የህዳር 11/2017 አበይት የዓለም ዜናዎች
🇷🇺🇺🇦 ሩሲያ በዩክሬን መዲና ኬይቭ ታካሂደዋለች ተብሎ በተሰጋው ግዙፍ የአየር ጥቃት ሳቢያ በመዲናዋ የሚገኙ የአሜሪካ፣ የጣሊያን፣ የግሪክ እና የሌሎች ሀገራት ኤምባሲዎች እየተዘጉ ነው ተባለ።
🇺🇦 የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ አሜሪካ የምታደርግልን የጦር መሣሪያ ድጋፍ ከቆመ ከሩሲያ ጋር የገባንበትን ጦርነት ተሸናፊ እንሆናለን ሲሉ ተናገሩ።
🇮🇱🇮🇷 የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ የዛሬ ወር ገደማ በኢራን ላይ ባካሄድነው ጥቃት የቴህራን የተወሰኑ የኒውክለር ጣቢያዎች መተናል ሲሉ ለሀገሪቱ ፓርላማ ተናገሩ።
🇿🇦 በቀጣይ የአውሮፓውያኑ 2025 የሚካሄደውን የቡድን 20 ሀገራት የመሪዎች ጉባዔ እንድታዘጋጅ ደቡብ አፍሪካ ተመረጠች።
🔷 በሥልጣን ላይ ያሉት የራስ ገዟ ሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሄ በምርጫው አሸናፊ ለሆኑት ተመራጩ ፕሬዝዳንት እንኳን ደስ አለዎት በማለት ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ለማድረግ ቃል ገቡ።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews