"፭ኛ ኮርስ "ነገረ ማርያም"
#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን🙏
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
፪.፪, #ክብረ_ድንግል
፪.፪.፬, #የክብረ_ድንግል_መገለጫዎች
፪.፪.፬.፩, #ስግደት_ለእመቤታችን
የእመቤታችን ክብር (ማክበራችንን) ከምንገለጥበት መንገድ አንዱ ለእመቤታችን የሚገባ “የፀጋ ስግደት” ነው። አንዳንድ ሰዎች (ከሃይማኖት ውጭ የሆኑ) ለእመቤታችን የምናቀርበውን “የፀጋ ስግደት” ልክ ለአምልኮ (ለእግዚአብሔር ብቻ የሚሰገድ) ስግደት
አድርገው ሲነቅፉት ይሰማሉ።
ኦርቶድክሳዊ ተዋህዶቤተ ክርስቲያን ግን ለእመቤታችን የምታቀርበው ስግደት የፀጋ (የአክብሮት) ስግደት እንጂ የአምልኮት ስግደት አይደለም። በእርግጥ የአሰጋገድ ሥርዓታችን ስንሰግድ ማለትም ለእግዚአብሔር የአምልኮት ለእመቤታችን የፀጋ ስግደት አንድ አይነት የሆነ ቢመስልም አምላካችን እግዚአብሔር ነገርን ሁሉ ስናደርግ አስቀድሞ ልባችንን የሚያይ በመሆኑ ዋናው ነገር ስግደቱን የሚያቀርበው ሰው ሕሊናው እና ልቡናው ነው። ስለዚህም ለእመቤታችን የፀጋ (የአክብሮት) ስግደት፤ ለአምላካችን ለልዑል እግዚአብሔር የአምልኮ ስግደት እናቀርባለን።
ለእመቤታችን የፀጋ ስግደት መስገድ እንዲገባ ቅዱሳት መጻሕፍት ተባብረው አስረግጠው ተናግረዋል። (ኢሳ 49፥22) “ወንድች ልጆችሽንም በጫንቃቸው ላይ ይሸከሟቸዋል። ነገስታትም አሳዳጊ አባቶችሽ ይሆናሉ። እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ። ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል የእግርሽን ትቢያ ይልሳሉ”። ብሎ ነቢዩ ቅዱስ ኢሳይያስ አስቀድሞ ተናግሯል። በሌላም ስፍራ ነቢዩ እንዲህ ብሏል። “የእግሬን ሥፍራ እሰብራለሁ፤ የአስጨናቂዎችም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ። የእግዚአብሔር ከተማ የእሥራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል። (ኢሳ 60፥13)
መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስም በሐዲስ ኪዳን ገና በእናቱ በቅድስት ኤልሳቤጥ ማኅፀን ሳለ በመንፈስ ቅዱስ የተመላ ስለነበር የእመቤታችንን ድምፅ ለኤሌሳቤጥ በተሰማበት ቅጽበት የፀጋ ስግደት ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የአምልኮት ስግደት በማኅፀነ ድንግል ሌላው ጌታ ለኢየሱስ ክርስቶስ ሰግዷል። ይህን ያስደረገ መንፈስ ቅዱስ ነው። ዛሬም የአግዚአብሔር መንፈስ ያልተለየው ሁሉ ለእመቤታችን ክብር ይንበረከካል ይሰገድለታልም። (ሉቃ 1፥15 / ሉቃ 1፥39-46)
፪.፪, #ክብረ_ድንግል
፪.፪.፬, #የክብረ_ድንግል_መገለጫዎች
፪.፪.፬.፪, #ምስጋና_ለእመቤታችን
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቀደም ብለን እንደገለጽነው ከሴቶች ሁሉ ተለይታ የተባረከች፤ በዚህም የአምላክ እናት የሆነ፤ በአማላጅነት በሰው እና በእግዚአብሔር መካከል የምትቆም፤ ንጽሕት ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን ሁሉ በላይ የከበረች፤ ማህደረ መለኮት በመሆኗ ከባህርይ አምላክ ቀጥል የፀጋ ምስጋና ይቀርብላታል። በቤተ ክርስቲያናችን በመዝሙራችንም ሆነ በቅዳሴያችን ከስመ ሥላሴ ቀጥለን የምንጠራው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ስም ነው።
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በብሉይ ኪዳን ክብሯ እና ልዕልናዋ በነቢያት ሲነገር የኖረ በሐዲስ ኪዳንም ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም በቀር “ደስ ይበልሽ ጸጋ የመላብሽ ሆይ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው አንቺ ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ” ተብሎ የተመሰገነ ማንም አልነበረም (ሉቃ 1፥28) ሰማያውያን መላእክት ቅዱስ ገብርኤልን አብነት አድርገው ያመሰግኗታል። ደቂቀ አዳም ደግሞ እንደ ቅዱስ ገብርኤል ባለ ምስጋና እንድታመሰግን መንፈስ ቅዱስ ገልፆላት እመቤታችንን ያመሰገናች ቅድስት ኤልሳቤጥን አብነት አድርገን እናመሰግናታለን። “...በኤልሳቤጥ መንፈስ ቅዱስ መላባት በታላቅ ድምፅ ጮኸ አንቺ ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ የማህፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው” አለች እንዲል። (ሉቃ 1፥39-45)
እመቤታችን ራሷ “ከእንግዲህ ወዲህ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል’’ ብላ ተናግራለች። (ሉቃ 1፥48) ይህም ማለት ትውልደ ሴም፣ ትውልደ ካም፣ ትውልደ ያፌት ንዕድ ነሽ ክብርት ነሽ እያሉ ያመሰግኑኛል ማለቷ ነው። ከዚህ የወጣ ትውልድ የለምና እንዲህ ብላ በተናገረችው መሠረትም በልጇ ያመንን ኦርቶድክሳዊያንም መመኪያ ዘውዳችን ጥንተ መድኃኒታችን የንፅሕና መሠረታችን ድንግል ማርያም ናት ብለን እናመሰግናታለን።
አምላካችን እግዚአብሔር ለወዳጁ ለአብርሃም “ታላቅ ሕዝብ አድርግሃለሁ፣ እባርክሃለሁ፣ ስምህንም አከብረዋለሁ። ለበረከትም ሁን የሚባርኩህንም እባርካለሁ፣ የሚረግሙህንም እረግማለሁ የምድር ነገዶች ሁሉ በአንተ ይባረካሉ። (ዘፍ 12፥1-3) ብሎታል ከዚህ የእግዚአብሔር ቃል የምንማረው የቅድስተ ቅዱሳን የድንግል ማርያም ስም ክቡር መሆኑንና ብናመሰግናት በረከትን እንደምናገኝ ብንነቅፋት መርገምን እንደምንቀበል ነው። ምክኒያቱም እመቤታችን የአብርሃም ዘር ነች አንድም እመቤታችን የአብርሃምን አምላክ የወለደች ለአብርሃም የተነገረው ተስፋ ሁሉ የተፈጸመባት ስለሆነ ከአብርሃም ትበልጣለች። ስለዚህ ለእመቤታችን ምስጋና ይገባታል።
ለእመቤታችን ምስጋና እንደሚገባ ከላይ ለመመልከት እንደ ሞከርነው ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው እመቤታችንን ካመሰገኑ ምስጋናቸው በመጽሐፍ ተጽፎ ከሚገኙ ሊቃውንት መካከል የጥቂቶቹን እንመለከታለን።...
፪.፪, #ክብረ_ድንግል
፪.፪.፬, #የክብረ_ድንግል_መገለጫዎች
፪.፪.፬.፪, #ምስጋና_ለእመቤታችን
ሀ. አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፦ ይህ ቅዱስ የእመቤታችን ፍቅር ያደረበት በመሆኑ በሰዓታት ድርሰቱ እመቤታችንን በሰፊው አመስግኗታል። ለአብነት ያህልም፦
“እዌድሰኪ ኦ ድንግል ምልእተ ውዳሴ መጠነ ይከል አፋየ አሰተበፅዕ ዕበየኪ ማርያም” #ትርጉም ምስጋናን የተመላሽ ድንግል ማርያም ሆይ አመሰግንሻለሁ የአንችን ምስጋና እና ልዕልና አንደበቴ ተናግሮ መፈፀም አይቻለውም።
“ልሳነ ኪሩቤል ኢይክል አብጽሐ ውዳስኪ ወአፈ ሱራፌል ኢይፈጽም ነጊረ እበየኪ ማርያም” #ትርጉም የኪሩቤል አፍ ምስጋናሽን መፈፀም አይቻለውም በሱራፌል አንደበትም ልዕልናሽ ድንቅነትሽ ተነግሮ አያልቅም (ሰዓታት ዘለሊት)
ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት ወሰብሕት በሀዋርያት አክሊለ በረከቱ ለያዕቆብ ወትምክሕተ ቤቱ ልእሥራኤል ።ትርጉም፦ እመቤታችን ማርያም ሆይ በነቢያት እና በሐዋርያት አንደበት ትመሰገኛለሽ ለአባታችን ለያዕቆብ የበረከቱ ዘውድ አንቺ ነሽ ለእሥራኤል ዘሥጋ ለእስራኤሌ ዘነፍስ መመኪያቸው አንቺ ነሽ።
ለ. አባ ሕርያቆስ፦ ይህ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ ተቀኝቶ ለእመቤታችን የቅዳሴ ድርሰት የደረሰ ሲሆን ይህ ቅዳሴ በሙሉ የእመቤታችንን ክብር፣ ልዕልና፣ ቅድስና፣ ድንግልና የሚመሰክር ነው። ለአብነት ያህልም፦ "ኦ ማርያም በእንተዝ ናፍቅረኪ ወናብዕኪ እስመ ወልደኪ ለነ መብልዕ ጽድቅ ዘበአማን ወስቴ ሕይወት ዘበአማን” #ትርጉም፦ ማርያም ሆይ ስለዚህ እንወድሻለን ከፍ ከፍም እናደርግሻለን እውነተኛ የሕይወት መብልንና እውነተኛ የሕይወት (መጠጥ) ክርስቶስን ወልደሽልናልና።
“ኦ ድንግል ምልዕተ ውዳሴ በመኑ ወበአምሳለ መኑ ናስተማስለኪ” #ትርጉም፦ ምስጋናን የተመላሽ ሆይ በማን እና በምን ምሳሌ እንመስልሻለን?