🌹#ምዕራፍ-፩_የነገረ ማርያም ምንነትና የመቤታችን ታሪክ🌹
#መግቢያ
#ቀጣይ_ትምህርታችን-->ነገረ ማርያምን መማር ለምን አስፈለገ?
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!💐
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯
#መግቢያ
በነገረ ድኅነት ትምህርት ውስጥ "ምክኒያተ ድኅነት" የሆነችውን የእመቤታችንን ነገር ማወቅና መረዳት እጅግ አስፈላጊ ነው።
ምክኒያቱም እግዚአብሔር ሰው ሆነ፣ ተወለደ ስንል እንዴት ሰው ሆነ የሚለው ጥያቄ መመለስ ያለበት በእመቤታችን ስለሆነ ነው፡፡
የትንቢተ ነቢያት ማረፊያ፣ የስብከተ ሐዋርያት መነሻ፣ የሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ምስጢር ነገረ ማርያም ነው።
ያለ ነገረ ማርያም ነገረ ክርስቶስን መናገር አይቻልም።
በክርስትና ሃይማኖት ታሪክ የተነሱ አያሌ መናፍቃን የመጀመሪያ ችግራቸው ነገረ ማርያምን አማናዊ ትምህርት መቀበል ነበር። ያም ችግራቸው ክርስቶስን በትክክል እንዳያምኑት አድርጓቸዋል። በነገረ ማርያም የተጣራ ትምህርትና እምነት ቢኖራቸው ኑሮ ለኑፋቄ አይጋለጡም ነበር።
ነገረ ማርያምን ከነገረ ክርስቶስ መለየት አይቻልም። የተዋህደ ነው። ስለ እመቤታችን የሚነገረው ከፉም ሆነ በጎ ክርስቶስን ይነካዋል። የእግዚአብሔርን የማዳን ሥራ በምንናገርበት ጊዜ እመቤታችንን ወደ ጎን መተው አይቻልምና። ምክኒያቱም ወልዳ ያስገኘች፣ አዝላ የተሰደደች፣ በማስተማር ጊዜው ከአገር አገር አብረው የተንከራተተች ናት። በተሰቀለበት ዕለትም ከእግረ መስቀሉ አልተለየችም።
ስለ ነገረ ድኅነት ስንናገር ጌታ ድኅነታችንን በመስቀል ላይ ፈጸመ የምንለው የዕለት ጽንስ ሁኖ በእመቤታችን ማኅጸን የጀመረውን ነው። ሥጋውን ቆረሰልን፣ ደሙን አፈሰሰልን፣ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠልን ብንል ከእርሷ የነሳውን ነው። ከእርሷ ነስቶ በመስቀል ላይ የፈተተውን ሥጋውን ደሙን የሕይወት ማዕድ አድርጎ ሰጥቶናል።
ከዚህም በላይ ምልዕተ ጸጋ ምልዕተ ክብር ሰለሆነች ሰዎች ነገረ ድኅነትን አምነው በምግባር ለመኖር ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ በሚያደርጉት ተጋድሎ ውስጥ ረዳት ምርኩዝ ልትሆናቸው የተሰጠች ስለሆነ አማላጅነትን፣ ፀጋዋን፣ በረከቷን፣ እየተማጸኑ መኖር የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን የነገረ ድኅነት አስተምህሮ አካል ነው።
ስለሆነም ተማሪዎች ትምህርተ ክርስትናን፣ ትምህርተ ሃይማኖትን፣ ክርስቲያናዊ ሕይወትና ሥነ ምግባርን እና የመጽሐፈ ቅዱስ ጥናትን ከተማሩ በኋላ የነገረ ማርያምን ትምህርት መማር አስፈላጊ ነው።
#ቀጣይ_ትምህርታችን-->ነገረ ማርያምን መማር ለምን አስፈለገ?
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!💐
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯