በኮሎኔል ታደሰ ህልፈተ ህይወት እጅጉን አዝነናል። ነገር ግን አንድ ነገር ተምረንበትም ታዝበንም አልፈናል።
ዛሬ ስለኮሎኔሉ ህልፈት በፀፀት የሚፅፈው፣ ቁጭቱን የሚገልፀው እና ወዳጄ ነው ባዮ በርከት ብሎ አየነው። ነገር ግን ከዚህ በፊት በጥቂት እኩያን የተጠለፉ ወንድሞችን በጅምላ የአደረጃጀት ፍረጃ ከማራቅ ይልቅ፣ ማቅረቡ ይሻላል ስንል "የተመረዘ ድርጅት ነው፣ ሁሉም አይጠቅሙም" የሚል የግብታዊ አካሄዶችን ተመልክተናል፤ ሃሳቦችም ደርሰውናል። ጭራሽ ውሃና ዘይትም ያለም ነበር። ዋናው ጥያቄ ግን ለአንድነት ቀናዒ የሆኑትን፣ ለአማራ ሕዝብ ፍላጎት ቅድሚያ ሰጠው ግለሰባዊ ፍላጎቶችን ገሸሽ ካደረጉት ጋር መስራቱ ላይ ነው።
ዛሬ ላይ መሰል የህልፈት ዜናዎች ሲሰሙ፣ በየትኛውም ደረጃ ቁጭት ብንሰማ ስላቅ መስሎ የሚሰማ ትርጉም አልባ ነው። መፈራረጁን አቁሞ የአደረጃጀት መስመሮችን ደፍሮ ማለፍ ያስፈልጋል። በአፋህድ በኩል ላሉት የኮሎኔል አሰግድ ጥቅም የገባቸው ገፍተውት ገፍተውት ኮሎኔል ከተያዘ በኋላ ከሆነ፣ በሌላው በኩል ያለው ደግሞ የኮሎኔል ታደሰ ጀግንነትና ቅንነት ትዝ ያላቸው ከህልፈቱ በኋላ ከሆነ… ከዚህ በላይ የግብታዊ አካሄድ ማሳያ የለም። ያልተሰሉ ስሜታዊ አካሄዶችና የጅምላ ፍረጃዎች ለእኛ የወል ውርደትን፣ ለጠላት ደግሞ ጥቂት ጥቂት ተደጋጋሚ ድልን የሚያስገኙ ይሆናሉ።
አሁን ላይ በሁሉም አቅጣጫ የሚያስደምም የፋኖ ሰራዊት ግንባታ ስራዎች እየተሰሩ ነው፤ የፖለቲካና ወታደራዊ ስልጠናው አስደማሚ ነው፤ የከባድ መሳሪያ ትጥቅ ለጉድ ነው። ይህ በሙሉ ለነጋችን ትልቅ ስንቅ ነው። ነገር ግን ማሸነፍ ካለብን ቢያንስ ቢያንስ ከልዮነቶች ይልቅ በሚያግባቡን ነገሮች ላይ በመስራት እንጀምር። አሁን አሁን የምንታዘበው ነገር ቢያንስ እንኳን አንዳንድ አመራሮች የአደረጃጀት ልዮነቶችን ለማጥበብ ንግግር ሲያስቡ እየፈሩ ያለው የስሜት ጋላቢውን ጩኸት ነው። ቢያንስ እንኳን አዋጭውን መንገድ በእራሳቸው አቅደው እንዳይፈፅሙ ስጋት የሆነባቸው፣ እንደቁራ የሚጮኸውን ታርጋ ለጣፊን መንጋ ነው።
በእንዲህ አይነት ሁኔታ ደግሞ ማሸነፍ አይቻልም። ሕዝባችን እንደ ሕዝብ አንድነትን ናፋቂ ነው። ስለዚህ ለሕዝብ ይበጃል ያላችሁን የተሰላ አካሄድ መከተላችሁ፣ ለአንድነትን መትጋታችሁ የሚያስጮኸው የማህበራዊ ሚዲያ መንጋ ካለ… እንደፈለገ ሲያጎራ ይኑር፤ ሲፈልግም በጅምላ ወይም በችርቻሮ ይታነቅ እንጅ ስምን እየፈሩ ወደኋላ የለም። ዛሬም ደግመን እንላለን - አሸናፊ የሚያደርገን "ስሜትን የገራና ከእኔ በላይ እኛ" የሚል አካሄድ ነው። የድል ቀናችንን የሚያቀርበውን አዋጭ መንገድ መርጦ፣ ሕዝባችሁ የሚወደውን ስሩ። ከዛ ግን የጮኸ ቁራ ሁሉ ምን ሊፈጥር? ምንም።
ነፍስህ በሰላም ትተፍ፣ ኮሎኔል!
እንኳን ለአድዋ ክብረበዓል አደረሳችሁ! ምኒልክነት መለያ ክብራችን ነው።