ኢትዮ መረጃ - NEWS


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት
ማክበር ባትችል አታዋርዳት
ማራመድ ባትችል አታዘግያት
መጠበቅ ባትችል አትበትናት።
ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም።

ለአስታየት @ethio_merjabot
@B_promotor

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


ዩክሬን በብሪታንያና ፈረንሳይ ስቶርም ሻዶ ሚሳኤል ሩሲያን መደብደብ ጀመረች

አሜሪካ ረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳኤሎችን ለዩክሬን አሳልፋ መስጠቷን ተከትሎ ሁለቱ አገራት ፍቃድ ሰጥተዋል፡፡

በዚህም ዩክሬን ስቶርም ሻዶ በተሰኙ ሚሳኤሎች ሩሲያን ማጥቃት ጀምራለች ተብሏል፡፡

ሩሲያም የእጃችሁን ታገኛላችሁ ስትል እየዛተች ነዉ፡፡

የሩሲያ መንግሥት ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ በሰጡት ምላሽ አገራቸው ዩክሬን ለምትጠቀማቸው ለእነዚህ ሚሳኤሎች ተገቢውን ወታደራዊ ምላሽ ትሰጣለች ብለዋል።

ለዩክሬን ተሰጠ የተባለው ‘ዘ ስቶርም ሻዶ’ የረጅም ርቀት ሚሳኤል ከዚህ በፊት የለንደንና እና የፓሪስ አየር ኃይሎች በባሕረ ሰላጤው አካባቢ በኢራቅ እና በሊቢያ ውስጥ ጥቅም ላይ አውለውታል።

የጦር አውድማ ላይ ሩሲያ የበላይነቷን እያሳየች ትገኛለች። የሩሲያ ወታደሮች የዩክሬንን ግዛቶች እየተቆጣጠሩ ወደፊት በመገስገስ ላይ ናቸው።


የቻናል ማስታወቂያ ‼️

ወቅታዊ ፤ትኩስ መረጃዎችን የሚዘግብ ቻናል 👇👇👇
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0


#የእግዚአብሔር ሰራዊት አለቃ ሆኜ ወዳንተ መጥቻለሁ

“በጎዳናህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላዕክትን ስላንተ ያዝዛቸዋል በእጃቸውም ይደግፉሃል፡፡” ይላል ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት፡፡ ይልቁንም የመላእክት ሁሉ አለቃቸው የሚሆን ቅዱስ ሚካኤል ከእግዚአብሔር ተልኮ በርካቶችን ሲጠብቅ በቅዱስ መጽሐፍ ተመልክተናል፡፡ በየዓመቱ በህዳር በ12 ቀን በዓለ ሲመቱ የሚከበረው ቅዱስ ሚካኤል የዋህ፣ ርህሩህ፣ አዛኝ፣ ለወዳጆቹ ቅርብ፣ የሰው ሁሉ ልጆችን ጠላት በእሳት ሰይፍ መትቶ የጣለው በክንፎቹ ረድኤት የሚጠብቀንም ነው፡፡ “በሰማይ ብርቱ ሰልፍ ሆነ ሚካኤልና መላአክቱም ዘንዶውን ተዋጉት ዘንዶውም አልቻላቸውም። ከዚያም በኃላ በስማይ ቦታ አልተገኘለትም” ተብሎ በራዕይ 12÷7 እንደተጻፈ ዲያብሎስ በትዕቢቱ ከወደቀ በኋላ የመላዕክት ሁሉ አለቃ የሆነው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡

አምላካቻን እግዚአብሔር ወደር የማይገኝለት ኃያል፣ የሚመስለው የሌለ ብርቱ፣ ዘመን የማይቆጠርለት ዘለዓለማዊ ነው፡፡ መላዕክቱን መንፈስ የሚላኩትን የእሳት ነበልባል የሚያደርጋቸው ተብሎ እንደተጻፈ የኃይሉ መገለጫ ከሆኑት አንዱ ናቸው ቅዱሳን መላዕክት፡፡ ይልቁንም የስሙ ትርጓሜ “ማን እንደ አምላክ ማለት የሆነው ታላቁ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በርካታ ድንቅ ስራ ሰርቷል፡፡ በበዓለ ሲመቱም በየዓመቱ ከሕዳር 12 እስከ የአእላፍ መላእ በዓል እስከሚከበርበት ሕዳር 13 ለሰው ልጆች ሁሉ ከአምላካችን ምሕረት ይለምናል፡፡ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ነፍሳትንም ከሲዖል ያወጣል፡፡

ሕዳር 12 እስራኤላውያንን ከግብጽ ባርነት መርቶ ያወጣበትም ቀን ነው፡፡ 430 ዘመን በባርነት ከቆዩባት ምድረ ግብጽ በሙሴ መሪነት ሲጓዙ፣ ግርማ ሌሊቱን በብርሃን አምድ፣ የቀኑን ሐሩር ደግሞ በደመና ጋርዶ ወደ ተስፋይቱ ምድር ያገባቸው እርሱ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ከሙሴ በኋላ እስራኤልን የመራው ነቢዩ ኢያሱም ኢያሪኮን ለመያዝ ሲሰናዳ የመላእክት ሁሉ አለቃቸው የሚሆን የከበረ ገናና መልአክ ቅዱስ ሚካኤል የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ ይዞ ተገለጸለት፡፡ እርሱም በምድር ላይ በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደለት፡፡ ወደ እርሱ ቀርቦም “አንተ ከእኛ ወገን ነህ ወይስ ከጠላቶቻችን?” ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም “አይደለሁም ነገር ግን የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁንም ወደ አንተ መጥቻአለው አለው፡፡ ኢያሱ 5÷13፡፡ የኢያሪኮ ግምብን አፍርሶም ድልን አጎናጽፎታል፡፡

ለሚጠሩት ሰዎች ሁሉ ቅርብ የሆነው ቅዱስ ሚካኤል ዛሬም በዙሪያችን ከቦ ይጠብቀናል፣ ያድነንማል፡፡ ነብዩ ቅዱስ ዳንኤልም “በዚያም ዘመን ለሕዝብ ልጆች የሚቆመው ታለቁ አለቃ ሚካኤል ይነሳል።” እንዲል ሁሌም ጥበቃው ከኛ ጋር ነው፡፡ ከእግዚአብሔር በተሰጠው ቃል ኪዳን ልጆቹን ለመርዳት ቸል አይልም፡፡ ይልቁንም በዱር በገደል ጤዛ ልሰው፣ ድንጋይ ተንተርሰው፣ ዳዋ ለብሰው የሚኖሩትን ገዳማዊያን ዘወትር ይጠብቃቸዋል ጸሎታቸውንም ያሳርጋል፡፡ የእግዚአብሔር ሰራዊት አለቃ ሆኖ ወደ እነርሱ ይመጣል፡፡ ለእነዚህ ገዳማዊያንና ለገዳማቸው እገዛ በማድረግ የመልአኩ ጥበቃና የጸሎታቸው በረከት ተካፋይ እንሁን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish


ከምትሰራበት ቤት ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት እና ገንዘብ ሰርቃ የተሰወረች ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለች

በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ከምትሰራበት ቤት ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት እና ገንዘብ ሰርቃ የተሰወረች ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር መዋሏን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።

ተጠርጣሪዋ ወንጀሉን የፈጸመችው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አያት ዞን 1 ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ነው።

ተጠርጣሪዋ በደላላ አማካኝነት በቤት ሰራተኝነት ከተቀጠረችበት መኖሪያ ቤት በሶስተኛ ቀን ቆይታዋ የግል ተበዳይ ወደ ስራ በሄዱበት ወቅት አጋጣሚውን በመጠቀም በቤቱ ውስጥ የተቀመጠውን የተለያዩ ሀገራት ገንዘብ እንዲሁም የተለያዩ የወርቅ ጌጣጌጥ ሰርቃ ትሰወራለች።

ይህን ተከትሎም የግል ተበዳይ የተፈፀመባቸውን የወንጀል ድርጊት ለመሪ ሉቄ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ያመለክታሉ፡።

ተጠርጣሪዋ የወንጀል ድርጊቱን ከፈፀመች በኋላ የግል ተበዳይ ጋር ከመቀጠሯ በፊት በክፍለ ከተማው ወረዳ 14 አባዶ አካባቢ ለሦስት ወራት ተከራይታው በነበረ ኮንዶሚኒየም ቤት ትደበቃለች።

የፖሊስ አባላት ባደረጉት ክትትል ከሰረቀቻቸው የተለያዩ አልባሳት፣ የሴትና የወንድ ጫማዎች፣ 18 ሺህ የአሜሪካ ዶላርና የህንድ ሩፒ፣ የወርቅና ልዩ ልዩ ጌጣጌጥ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሏን ከክፍለ ከተማው የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

በተጨማሪም ተጠርጣሪዋ በሁለት የተለያዩ ስሞች የነዋሪነት መታወቂያ እንደተገኘባትም ተገልጿል።

ተጠርጣሪዋ በእጇ ላይ የተገኘውን የውጭ አገራት ገንዘብ ከየት ያመጣችው እንደሆነ ፖሊስ እያጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ በተለይ ለEBC DOTSTREAM ገልፀዋል።


#የእግዚአብሔር ሰራዊት አለቃ ሆኜ ወዳንተ መጥቻለሁ

“በጎዳናህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላዕክትን ስላንተ ያዝዛቸዋል በእጃቸውም ይደግፉሃል፡፡” ይላል ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት፡፡ ይልቁንም የመላእክት ሁሉ አለቃቸው የሚሆን ቅዱስ ሚካኤል ከእግዚአብሔር ተልኮ በርካቶችን ሲጠብቅ በቅዱስ መጽሐፍ ተመልክተናል፡፡ በየዓመቱ በህዳር በ12 ቀን በዓለ ሲመቱ የሚከበረው ቅዱስ ሚካኤል የዋህ፣ ርህሩህ፣ አዛኝ፣ ለወዳጆቹ ቅርብ፣ የሰው ሁሉ ልጆችን ጠላት በእሳት ሰይፍ መትቶ የጣለው በክንፎቹ ረድኤት የሚጠብቀንም ነው፡፡ “በሰማይ ብርቱ ሰልፍ ሆነ ሚካኤልና መላአክቱም ዘንዶውን ተዋጉት ዘንዶውም አልቻላቸውም። ከዚያም በኃላ በስማይ ቦታ አልተገኘለትም” ተብሎ በራዕይ 12÷7 እንደተጻፈ ዲያብሎስ በትዕቢቱ ከወደቀ በኋላ የመላዕክት ሁሉ አለቃ የሆነው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡

አምላካቻን እግዚአብሔር ወደር የማይገኝለት ኃያል፣ የሚመስለው የሌለ ብርቱ፣ ዘመን የማይቆጠርለት ዘለዓለማዊ ነው፡፡ መላዕክቱን መንፈስ የሚላኩትን የእሳት ነበልባል የሚያደርጋቸው ተብሎ እንደተጻፈ የኃይሉ መገለጫ ከሆኑት አንዱ ናቸው ቅዱሳን መላዕክት፡፡ ይልቁንም የስሙ ትርጓሜ “ማን እንደ አምላክ ማለት የሆነው ታላቁ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በርካታ ድንቅ ስራ ሰርቷል፡፡ በበዓለ ሲመቱም በየዓመቱ ከሕዳር 12 እስከ የአእላፍ መላእ በዓል እስከሚከበርበት ሕዳር 13 ለሰው ልጆች ሁሉ ከአምላካችን ምሕረት ይለምናል፡፡ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ነፍሳትንም ከሲዖል ያወጣል፡፡

ሕዳር 12 እስራኤላውያንን ከግብጽ ባርነት መርቶ ያወጣበትም ቀን ነው፡፡ 430 ዘመን በባርነት ከቆዩባት ምድረ ግብጽ በሙሴ መሪነት ሲጓዙ፣ ግርማ ሌሊቱን በብርሃን አምድ፣ የቀኑን ሐሩር ደግሞ በደመና ጋርዶ ወደ ተስፋይቱ ምድር ያገባቸው እርሱ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ከሙሴ በኋላ እስራኤልን የመራው ነቢዩ ኢያሱም ኢያሪኮን ለመያዝ ሲሰናዳ የመላእክት ሁሉ አለቃቸው የሚሆን የከበረ ገናና መልአክ ቅዱስ ሚካኤል የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ ይዞ ተገለጸለት፡፡ እርሱም በምድር ላይ በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደለት፡፡ ወደ እርሱ ቀርቦም “አንተ ከእኛ ወገን ነህ ወይስ ከጠላቶቻችን?” ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም “አይደለሁም ነገር ግን የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁንም ወደ አንተ መጥቻአለው አለው፡፡ ኢያሱ 5÷13፡፡ የኢያሪኮ ግምብን አፍርሶም ድልን አጎናጽፎታል፡፡

ለሚጠሩት ሰዎች ሁሉ ቅርብ የሆነው ቅዱስ ሚካኤል ዛሬም በዙሪያችን ከቦ ይጠብቀናል፣ ያድነንማል፡፡ ነብዩ ቅዱስ ዳንኤልም “በዚያም ዘመን ለሕዝብ ልጆች የሚቆመው ታለቁ አለቃ ሚካኤል ይነሳል።” እንዲል ሁሌም ጥበቃው ከኛ ጋር ነው፡፡ ከእግዚአብሔር በተሰጠው ቃል ኪዳን ልጆቹን ለመርዳት ቸል አይልም፡፡ ይልቁንም በዱር በገደል ጤዛ ልሰው፣ ድንጋይ ተንተርሰው፣ ዳዋ ለብሰው የሚኖሩትን ገዳማዊያን ዘወትር ይጠብቃቸዋል ጸሎታቸውንም ያሳርጋል፡፡ የእግዚአብሔር ሰራዊት አለቃ ሆኖ ወደ እነርሱ ይመጣል፡፡ ለእነዚህ ገዳማዊያንና ለገዳማቸው እገዛ በማድረግ የመልአኩ ጥበቃና የጸሎታቸው በረከት ተካፋይ እንሁን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444


ሰላሌ😭😭😭

ሰላሌ አዝናለች😭😭

ከዛ መንደር ያየነውን ቪዲዮ በእውነት በእውነት እጅግ ያሳዝናል ልብ ይሰብራል ምን ያህል ብንጨካከን ነው ግን።

እውን ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ያለነው ከቅርብ ጊዜ ወዲ የምንሰማቸውና የምናያቸው ዜናዎች ሁሉ ልብ ይሰብራሉ።

ቪድዮው እዚ መለጠፍ ለኛ ለሸገሮች በጣም ከባድ ሆኖብናል ከልብ እናዝናለን።

እውነት ለመናገር ቪዲዮውን ለማየት አቅም ያሳጣል።

የሚመለከተው አካል እነዚህ አጥፊዎችን ይዞ ለህግ እንዲያቀርብ በትህትና እንጠይቃለን ከሸገር ፕረስ።

በተጫማሪም በአሰቃቂ ሁኔታ ለተገደሉ ወገኖቻችን ሁሉ ነብስ ይማር ነፍሳቸው በሰላም ትረፍልን።

ያሳዝናል😭😭😭😭

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news







7.7k 0 12 18 83

የባይደን አስተዳደር የብሪታንያ የረዥም ርቀት ማዕበል ጥላ ሚሳኤሎችን ወደ ሩሲያ ገብተው ጥቃቶች እንዲፈፅሙ ፈቀደ - ዘ ታይምስ


#ከዓይን ሲርቅ የሚደርቀው እንቁላል…


“ሐልዎተ እግዚአብሔር” የእግዚአብሔርን መኖር ከምናውቅባቸው ነገሮች አንዱ ፍጥረታትን መመልከት እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አባቶቻችን ያስተምሩናል፡፡

ይህ ሁሉ ስፍር ቁጥር የሌለው ፍጥረት አስገኚ፣ ፈጣሪ ባይኖረው ከዓለም ጅማሬ እስካለንበት ዘመንና እስከ ዓለም ፍጻሜ ስርዓቱን ጠብቆ ባልኖረም ነበር ይሉናል፡፡

ያውም ከድንቅ ተፈጥሯዊ ባሕርዩ ጋር፡፡ በዚህ ድንቅ ተፈጥሯዊ ባህርይ ከሚታወቁት ፍጥረታት አንዷ ግዡፏ የአእዋፋት ዝርያ ሰጎን ናት፡፡

ሰጎን እንቁላል ከጣለች በኋላ እስኪፈለፈል ድረስ አይኗን ከእርሱ ላይ አታነሳም፡፡ ምግብ ፍለጋ ስትሔድም ወንዱን አስጠብቃ ነው፡፡ አይኗን አንስታ ረጅም ጊዜ ከቆየች ይደርቅና አይፈለፈልላትም፡፡

የመፈልፈያ ጊዜያቸው ሲደርስም ከውጪ ሆና ቅርፊቱን ታንኳኳለች፣ እነርሱም ከውስጥ ሆነው ያንኳኳሉ፡፡ ድምጽ ታሰማቸዋለች፣ እነርሱም መልሰው ድምጽ ያሰማሉ፡፡ ይህን ጊዜ እንቁላሉን ሰብራ ታወጣቸዋለች፡፡

ስታንኳኳ ካላንኳኩ፣ ድምጽ ስታሰማቸው ድምጽ ካላሰሙ ጊዜያቸው ገና ነው አሊያም ሞተዋል፣ ወይም እንቁላሉ ባዶ ነው ብላ ስለምታስብ ትታቸው ትሔድና በዚያው ይደርቃል፡፡


እኛም እንደ ጫጩቶቹ ነን፡፡ አባታችን እግዚአብሔርም የከከበበን የኃጢአት ቅርፊት ሰብሮ የሚያወጣን ዘወትር አይኖቹን ከኛ የማያነሳ ጠባቂያችን ነው፡፡

ይህ እንዲሆን ግን ቅርፊቱን ሲያንኳኳ እኛም በኃጢአት ውስጥ እንኳን ብንሆን አድነኝ ብለን መልሰን እናንኳኳ፤ ድምጽ ሲያሰማ፣ ሲጠራን፣ ተመለሱ ሲለን የእሺታ፣ የመዳን ፍላጎት ድምጽ እናሰማው፡፡

አዎ ቅርፊቱን አንሳልኝ መውጣት፣ መራመድ፣ በጽድቅ ስራ መብረር እፈልጋለሁ እንበለው፡፡ በዘመነ ስጋዌው በዚህ ምድር ሲመላለስ ፈውስ ፈልገው ወደርሱ የሚመጡትን “ልትድን ትወዳለህን? ብሎ ይጠይቅ የነበረው በፈቃዳችን ስለሚሰራ ነው፡፡

መዳን፣ እንደ ሰጎኗ ጫጩቶች ከቅርፊቱ መውጣት፣ በበጎ ምግባር፣ በትሩፋት መጓዝ የምንችልበት እድል ተሰጥቶናል፡፡

ይህን ድንቅ ምስጢር የሚገልጹልን የመዳንን መንገድ እንድንከተል በጸሎታቸው የሚያስቡንን፣ የኃጢአት ቅርፊቷን የምትጭንብንን ይህቺን ዓለም ንቀው የመነኑትን ገዳማውያንና ቅዱሳት መካናትንም እናስብ፡፡ ጥሪውን እንድንሰማ፣ ለማንኳኳቱም መልስ እንድንሰጥ ይርዳን፡፡


ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish


ሱዳን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውሳኔን አትቀበልም ሲሉ  ጀነራል አብደል ፈታህ አልቡርሃን ተናገሩ

የሉዓላዊው ምክር ቤት ፕሬዝደንትና የሱዳን ጦር ሃይሎች ዋና አዛዥ ጄኔራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን፣ የመንግስታቱ ድርጅት በሱዳን ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔ በራሺያ ድምፅን በድሞፅ የመሻር መብት ተጠቅመው የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔን ውድቅ አድርገውታል።

በፖርት ሱዳን በተካሄደው የኤኮኖሚ ኮንፈረንስ ላይ ንግግር ያደረጉት አል-ቡርሃን የውሳኔ ሃሳቡን ለፈጣን የድጋፍ ሰጪ ሃይሎች የጦር መሳሪያ በማቅረብ ረገድ የውጭ ተዋናዮችን ሚና ባለመቀበል ተችተዋል። አል-ቡርሃን ሱዳን ከጦርነቱ በኋላ ከዓለም አቀፍ ተዋናዮች ጋር የሚኖራት ግንኙነት በግጭቱ ወቅት ባላቸው አቋም እንደሚወሰን አጽንኦት ሰጥተዋል።

አርኤስኤፍ ቀደም ሲል በጅዳ የተካሄደውን የተኩስ አቁም ስምምነት እንደገና ለማስታጠቅ እና የከተሞችን ከበባ ለማጠናከር ውሏል ሲሉ ከሰዋል። ጦር አዛዡ በውስጥ በኩል መፍትሄ ለመፈለግ እና የውጭ ጣልቃ ገብነትን እንደሚቃወሙ ገልፀው ጦራቸው በሱዳን ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች ላይ ድል ለመጎናፀፍ መቃረቡን ተናግረዋል። አል-ቡርሃን የተኩስ አቁም ስምምነትን ለመቀበል ቅድመ ሁኔታዎችን ዘርዝረዋል።

የአርኤስኤፍ ኃይሎች ከተያዙ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ለቀው እንዲወጡ እና በተመረጡ ካንቶን ቦታዎች እንዲሰበሰቡ አሳስበዋል።  ይህም የሰሜን ዳርፉር ዋና ከተማ የሆነችውን ኤል ፋሸር ከበባ ለማንሳት እና የዜጎችን እና የዕርዳታ አቅርቦት ነጻ እንቅስቃሴን ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው ብለዋል። "ሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ከገባችባቸው አካባቢዎች በሙሉ መውጣትን የማያካትት ማንኛውንም የተኩስ አቁም ወይም ጦርነት ማቆም አትቀበልም" ሲለ አል-ቡርሃን ተደምጠዋል።

መንገዶችን ለመክፈት እና ሰብአዊ ተደራሽነትን ለማሳለጥ አርኤስኤፍ በተለዩ ቦታዎች መሰብሰብ እንዳለበትም አሳስበዋል። የአል-ቡርሃን አስተያየት የሱዳን መንግስት ግጭቱን በራሱ መንገድ ለመፍታት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያጎላ ሲሆን ይህም የአለም አቀፍ ጣልቃ ገብነትን አለመቀበል እና በፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች ላይ ወታደራዊ ድልን ለማምጣት ትኩረት የሰጠ ነው ተብሎ ታምኖበታል። (dagu)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news


መረጃ ‼️

በምግብ መመረዝ ምክንያት በሚል ጎሮ አንደኛ ትምህርት ቤት የሚማሩ ተማሪዎች ህመም አጋጥሞቸዉ ከደቂቃዎች በፊት በአንቡላንስ ወደ ጤና ጣቢያ መወሰዳቸዉን አንኳር መረጃ ሰምታለች፡፡

ትምህርት ቤቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምገባ ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆኑ ይታወሳል ፡፡

ህመሙ ቀለል ያለ እና ተማሪዎቹ ከጤና ጣቢያ መጠነኛ ህክምና ተደርጎላቸዉ እየተመለሱ መሆኑ ሰምተናል ፡፡፡


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
“የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ሥርዓት በከፍተኛ ደረጃ እየሰፋ መጥቷል”_ በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሠረተ ልማት ጉዳዮች ዋና ሥራ አስፈፃሚ

በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሠረተ ልማት ጉዳዮች ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ሥርዓት በከፍተኛ ደረጃ እየሰፋ መምጣቱን ጠቅሰው ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ተቋማቱ ከ2 ዩኒቨርሲቲዎች ወደ 51 የመንግስት እና 315 የግል ተቋማት ማደጋቸውን እንዲሁም የተማሪዎች ምዝገባ ወደ 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ከፍ ማለቱን ገልጸዋል።

ነገር ግን የትምህርት ጥራት ማሽቆልቆሉን አምነው፣ ተቋማቱ ብቁ ተመራቂዎችን ለመፍጠር፣ችግር ፈቺ የሆኑ ተግባራዊ እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ጥናትና ምርምሮችን ለማድረግ እንዲሁም ውጤታማ አስተዳደርን ለማስፈን እየሰሩ ነው ብለዋል።

አክለውም እነዚህን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ በ2011 ዓ.ም የወጣው የትምህርት ፍኖተ ካርታ የዩኒቨርሲቲዎች ራስን በራስ ማስተዳደርን እንደ ቁልፍ ማሻሻያ ጠቁመዋል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም በአዋጅ ቁጥር 1294 መሠረት የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ በመሆን የሁለት ዓመት ሽግግር ያደርጋል ተብሏል።

በሚቀጥለው ዓመትም 10 ተጨማሪ ዩኒቨርሲቲዎች የራስ ገዝ አስተዳደር ማዕቀፉን እንዲቀላቀሉ እቅድ መያዙን አመልክተዋል።

እነዚህ ማሻሻያዎች ከፍተኛ መዋቅራዊ ለውጦችን እና በባለድርሻ አካላት መካከል የትብብር ጥረቶችን ይጠይቃሉ ብለዋል።

ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ይህን የገለጹት የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጋር ዘጠኝ የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ራስ ገዝ ለማድረግ የሚያስችል የግማሽ ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ስምምነት ባደረገበት ወቅት ነው።

!


የቻናል ማስታወቂያ ‼️

ወቅታዊ ፤ትኩስ መረጃዎችን የሚዘግብ ቻናል 👇👇👇
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0


አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ከትላንት ጀምሮ መሾማቸው ተሰምቷል

አምባሳደር ሽፈራው ወደ ህብረት ስራ ኮሚሽነርነት እስከ ተሾሙበት ጊዜ ድረስ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣንን በዋና ዳይሬክተርነት ሲመሩ ቆይተዋል።

የኢትዮጵያ ኅበረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት ጌታቸው መለሰ (ዶ/ር) ከወር በፊት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል።

አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ፤ ኢህአዴግ ከመፍረሱ በፊት በተለያዩ የክልልና የፌዴራል የስልጣን እርከኖች ላይ ኢህአዴግ ፈርሶ ብልፅግና ከመጣም በኃላ በተለያዩ የስልጣን እርከኖች ላይ ተሹመው እየሰሩ ናቸው።

በሌላ በኩል ፤ በአምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ምትክ አህመድ አብተው (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ከትላንት ጀምሮ እንደ ተሾሙ ሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ዘግቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news


ዘመናቸውን የጨረሱ የምርጫ ቦርድ አመራሮች ከሃላፊነታቸው ሊነሱ ይገባል” ገዳ ቢሊሱማ ፓርቲ

ዘመናቸውን የጨረሱ የምርጫ ቦርድ አባላት ከሃላፊነት ሊነሱ ይገባል ሲል ከሰሞኑ ፍቃዱ የተሰረዘው ገዳ ቢሊሱማ ፓርቲ ከሷል፡፡

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የፓርቲዎችን ፍቃድ በመሰረዝ የሰላማዊ ትግል በርን እየዘጋ ነው ያለው ፓርቲው፣ ይህ ደግሞ ሆን ብሎ የሚከናወን ነው ሲል አብራርቷል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news


ዛሬ የዓለም የጋዜጠኞች ቀን ነው።

የጋዜጠኝነት ውሃ ልኮች እንኳን አደረሳችሁ።

ጋዜጠኛ ምስጢረሥላሴ ታምራት
ጋዜጠኛ ኃይለገብርኤል ታደሰ
ጋዜጠኛ ሙሀመድንጉስ አብዱ

በአጠቃላይ የአሻም ቴሌቭዥን ጋዜጠኞችና ማኔጅመንት
አባላት በሙሉ ፦

ነጭ ነጯን ፣ እውነተኛ መረጃ በማስረጃ እያስደገፋችሁ
የተለያዩ ጫናዎችን ተቋቁማችሁ እዚሁ ሀገራችሁ ላይ ተቀምጣችሁ በልበ ሙሉነት የሕዝብን ብሶት ስለምትተነፍሱ
እና ለታመናችሁለት ሙያ ለደሞዝ ሳይሆን ለሕሊናችሁ ስለምትሰሩ እንኳን ለዓለም የጋዜጠኞች ቀን አደረሳችሁ።

ጊዜያችሁን በማይመለከተን የእስራኤልና የሀማስ ፣
የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት በመዘብዘብ ስለማታውሉት
ክብር ይገባችኋል።

ወደፊት የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሸልማችኋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ውለታውን የሚረሳ አይደለም።

ጋዜጠኛ አቤል ነኝ አክባሪያችሁ
ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ !

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.