✨🌏የምስራች!
በኦሮሚያ ክልል ለሰልጣኞች እና ስራ ፈላጊዎች በሳኮሜትሪ የታገዘ የኢንተርፕሪዝ ምስረታ መርሃ ግብር በአዳማ ከተማ በይፋ ተጀመረ!!
በሥራና ክህሎት ሚኒስትር በለማው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት E-LMIS የለማው የሳኮሜትሪክ ምዘና ስርዓት በኢንተርፕራይዝ ለመደራጀት ፍላጎት ያላቸውን ስራ ፈላጊዎች እና ሰልጣኞችን ውስጣቸው ያለውን ዝንባሌ፣ ተሰጥኦ እና ብቃት ለይተው እንዲያውቁ እንዲሁም በአካባቢያቸው ከሚገኘው ጸጋ ጋር በማስተሳሰር ወደ ተለያዩ ዘርፎች እዲሰማሩ የሚያግዝ አገልግሎት ነው፡፡
የዚሁ አካል የሆነው እና በኦሮሚያ ክልል አዳማ የተካሄደው የስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ከ2000 በላይ ሰልጣኞችን እና ስራ ፈላጊ ወጣቶች ያለውን እምቅ ችሎታ እና ዝንባሌ ለመለየት አንዲያግዛቸው የሰይኮሜትሪ ግንዛቤ ማስጨበጫ እና ምዘና በይፋ ተጀሯል፡፡ ይህ የሳይኮሜትሪ ምዘና በማካሄድ ወጣቶች ያላቸው እምቅ ችሎት እና ፍላጎት እንዲለዩ በማድረግ ተሰጥኦዋቸውን መሰረት ባደረገ የስራ ዘርፎች እዲሰማሩ የሚረዳ ነው፡፡
በተጨማሪም ይህ ስርዓት በአከባቢው ያለውን የተለየ ጸጋ መሰረት ባደረጉ የስራ መስኮችን በመለየት ወጣቶች ካላቸው ዝንባሌ ጋር በማስተሳሰር የኢንተርፕራይዝ አደረጃጀትን የሚያግዝ ነው፡፡
በመረሃ ግብሩ በአጠቃላይ 20ሺህ ሚሆኑ ዜጎችን የስራ ስምሪት በስርዓቱ ለማገግ እቅድ ተይዟል፡፡
✨ብቁ ሰራተኛ • ብቁ ቀጣሪ • ብቁ ውሳኔ ሰጪ
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!
ድህረ-ገፃችንን ይጎብኙ ይመዝገቡ :
https://lmis.gov.et