜዬን
በተኛሁ ዘላለም!

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha


***
"እኔ ሳድን የሷን ጥላ፣
ሄደች ሌላ ተከትላ።"

ብሎ አዎራ ከጄርባዬ
  አንሾካሽኮ እንደፈሪ
    ሀሜት ቢጤ ደራርቦበት፣
አሳምኖ ከወሰደኝ
  እንቅፋቴን እያነሳ
    ብከተለው ምን አለበት?

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha


#የአባት_ሀዘን

ሙላቴ ጎሏል በሀዘን
ፍካቴ ፀልሟል ባባ፣
ግማሹን የእኔ አካል
ይዞት ከጉድጓድ ገባ፤

ፈጣሪ ፈቅዶ እንደልጅ
ተንከባክቤ ሳልጦረው፣
የምድርን ትቢያ አልብሶ
እንዳይመለስ አስቀረው፤

ጎደልኩኝ መቼም ላልካስ
እወደው ነበረ በጣም፣
እህህ.. ማለቴም ከንቱ
ሀዘኔ መቼም አይወጣም፤

አቃተኝ እውነቱን ማመን
ውል አለኝ ሳቁ እና ድምፁ፣
ፈለኩት በሰዎች መሀል
ናፈቀኝ ኮስታራው ገፁ፤

በእንባ ቢታጠብ ገላዬ
ሁለመናዬ የሱ አምሳል፣
ለቅሶስ በምን ስልጣኑ
ያባትን ሀዘን ያስረሳል?

መፅናናት በምን ይቻለኝ
ልጠንክር እንዴት አባቴ፣
ስረታ የሚያጎብዘኝ
እርሱኮ ነበር ብርታቴ።

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha

3k 1 16 8 30

ያቺን ቀን....
ምነው በሰረዛት
  ከህይዎቴ መዝገብ፣
ተገብቶሽ አይደለም
  ዘለፋ እና ስድብ፣
ተደፍቼ ላልቅስ
  ከደጀሰላሙ፣
መቅለሌን ባየና
  በሰጠልኝ ላንቺ
    የይቅርታ ልቡን።

ይህቀረን የምለው
  እንደሌለ አውቃለው፣
ከልቤ ነው ማማ
  መልካሙን መልካሙን
    በሄድሽበት ሁሉ
      እመኝልሻለው፣
ዳግም ከሕይዎትሽ
  ላልገባብሽ ፍፁም
    እምልልሻለው።

#ተፃፈ_በዳዊት
@Davunin


**
ትዝ ይለኛል ያወኩት ቀን
ስለራሱ ብዙ ነግሮኝ
ማነው ስምሽ ያለኝ እለት፣
ከእናት ካባት የወጣልኝ
መጠሪያዬ ጠፋኝ እና
የራሱን ስም ደገምኩለት።

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha

2k 1 10 4 40

#ባቅፈው_ደስ_ይለኛል

ባርፍ ብጠመጠም
ብገባ ከቅፋ፣
ደቂቃዎች ቁመው
ሰአታት ሳይከንፋ፣
ራሴን አስደግፌ
በደረቱ ተርታ፣
ባደምጥ እንደዜማ
የልቡን ትርታ፣

ዝም ብለን ብቻ
ምንም ሳናዎራ፣
አንድ አይነት ስሜትን
አብረን ብንጋራ፣
ክንዱን ተጠልዬ
ናፍቆቴን እንዳልፈው፣
ደስ ይለኝ ነበረ
ሳብ አድርጌ ባቅፈው።

ግን በምን ጀግንነት
በየትኛው ወኔ፣
ስንቱን ሰው አልፌ
አቅፈዋለው እኔ፣
ይሉኝታዬን ሽሬ
ብደርስ እንኳን ከሱ፣
ይመልሰኝ የለ
ያ ግርማ ሞገሱ።

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha

3k 1 42 4 40

#የኔ...

ተከፍቼ ሳዝን እንደ ወንድም፣
በደስታዬ አብሮነት የማትደክም፣
ስትቆጣኝ እንደ አባት ፣
ስትመክረኝ እንደ እህት ፣
የኔ መልካም የፍቅሬ እናት፣
ለኔ ስትል የማቶነው ምንም የላት።

ምን ልበላት...የኔ ፍቅር ማር ጣፋጬ?
ስም ከንቱ... ይጨነቅበት ስም አውጭው፡
እኔግን የእኔ ብያት፣
በአንዲት ውብ ቃል ልቋጭላት።

@Davunin


ድሮ፦
እንደ ንጋት ፀሀይ
እንደ ማታ ጀንበር፣
ሲመጣ እንዳይሄድ
ሲሄድም እንዳይቀር፣
እናፍቀው ነበር።
.
.
ዘንድሮ፦
እንደቀትር ፀሀይ
ልክ እንደሚጠላው፣
ከሱ ለመከለል
አይበቃኝም ጥላው።
.
.
ግን ለምን...
ለምን... ተቀየርኩኝ
አልገባኝም መልሱ፣
የማን ነው ስህተቱ
የእኔ ወይስ የእሱ ? 
 
                      እንጃ...

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha


#አትጥቀሰኝ

ሳይሰነዝር 'ሚጥል
ሳይገል የሚረታ፣
አንዳች ጉልበት አለው
ያይንህ ስልምልምታ።

እንኳንስ ጨክነህ
አርገብግበህብኝ፣
ድሮም እኔ ልጅት
ፍርሃት አለብኝ፣
እኒያ ውብ ዓይኖችህ
ወደኔ ካመሩ፣
ይመስሉኛል ውስጤን
የሚመረምሩ፣
ያስጎነብሱኛል እንደ
ጨረር ግለት፣
አንተን ለመጋፈጥ
ያሳጡኛል ጉልበት።

ታዲያ ለምንድን ነው....
እንደምንም ችዬ
ሆኜ እንደጠንካራ፣
ወዳንተው ለማዬት
በድንገት ሳመራ፣
ተዘጋጂ ሳትል
ወይ ሳታሳውቀኝ፣
በአይኖችህ ጠቅሰህ
ቀልቤን የምትሰርቀኝ?

አስበኸው ይሆን
ወይስ ሳታስበው፣
የእኔን ሁለመና
ወዳንተ ምትስበው?

ደጋግሞ እጅ መስጠት
ባይኖችህ ብለምድም፣
በአንተ አይነት ጩልሌ
መሸነፍ አልፈቅድም፣
አካሌ እንደባዳ ልቀቂኝ እያለ
ሁሌ ከሚወቅሰኝ፣
ልለምንህ በቃ በምትወደው ነገር
ተወኝ አትጥቀሰኝ።

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha


እሺ..

ከዝምታ ቀጣይ : በዚህ በትንሽ ቃል፣
ንዴትም ይለቃል : ንግግርም ያልቃል።

እሺ..
ሀተታ አይፈልግም : አይልም ማመልከቻ፣
ሰከን ብሎ አድምጦ : እሺ ማለት ብቻ፣
ሊነድ ያሰበውን : በእርጋታው ያጠፋል፣
ግሎ የመጣውን : አቀዝቅዞት ያልፋል።

እሺ!

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha

4k 1 29 2 33

እንኳን አደረሰን

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.