We are all connected!
By Demis Seifu
Part One
“We are one, after all, you and I, together we suffer, together exist and forever will recreate one another.” ― Pierre Teilhard de Chardin
ሲጀምር ሕይወት ከአንድ ምንጭ ፈሰሰች ወደ ሕላዌ ውቅያኖስ ወደ መኖር ወደብ Creationism እንደሚለው ከምንም ባዶነት ወደ አንዳች ገሃድነት፣ አልያም የ Big Bang theory አራማጆች እንደሚነግሩን ከአንዳች ኢምንትነት ወደ ሁለንተናዊ ግዝፈት አልያም ዳርዊንያውያኑ Evolutionist እንደሚሉን በዝግመተ ለውጥ በሂደተ ውላጤ በምንም ይሁን ብቻ ከአንድ ምንጭ ከሕላዌ በረከት ከዘላለማዊ ፍሰት እስከ ከሌለው ኑረት ስለዚህም እኛ ለሕይወት የአንድ ግንድ ብዙ ቅርንጫፎች ነን ስሩ ከማይደርቅ፣ ውሃው ከማያልቅ ውቅያኖስ መሃል ያለ ዘላለማዊ ግንድ በተገበርከው ክፋት ብቻ ሳይሆን በተብሰልስሎትህ ሂደት ነገር ዓለማችን ይታወካል በተነፈስከው በጎ ቃል አይደለም ባሰላሰልካት ደግነትም መውጣት መግባታችን ይዋባል ብቻህን አይደለህምና የብቻ ሰላም የለህም አልተነጣጠልንምና የብቻ ሕመምም አይኖርህም የድርጊት ሆነ የሃሳብ ሲዖልህ ጨለማ የውሎዋችን ብርሃን ውስጥ ይረጫል የበጎነትህ ገነት መዓዛ ለየአፍንጫችን ይደርሳል የግብርህ ሆነ የኃልዮ ምላሽህ ገሃነም የሁላችንንም ልብ ያነዳል የቅንነትህ መንግስተ ሰማይ ለየነፍሳችን ይተርፋል የግዙፍ ውቅያኖስ አካል ነን እኛም ሆንን በዙሪያችን ያለው የተፈጥሮ ስንክሳር የውቅያኖሱ አንድ ጠብታ ነው...