አርድእት፣ለ36ቱ ቅዱሳት አንስት ‹‹እስከ ሦስት ቀን እነሣላችኋለሁ እዘኑ አልቅሱ፣ እህል ውኃ አትቅመሱ በሏቸው›› ብሎ ለዮሴፍና ለኒቆዲሞስ አክፍሎት አስተማራቸው፡፡
ዳግመኛም መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከዕርገቱ በኋላ ለቅዱሳን ሐዋርያት የሞቱን መታሰቢያ እንዲያደርጉ ነግሯቸዋልና፡፡ ሕማሙንና ሞቱንም እንዲዘክሩ አዟቸዋልና አሁንም ያንን ሁሉ የመድኃኔዓለምን ሞቱን ያላሰበና የሞቱን መታሰቢያ በዓል ያላከበረና እርሱንም የማይወደው ቢኖር ዕድል ፈንታው ጽዋ ተርታው ከአይሁድ ጋር ነው፡፡
የአምላካችንን የመድኃኔዓለምን ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ተባብረን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ከእርሱ ለመተባበር ያብቃን፡፡
አባቶቻችን በሠሩልን ሥርዓት መሠረት የመጋቢት 27 የመድኃኔዓለም ክርስቶስ የስቅለቱን በዓል ወደ ጥቅምት 27 ቀን መጥቶ እንዲከበር አባቶቻችን ወስነዋል፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ያበሠራትና የጌታችንም ፅንሰት የተከናወነው በመጋቢት ወር በ29ኛው ቀን በዕለተ እሁድ በ3 ሰዓት ነው፣ ነገር ግን ብሥራቱና ፅንሰቱ ግን ታኅሣሥ 22 ቀን እንዲከበር ቅዱሳን አባቶች እነ ቅዱስ ደቅስዮስ ወሰኑ፡፡ እነርሱም በዓሉን በዚሁ ዕለት አክብረውታል፡፡ አንድም ነገረ ልደቱን ከማክበር አስቀድሞ ነገረ ፅንሰቱን ማዘከር ማክበር ተገቢ ስለሆነ ነው፡፡ በዓቢይ ጾም ወቅት ደግሞ ፍጹም ሐዘን ልቅሶ ጾም ጸሎት ይያዛል እንጂ ደስታ ፌሽታ እልልታ ጭብጨባ የለም፡፡ ዓቢይ ጾም ፍጹም የሐዘን ወራት ነው፡፡ ታቦት አውጥቶ በዓል ማክበር ስህተት ነው፤ የአባቶችንም ሥርዓት ማፍረስ ነው፡፡ ምስጋና ይድርሳቸውና ቅዱሳን አባቶቻችን ሁሉንም ነገር በሥርዓት በሥርዓቱ አድርገው ሰፍረው ቆጥረው አስቀምጠውልናል፡፡ ከዓቢይ ጾም በኋላ ያሉትን 50 ቀናት ረቡዕና ዓርብንም ጭምር ሥጋ እንኳን እንድንበላ ነው ሥርዓት የሠሩልን፡፡ አባቶቻችን የሠሯት ሕግ ፍጽምት ናት፡፡ በዚህም መሠረት አባቶቻችን ሥርዓትን ሠሩልንና የመጋቢት 27 የጌታችንን የስቅለቱን በዓል ወደ ጥቅምት 27 ቀን አምጥተው እንዲሁም የመጋቢት 5 የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን የዕረፍት በዓል ወደ ጥቅምት 5 ቀን አዙረው እንዲከበር አድርገዋል፡፡
+++
+ ዳግመኛም በዚህች ዕለት ጥቅምት 27 ቀን ታላቁ አባት አቡነ መብዓ ጽዮን ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ አባ መቃርስ ዘሀገረ ቃው ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ የላመ የጣፈጠ ከመብላት ተቆጥበው ጥሬ እየተመገቡ 9 ዓመት ከቆዩ በኋላ ከአቡነ ገብረ ማርያም ጋር ሆነው የእመቤታችንን ስደት በጥልቀት የሚተርከውን ‹ማኅሌተ ጽጌን› የደረሱት አቡነ ጽጌ ድንግል ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ በንስር አሞራ የተመሰለ መልአክ ትኩስ የሆነ የቅዱሳንን አስክሬን እያመጣ የሚያስቀምጥበትን አርብ ሐራ መስካበ ቅዱሳን መድኃኔዓለም ገዳምን የመሠረቱት ታላቅ ጻድቅ ግብፃዊው አቡነ ሐራ ድንግልም ዕረፍታቸው ነው።
+ + +
አባ መቃርስ ዘሀገረ ቃው፡- ቃው የምትባል ሀገር ኤጲስቆጶስ የሆኑት አባ መቃርስ ሁልጊዜ ወንጌልን በሚያስተምሩበት ወቅት ያለቅሱ ነበር፡፡ ከደቀ መዛሙርቶቻቸውም አንዱ በእግዚአብሔር ስም ካማላቸው በኋላ ለምን ሁልጊዜ እንደሚያለቅሱ በመሐላው አምሎ ጠየቃቸው፡፡ እርሳቸውም ስለመሐላቸው ፈርተው ነገሩት ‹‹ዘይት በብርሌ ውስጥ ጎልቶ እንደሚታይ የወገኖቼም ኃጢአት እንዲሁ በታየኝ ጊዜ አለቅሳለሁ›› አሉት፡፡ በሌላም ጊዜ ጌታችን በመሠዊያው ላይ ሆኖ ተገልጦላቸው የእያንዳንዱን ሰው ኃጢአት መላእክት ሲያቀርቡለት አሳያቸው፡፡ ቀጥሎም ‹‹ሕዝቡን አስተምረህ ከክፋታቸው መልሳቸው›› አላቸው፡፡ እሳቸውም ‹‹አይሰሙኝም›› ቢሉት ጌታችንም ‹‹አስተምረሃቸው ከክፋታቸው ባይመለሱ ደማቸው በራሳቸው ላይ ይሆናል›› አላቸው፡፡
መና*ፍቁ ንጉሥ መርቅያኖስና ተከታዮቹ ክብር ይግባውና ጌታችንን ‹‹ሁለት ባሕርይ›› በማለታቸው ጉባዔ ሠርተው አባቶች ሲሰበሰቡ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ አባ መቃርስን አስከትሎ በጉባዔው ተገኘ፡፡ አባ ዲዮስቆሮስና አባ መቃርስም ሁለት ባሕርይ ባዮችን አስተምረዋቸው እምቢ ቢሏቸው አውግዘውና እረግመው ከቤተ ክርስቲያን ለዩአቸው፡፡ ለመከራም የተዘጋጁ ሆነው ራሳቸውን አሳልፈው ሰጧቸው፡፡ ከሃዲው ንጉሥም ወደ ጋግራ ደሴት አጋዛቸው፡፡ አባ ዲዮስቆሮስም ለአባ መቃርስ ‹‹አንተ በእስክንድርያ ሀገር ሰማዕትነት ትቀበላለህ›› በማለት ትንቢት ነግረዋቸው ከአንድ ነጋዴ ጋር ወደ እስክንድርያ ላኳቸው፡፡ እዚያም ሲደርሱ መና*ፍቁ ንጉሥ መርቅያኖስ አባ መቃርስን ይዞ ብዙ ካሠቃያቸው በኋላ ኩላሊታቸውን ብሎ ገደላቸውና የሰማዕትነታቸው ፍጻሜ ጥቅምት 27 ቀን ሆነ፡፡ ክርስቲያኖችም ሥጋቸውን ወስደው ከነቢዩ ኤልሳዕና ከመጥምቁ ዮሐንስ ሥጋ ጋር በአንድነት አኖሩት፡፡ ከሥጋቸውም ብዙ ተአምራት ተፈጽመው ታዩ፡፡ የአባ መቃርስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
+ + +
አቡነ መብዓ ጽዮን፡- አባታቸው ንቡረ ዕድ እናታቸው ደግሞ ሀብተ ጽዮን ይባላሉ፡፡ በሌላኛው ስማቸው ተክለ ማርያም ይባላሉ፡፡ ይህንንም ስም ያወጣችላቸው እመቤታችን ናት፡፡ እመቤታችንን ከሕፃንነታቸው ጀምረው እጅግ ይወዷት ነበር፡፡ ትንሽ ልጅ ሳሉ አንድ ካህን ወደ ሀገራቸው በእግድነት መጣና አባታቸው ሀብተ ጽዮን አሳደሩት፡፡
እንግዳውም ካህን የእመቤታችንን ሥዕል ምስለ ፍቁር ወልዳን ይዞ ነበር፡፡ ሲተኛም በራስጌው ያኖራት ስለነበር በሀብተ ጽዮንም ቤት አድሮ ጠዋት ተነሥቶ ሲሄድ የእመቤታችንን ሥዕል በራስጌው እንዳኖራት እረስቶ ሄደ፡፡ ያንጊዜ ሕፃን የነበሩት አባ መብዓ ጽዮንም ሥዕሏን ወስደው ሳሟት፣ በእርሷም ደስ ተሰኙባት፡፡ ለሌላም ሰው አልሰጥም ብለው በአንገታቸው አሰሯት፡፡ ሀብተ ጽዮንም ‹‹ይህችን የእግዳው ካህን ንብረት የሆነች የእመቤታችንን ሥዕል ከቤት እንዳላስቀምጣት ኃጢአት ይሆንብኛል እንዳልሰጠውም ከየት አገኘዋለሁ›› እያለ ሲቀጨነቅ ከዕለታት በአንደኛው ቀን ያንን እንግዳ አገኘው፡፡ ባገኘውም ጊዜ ከቤት የተዋትን የእመቤታችንን ሥዕል እንዲወስድ ነገረው፡፡ መጀመሪያ ሕፃን መብዓ ጽዮን እንዳገኛትና በጣም እንደወደዳት ለሌላ ሰውም አልሰጥም ብሎ በግድ ቀምቶ እንዳስቀመጣት ነገረው፡፡ እንግዳውም ይህን ሲሰማ ‹‹የሥዕሊቱ ባለቤት እርሷ የሕፃኑ እንድትሆን ፈቅዳለታለች፤ ከእኔ ዘንድ መሆኗን ፈቅዳ ቢሆንማ ኖሮ ባልተረሳችኝ ነበር ለዚያ ላገኛት ልጅህ የተገባች ናት›› ካለው በኋላ እርስ በእርሳቸው ሰላምታ ተሰጣጥተው ተለያዩ፡፡
አቡነ መብዓ ጽዮን ዕድሜያቸው ከፍ ሲል ወላጆቻቸው ሚስት ሊድሩላቸው ሲሉ እርሳቸው ግን አላገባም ብለው የዚህን ዓለም ጣዕም ንቀው ነው የመነኑት፡፡ የምንኩስና ልብስ ከለበሱበት ጊዜ ጀምረው በበቅሎና በፈረስ ላይ ተቀምጠው አያውቁም፤ በአልጋም ሆነ በምንጣፍ ላይ አልተኙም ይልቁንም የአንድ ሰው ሸክም የሚያህል ትልቅ ድንጋይ በደረታቸው ተሸክመው ከአመድ ላይ ይተኙ ነበር እንጂ፡፡ ከሰንበት ቀናት ውጭ ሲቀመጡም ድንጋዩን በራሳቸው ላይ ይሸከሙታል፣ ሲሰግዱም በጀርባቸው ያዝሉት ነበር፡፡
አባታችን ለቅዱስ ሥጋ ወደሙ እጅግ ትልቅ ክብር ስለነበራቸው የቆረበ ሰው ከቤተክርስቲያን ወጥቶ ሲሄድ እንቅፋት እንኳን ሲመታው ስለሥጋ ወደሙ ክብር ብለው እግሩ የደማበትን ሰው ደሙን ይጠጡት ነበር፣ ደሙ የፈሰሰበትንም አፈር ይልሱታል፡፡ ይህም የመድኃኔዓለምን ሥጋና ደም ከማክበራቸው የተነሣ ነው፡፡ ጻድቁ ጌታችን በዕለተ ዓርብ መራራ ሐሞት መጠጣቱን አስታውሰው ሁልጊዜ ዐርብ ዐርብ ኮሶ ይጠጡ ነበር፡፡ መድኃኔዓለምም በየጊዜው በሕፃን አምሳል ይገለጥላቸዋል፡፡ በዕለተ ዓርብም