የተፈጥሮ መላው ነጥብ መመልከት ነው።ሰዎችን፡እፀዋትን፡ክስተቶችን፡አለማትን ማንነቶችን፡ምናቦችን፡ለውጧችን ያለምንም ጣልቃ ገብነት መመልከት!ማንም በተፈጥሮ የሚበላበት አፍ እንጂ የሚነጋገርበት ቃል አልተሰጠውም። ፅሞና ከተፈጥሮ የወረስናት ስትሆን ተናጋሪነት ግን ያደበርነው ክህሎት ነው።ካህሊል ጅብራን "I have learned silence from the talkative, toleration from the intolerant, and kindness from the unkind; yet strange, I am ungrateful to these teachers." በሚል የገለፀው ቃል የሰው ተፈጥሮ በመመልከት ውስጥ የሚመጣው አንደኛው የመማር ደረጃን ለማስታወስ ነው። መናገር ካለብን የምናገረው የተመለከተውን ሲሆን ያኔ የሕልውናችን ስርአት ቦታውን ያገኛል። በዝምታ ውስጥ የቅጣት አርጬሜ አለ፣ ፣የደስታ ኃይል አለ፣የፀፀት እስትንፋስ አለ ፣የዝለት ስቃይ አለ. . .ሁሉም አእምሮ ውስጥ ያለውን በቃል ድርደራ ማውጣት አይችልም።ቃላቶች ስንኩል ናቸው የነፍስን ሁነት መግለጥ አይችሉም።ምናብ በቃል ውስጥ ሲገለፅ መልኩ ያጣል ይደበዝዛል።የየትኛው አርቲስት ህልም በቃል ወይም ስዕል ለመግለፅ ሲሞክር ይከሽፋል።ፅሞና ከራስ ጋር ንግግር ራሱ በቂ አደለም።ምንም የተሻለ ጥቅም የለውም።ቃሎች ያለዝምታ ኃይል ያጣሉ።ዝምታም ያለ ተመልካችነት ተራ ይሆናል።ሰው ምንም ባይናገርም ነገር ግን ሁሉን ቢያይ ይሻለዋል
( 𓂀 )
( 𓂀 )