የፃፍኩልሽን ደብዳቤ አታንብቢው!
(ልዑል ኃይሌ)
ሞኝ ነው ወረቀት
የፃፉለትን ቃል ያምናል ተቀብሎ፤
አልወዳትም የሚል
ፅሁፍ ሰፈረበት የኔን እውነት ጥሎ፤
ከንዴት ስነቃ
ወረቀት የያዘው ረገምኩት ያንን ቃል፤
መውደዴ እንዴት ጠፋው
በብጣሽ ወረቀት እንዴት ፍቅር ያልቃል?፤
.
ይህን የውሸት ቃል
የውሸት ደብዳቤ ጨምድጄ እንዳልቀደው፤
እንዲሠጥሽ ብዬ
አዘጋጅቼለት ፖስተኛ ወሠደው፤
ግን ደግሞ ፈራሁኝ
በዚህ ቅፅበት ምክንያት አንቺን እንዳላጣ፤
የፍርዴን ደብዳቤ
የሚሽርልኝን ቅፅበት ከየት ላምጣ?፤
.
ሌላ ደብዳቤ ፃፍኩ!..
ይድረስ ለማልወድሽ
ለማትናፍቂኝ ሴት ለማልፈልግሽ ሠው፤
ከሃዲ ነች ብልም
ሰሚ ስለማጣ ዓለሙ ይቅመሠው፤
ሂጂለት ሕዝበ-አዳም
ምን ተዳዬ 'ኔ ብቻ ለምን 'ታመማለሁ፤
ማመን የፈለገ ይምጣና ይጎብኘኝ
ስታርጂኝ የቀረ ጠባሳ ይዣለሁ፤
ካመንሺም እመኚ
ካላመንሺም ይቅር፤
ከእንግዲህ በቅቶኛል
የዕቃቃ ጨዋታ የማስመሠል ፍቅር፤
.
ደገምኩት!ያንን ቃል
የላዩን መልዕክቴን የፊቱን ደብዳቤ፤
ሞኝ ነው ወረቀት
ምንም አልገባውም
ባሠፈርኩበት ቃል እንዲያ መንገብገቤ፤
.
ደግሜ መከርኩት
'አትመልከትብኝ የልቤን ስብራት'፤
ይልቅ እንዳልታመምኩ አስመስለህ ጥራት፤
ብዬ ብገስፀው
እያስተሳሰረ ከልቤ ሕመም ጋራ፤
እውነቴን መሸፈን
ክህደቴን መሸፈን ወረቀቴ ፈራ፤
.
እውነት ነው!
.
ሞኝ ነው ሞኝ ነው
ሞኝ ነው ወረቀት፤
እንዴት ብሎ አመነኝ
ባሰፈርኩበት ልክ በፃፍኩበት ርቀት፤
.
(ቲሽ!...ቀደድኩት!..)
.
(በቃ ትቼዋለሁ)
ለማስፈር ከበደኝ
ለዛኛው ደብዳቤ ማስተባበያ ቃል፤
ባስተባብለውም
የብዕሬ ቀለም ከልቤ እውነት ርቋል፤
.
ደጋግመሽ ብትጥይኝ
ያላንቺ ማትወጣ ጀምበር ታቅፌያለሁ፤
ይሄንን እያወቅኩ
አልወድሽም ብዬ እንዴት እፅፋለሁ?፤
ስለዚህ ሲደርስሽ
"ወረቀት ሞኝ ነው" የሚል ቃል አስታውሺ፤
ሞኝ አያጣላንም
ቀዳድደሽ ጣዪና ደግመሽ ተመለሺ፤
ታኅሳስ 5,2012 ዓ.ም.
🦋🙏
@betagitim
@betagitim.
@betagitim
(ልዑል ኃይሌ)
ሞኝ ነው ወረቀት
የፃፉለትን ቃል ያምናል ተቀብሎ፤
አልወዳትም የሚል
ፅሁፍ ሰፈረበት የኔን እውነት ጥሎ፤
ከንዴት ስነቃ
ወረቀት የያዘው ረገምኩት ያንን ቃል፤
መውደዴ እንዴት ጠፋው
በብጣሽ ወረቀት እንዴት ፍቅር ያልቃል?፤
.
ይህን የውሸት ቃል
የውሸት ደብዳቤ ጨምድጄ እንዳልቀደው፤
እንዲሠጥሽ ብዬ
አዘጋጅቼለት ፖስተኛ ወሠደው፤
ግን ደግሞ ፈራሁኝ
በዚህ ቅፅበት ምክንያት አንቺን እንዳላጣ፤
የፍርዴን ደብዳቤ
የሚሽርልኝን ቅፅበት ከየት ላምጣ?፤
.
ሌላ ደብዳቤ ፃፍኩ!..
ይድረስ ለማልወድሽ
ለማትናፍቂኝ ሴት ለማልፈልግሽ ሠው፤
ከሃዲ ነች ብልም
ሰሚ ስለማጣ ዓለሙ ይቅመሠው፤
ሂጂለት ሕዝበ-አዳም
ምን ተዳዬ 'ኔ ብቻ ለምን 'ታመማለሁ፤
ማመን የፈለገ ይምጣና ይጎብኘኝ
ስታርጂኝ የቀረ ጠባሳ ይዣለሁ፤
ካመንሺም እመኚ
ካላመንሺም ይቅር፤
ከእንግዲህ በቅቶኛል
የዕቃቃ ጨዋታ የማስመሠል ፍቅር፤
.
ደገምኩት!ያንን ቃል
የላዩን መልዕክቴን የፊቱን ደብዳቤ፤
ሞኝ ነው ወረቀት
ምንም አልገባውም
ባሠፈርኩበት ቃል እንዲያ መንገብገቤ፤
.
ደግሜ መከርኩት
'አትመልከትብኝ የልቤን ስብራት'፤
ይልቅ እንዳልታመምኩ አስመስለህ ጥራት፤
ብዬ ብገስፀው
እያስተሳሰረ ከልቤ ሕመም ጋራ፤
እውነቴን መሸፈን
ክህደቴን መሸፈን ወረቀቴ ፈራ፤
.
እውነት ነው!
.
ሞኝ ነው ሞኝ ነው
ሞኝ ነው ወረቀት፤
እንዴት ብሎ አመነኝ
ባሰፈርኩበት ልክ በፃፍኩበት ርቀት፤
.
(ቲሽ!...ቀደድኩት!..)
.
(በቃ ትቼዋለሁ)
ለማስፈር ከበደኝ
ለዛኛው ደብዳቤ ማስተባበያ ቃል፤
ባስተባብለውም
የብዕሬ ቀለም ከልቤ እውነት ርቋል፤
.
ደጋግመሽ ብትጥይኝ
ያላንቺ ማትወጣ ጀምበር ታቅፌያለሁ፤
ይሄንን እያወቅኩ
አልወድሽም ብዬ እንዴት እፅፋለሁ?፤
ስለዚህ ሲደርስሽ
"ወረቀት ሞኝ ነው" የሚል ቃል አስታውሺ፤
ሞኝ አያጣላንም
ቀዳድደሽ ጣዪና ደግመሽ ተመለሺ፤
ታኅሳስ 5,2012 ዓ.ም.
🦋🙏
@betagitim
@betagitim.
@betagitim