#... ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ
በዕለተ ሥቅለተ ክርስቶስ ካሕናት አባቶቻችን የዘጠኝ ሰዓት ስግደት ሲሰገድ “ኦ ዘጥዕመ ሞተ በስጋ” “በስጋው ሞትን የቀመሰ ኢየሱስ ክርስቶስ” እያሉ ልብን በሚያሳዝን ዜማ ያዜማሉ፡፡ በመለኮቱ ሕያው ሲሆን በስጋው ግን ሞትን ቀመሰ፡፡ የአዳምን ሞት በሞቱ ሊሽር መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን በገዛ ፈቃዱ አሳልፎ ሰጠ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ክርስቲያኖች ሲጽፍ “ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን… አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን” ይላል፡፡
የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ቄርሎስም “ለቤተ ክርስቲያን ስትል በአደባባይ በጥፊ የተመታህ አቤቱ ይህን ማድረግህ እርስዋን በከበረ ደምህ ትቀድሳት ዘንድ ነው፡፡ ለእርስዋ ሲል ታሥሮ መጎተት የቻለ የበደለውም በደል ሳይኖር፣ ርኩስ ምራቅን ሲተፋበት የታገሠ መድኃኔ ዓለም በእንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ” በማለት ገለጸው፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር ሰው ሆኖ እንደሚያድነን በመጀመሪያ ለአዳም ቃል ገባለት፡፡ ከዚያም በነቢያት ትንቢት አስነገረ፡፡ በስጋ በተገለጠ ጊዜም የሰቀሉትና የገደሉት አይሁድ ሳይቀሩ እንዲናገሩ አፋቸውን አስከፈታቸው፡፡ አልአዛርን ለአራት ቀናት በመቃብር ከቆየ በኋላ ከሙታን ሲያስነሳው ከአይሁድ ወገን ብዙዎች አመኑ፡፡ አንዳንዶች ግን ወደ ፈሪሳውያን ሄደው ኢየሱስ ያደረገውን ነገሯቸው፡፡
በዮሐንስ 11 እንደተጻፈው ከተአምራቱና ከትምህርቱ የተነሳ ሕዝቡ ሁሉ ትቷቸው እንዳይሔድ የፈሩት አይሁድ ሲማከሩ “በዚያች ዓመት ሊቀ ካህናት የነበረ ቀያፋ የሚሉት ከእነርሱ አንዱ። እናንተ ምንም አታውቁም፤ ሕዝቡም ሁሉ ከሚጠፋ አንድ ሰው ስለ ሕዝቡ ይሞት ዘንድ እንዲሻለን አታስቡም አላቸው። ይህንም የተናገረ ከራሱ አይደለም÷ ነገር ግን በዚያች ዓመት ሊቀ ካህናት ነበረና ኢየሱስ ስለ ሕዝቡ ሊሞት እንዳለው ትንቢት ተናገረ፡፡ ስለ ሕዝቡም ሁሉ አይደለም÷ ነገር ግን የተበተኑትን የእግዚአብሔርን ልጆች ደግሞ በአንድነት እንዲሰበስባቸው ነው እንጂ።” ተብሎ ተጽፏልና፡፡ የቀድሞው የግብጽ ኦርቶዶክሳውያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ “ሺኖዳ እኛ ወደ እርሱ መውጣት ሲያቅተን መድኃኔ ዓለም ወደኛ ወረደ” በማለት ይገልጹታል፡፡
አምላክነትን ሲሻ የወደቀ የሰው ልጅን የወደደውን አምላክነት ያገኝ ዘንድ የሰውን ባሕርይ ተዋህዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ፡፡ ከኛ በነሳው ስጋም ወደ ሰማይ አረገ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይለናል፡፡ “ሔዋንን ዲያብሎስ አሳታት የሞት ምክንያት የሚሆን ቃልን ወለደች፡፡ ድንግል ማርያም ግን መልአክ በአበሠራት ጊዜ ሁሉን ወደ ዘለዓለም ሕይወት የሚመራ አካላዊ ቃልን በሥጋ ወለደች፡፡” በማዳኑ ስራ ውስጥ የቅድስት ድንግል ማርያም ድርሻ ታላቅ ነው፡፡ “የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ፡፡” ሲል ቅዱስ ጳውሎስም ለገላትያ ክርስቲያኖች ጽፏል፡፡ ገላ 4÷4 ስለፍጹም የሰው ልጆች ፍቅር መድኃኔ ዓለም “በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፣ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ” ፊልጵ 2÷8 ተብሎ እንደተጻፈ፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444