"
በአካውንትህ ውስጥ ካለ ብር 86,400 አንድ መናኛ 10 ብር ቢሰርቅህ፣ በብስጭት የቀረህን 86,390 ወርውረህ፣ 10 ብር ፍለጋ በመኳተን ጊዜህን ታባክናለህ ወይስ ኑሮህን ትቀጥላለህ?!"
ዐየህ፦ በቀን ውስጥ 86,400 ሴኮንዶች አሉ። መጥፎ አመለካከት ባለው አንድ ግለሰብ የ10 ሴኮንድ አስቀያሚ ንግግር ወይም በሆነብህ ቅፅበት ሳቢያ ቀሪ 86,390 ሴኮንዶችህን አታበላሽ። ለአንድ ገፅ ስህተት 1000 ገፅ መፅሐፍ በመቅደድ ከማባከን ተቆጠብ።
ተራ ነገር በማሳደድ የዕድሜ ካቦችህ እንዲናዱ በፍፁም አትፍቀድ! በምንም ሁኔታ ወደኋላ ዕያየህ ወደፊትህን አታዘግይ።"