ባለው የፀጥታ ሁኔታ ለምዕራብ ትግራይ ዞን መድኃኒት ማሰራጨት አልተቻለም ተባለ።
ለምዕራብ ትግራይ ዞን በተለይ ለማይፀብሪ ወረዳ መድኃኒት ለማሰራጨት መቸገሩን በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሽሬ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ለጣቢያችን አስታውቋል።
የፅ/ቤቱ ሃላፊ አቶ ሙሌ አብርሃ ፤ መድኃኒቶችን ለሶስት ዞኖች የምናሰራጭ ቢሆንም ለምዕራብ ትግራይ ግን ማድረስ አልቻልንም ብለውናል።
በተደጋጋሚ ጥያቄዎች ቢመጡም በእኛ በኩል የሚቻል ባለመሆኑ በጎንደር ቅርንጫፍ በኩል እንዲደርሳቸው ለማድረግ ተሞክሮ ነበር ብለዋል።
ከዚህ ቀደም ከወረዳው ሁለት ጊዜ መድኃኒት እንድንሰጥ ተጠይቀን ነበር የሚሉት ሃላፊው፤ ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻላቸው ጥያቄያቸውን መመለስ አልተቻለም ነው ያሉት።
የወባም ሆነ የኤችአይቪ መድኃኒቶች አሁን ላይ ችግር የለብንም ያሉት ሃላፊው፤የብድር ሁኔታ ግን አስቸጋሪ ሆኖ ቀጥሏል ብለውናል።
በብድር መድኃኒቶችን ወስደው ፤ ብድራቸውን ያልጨረሱ ስለመኖራቸውም አንስተዋል።
Ethio Fm
@ethio_mereja_news