ሀሳብና ስሜት …
ብዙ መላእክት ያየ
የስድስት ወር ጨቅላ ፍልቅልቅ ፈገግታ
የጠዋት ላይ ጤዛ
የጤዛ ላይ ውሃ እንክብል ጠብታ
የረጋው ሃይቅ ላይ
ከንፋስ ያወራ ሰንበሌጥ ሹክሹክታ
እኝህን እያየሁ እኝን እየሰማሁ
ናፍቆት ብራና ላይ ጨረቃዋን ስዬ
ሐዘን ናፍቆት ስቃይ ወ..ዲያ ማዶ ጥዬ
(እንዲህ አይነት ሀሳብ)
ሰማይ ላይ ደመና
ደመና ላይ ሥዕል
ሥዕሉ ውስጥ እኔ
እኔ ውስጥ ደግሞ አንች
ፍቅር ተወለደ ጥላቻችን ሞተ
ግዜው ተለወጠ ዘመን ለኛ ባተ
ንፋስ ወድያ ወዲህ እኛ ግን ወደላይ
ተቃቅፈን ወደላይ…
የነገ ፍቅራችን ዛሬ ውስጥ እስክናይ
ተቃቅፈን ወደላይ
(እንዲህ አይነት ስሜት)
ነገ ሙሉ እሚሆን የሙሉነት አስኳል
ንጹህነትሽ ላይ የማኖርን ያህል
ነገ እርግብ የሚሆን የእርግብ እንቁላል
በላባ ተስሞ የመሞቅን ያህል
ደመናው ነጭ ነው ፀሃይዋ እሳት ናት
ሰማይ ላይ ሉል አለ ጨረቃም ቤቴ ናት
ብርቱ ዋናተኛ….
ዶልፌን ግማሽ ክቡን ሲቀዝፍ ውሎ ተኛ
… ይህን ሁሉ ያየው ይህ የሕይወት ባሕር
አልጮኸም ዝም ብሏል
ይህ የሕይወት ባሕር ለራሱ ዝም ብሎ
እኔን ግን …እኔን ግን …
ወርቅማ አሳ ደግሞ
ሚልዮን እንቁላል መጠበቁን ትቶ
ከሚስቱ ጋር ፍቅር መዳራት ጀምሯል
እንቁላሉን ተውት …
እንዲህ ባለ ግዜ እንዲህ ባለ ሰአት
ወርዶ አያውቅም ማአት
ታይቶ አያውቅም ጠላት
(እንዲህ አይነት እውነት)
በምናብበት ባገርሽ ባገሬ
ለምለም ጨፌ ግጠው
ከምንጩ ጠጥተው
ግልገሎቹ ሮጡ
ግልገሎቹ ሮጡ
አንደኛው ነጭ ነው
አንደኛውን እንጃ ብቻ ግን ነጭ ነው
ሚስጢር የለበትም ትርጉሙ ሰላም ነው
ግልገሎቹ ሮጡ ያቻት እናታቸው
ፍቅር የሞላውን ወተት ያጋተውን
ጡቷን ልትሰጣቸው እንኩ ልትላቸው
የግልገል ቡረቃ የደመና ሥዕል
የዶልፊን ቀዘፋ የእርግብ እንቁላል
አንድ ነው ትርጉሙ አንድ ነው ስያሜው
እንደኔ እና እንዳንች አንድ ሆኖ ላየው
(እንዲህ አይነት ሀሳብ)
ይህን ሁሉ ያየው ይህ የሕይወት ባሕር
አልጮኸም ዝም ብሏል
ይህ የሕይወት ባሕር ለራሱ ዝም ብሎ
እኔን ግን … እኔን ግን
"ሂድ በደስታ ቦርቅ በረሃው ላይ ዝነብ
ውቅያኖሱን ቀዝፍ
ሜዳው ይሁን ምንጣፍ
ተራራውን እቀፍ
ሂድ በደስታ ቦርቅ እንደ እንቦሳ ፈንጥዝ
ደመናውን ጋልበው በግዛትህ እዘዝ
መሬት ላይ ቁጭ በል ዘለህ ሰማይ ንካ
ሂድ በደስታ ቦርቅ ጠልቀህ ግባ ዲካ"
እንዲያ በል ይለኛል እንዲህ ሁን ይለኛል
እረፍት ሳይሰጠኝ ጠዋትና ማታ
ፈልጌሽ ፈልጌሽ ያገኘሁሽ ለታ
እንዲህ አይነት ስሜት እንዲ አይነት እውነታ!!!
@betagitim
@betagitim
ብዙ መላእክት ያየ
የስድስት ወር ጨቅላ ፍልቅልቅ ፈገግታ
የጠዋት ላይ ጤዛ
የጤዛ ላይ ውሃ እንክብል ጠብታ
የረጋው ሃይቅ ላይ
ከንፋስ ያወራ ሰንበሌጥ ሹክሹክታ
እኝህን እያየሁ እኝን እየሰማሁ
ናፍቆት ብራና ላይ ጨረቃዋን ስዬ
ሐዘን ናፍቆት ስቃይ ወ..ዲያ ማዶ ጥዬ
(እንዲህ አይነት ሀሳብ)
ሰማይ ላይ ደመና
ደመና ላይ ሥዕል
ሥዕሉ ውስጥ እኔ
እኔ ውስጥ ደግሞ አንች
ፍቅር ተወለደ ጥላቻችን ሞተ
ግዜው ተለወጠ ዘመን ለኛ ባተ
ንፋስ ወድያ ወዲህ እኛ ግን ወደላይ
ተቃቅፈን ወደላይ…
የነገ ፍቅራችን ዛሬ ውስጥ እስክናይ
ተቃቅፈን ወደላይ
(እንዲህ አይነት ስሜት)
ነገ ሙሉ እሚሆን የሙሉነት አስኳል
ንጹህነትሽ ላይ የማኖርን ያህል
ነገ እርግብ የሚሆን የእርግብ እንቁላል
በላባ ተስሞ የመሞቅን ያህል
ደመናው ነጭ ነው ፀሃይዋ እሳት ናት
ሰማይ ላይ ሉል አለ ጨረቃም ቤቴ ናት
ብርቱ ዋናተኛ….
ዶልፌን ግማሽ ክቡን ሲቀዝፍ ውሎ ተኛ
… ይህን ሁሉ ያየው ይህ የሕይወት ባሕር
አልጮኸም ዝም ብሏል
ይህ የሕይወት ባሕር ለራሱ ዝም ብሎ
እኔን ግን …እኔን ግን …
ወርቅማ አሳ ደግሞ
ሚልዮን እንቁላል መጠበቁን ትቶ
ከሚስቱ ጋር ፍቅር መዳራት ጀምሯል
እንቁላሉን ተውት …
እንዲህ ባለ ግዜ እንዲህ ባለ ሰአት
ወርዶ አያውቅም ማአት
ታይቶ አያውቅም ጠላት
(እንዲህ አይነት እውነት)
በምናብበት ባገርሽ ባገሬ
ለምለም ጨፌ ግጠው
ከምንጩ ጠጥተው
ግልገሎቹ ሮጡ
ግልገሎቹ ሮጡ
አንደኛው ነጭ ነው
አንደኛውን እንጃ ብቻ ግን ነጭ ነው
ሚስጢር የለበትም ትርጉሙ ሰላም ነው
ግልገሎቹ ሮጡ ያቻት እናታቸው
ፍቅር የሞላውን ወተት ያጋተውን
ጡቷን ልትሰጣቸው እንኩ ልትላቸው
የግልገል ቡረቃ የደመና ሥዕል
የዶልፊን ቀዘፋ የእርግብ እንቁላል
አንድ ነው ትርጉሙ አንድ ነው ስያሜው
እንደኔ እና እንዳንች አንድ ሆኖ ላየው
(እንዲህ አይነት ሀሳብ)
ይህን ሁሉ ያየው ይህ የሕይወት ባሕር
አልጮኸም ዝም ብሏል
ይህ የሕይወት ባሕር ለራሱ ዝም ብሎ
እኔን ግን … እኔን ግን
"ሂድ በደስታ ቦርቅ በረሃው ላይ ዝነብ
ውቅያኖሱን ቀዝፍ
ሜዳው ይሁን ምንጣፍ
ተራራውን እቀፍ
ሂድ በደስታ ቦርቅ እንደ እንቦሳ ፈንጥዝ
ደመናውን ጋልበው በግዛትህ እዘዝ
መሬት ላይ ቁጭ በል ዘለህ ሰማይ ንካ
ሂድ በደስታ ቦርቅ ጠልቀህ ግባ ዲካ"
እንዲያ በል ይለኛል እንዲህ ሁን ይለኛል
እረፍት ሳይሰጠኝ ጠዋትና ማታ
ፈልጌሽ ፈልጌሽ ያገኘሁሽ ለታ
እንዲህ አይነት ስሜት እንዲ አይነት እውነታ!!!
@betagitim
@betagitim