ባህረ ጥበባት


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


"ህዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቷል" ት. ሆሴዕ 4:6
አለማወቅ እያጠፋን ነውና እንወቅ።
ለማንኛውም አስተያየትና ጥያቄ @Filoppader

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


























ለአባ ተክለሐይማኖት
ያለ ማወቅ ጽልመት ሀገሩን ሲወርሰው
ማን ነበር ትውልዱን በወንጌል ያረሰው?
አባ ተክለ ሃይማኖት አባ የትናንቱ
ትዝ አለኝ ተጋድሎው ውል አለኝ ሕይወቱ
በቆላ በደጋ የተንከራተትኸው
የሃይማኖትን ተክል ዞረህ የተከልኸው
የኢትዮጵያ ፀሐይ አባ ተክለ አብ
እስቲ መለስ ብዬ ሥራህን ላስብ
የክህደት ጨለማ በአንተ ሲርቅ
የሃይማኖት ብርሃን ሲያንጸባርቅ
በቀንና ሌሊት ከላይ ታች ዞረህ
ሕዝቡን አደረስከው አስተምረህ መክረህ
ስንት ነበር አባ ‹የጉዞ አበልህ›?
ያረፍህበት ስፍራ የተዘጋጀልህ
የት ነበር መኝታው ጎን ማሳረፊያህ?
ንገረኝ እባክህ ማን ነበር የሸኘህ?
እሳት አባቴ ሆይ እኔ አመድ ልጅህ
በዘመኔ ቋንቋ እስኪ ልጠይቅህ?

እንኳን አደረሳችሁ🙏

ፍንጭ: fb















20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.