የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ "ትእዛዝ አልቀበልም አልፈፅምምየ በማለት የአንድ ቡድን ወታደራዊ ክንፍ ሆኖአል ሲሉ አሳወቁ።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት ፤ " በቢሮው ስም የቀረበው መግለጫ የአንድ የጊዚያዊ አስተዳደሩ አካል ሳይሆን የአንዱ ቡድን ወታደራዊ ክንፍ መሆኑ በግልፅ የሚያሳብቅና የተፈጠረውን ችግር የሚያባብስ ነው " ብሎታል።
ትናንት መጋቢት 1/2017 ዓ.ም ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ በሦስት ከፍተኛ የሰራዊት አመራሮች የጣሉት ጊዚያዊ እግድ ተከትሎ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመሩት ህወሓት " እገዳው መሰረተ ቢስ እና የማይተገበር " በማለት ውድቅ ለማድረግ ጊዜ አልወሰደበትም።
ዛሬ ማክሰኞ ጠዋት ደግሞ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጊዚያዊ እግድ ሙሉ በሙሉ በመፃረር ባወጣው መግለጫ ፤ በግልባጭ የተፃፈለትን ትእዘዛዝ እንደማይቀበል በመግለፅ " የህግ ማስከበር እርምጃው " ይቀጥላል ብሏል።
የሰላምና ፀጥታ ቢሮ መግለጫ ተከትሎ ከመቐለ በ115 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው የዓዲግራት ከተማ በሰራዊት የታገዘ መፈንቅለ ስልጣን መካሄዱን ለማወቅ ተችሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ዛሬ ጠዋት ወደ ምስራቃዊ ዞን የሰላምና የፀጥታ ሃላፊ ደውሎ " ከቀበሌ የተወጣጡ ጥቂት ደጋፊዎች በሰራዊት በመታገዘ ጊዚያዊ አስተዳደሩ የሾማቸው ከንቲባ ሲገለገሉት የነበረው ፅሕፈት ቤት በመስበር በደብረፅዮኑ ህወሓት ለተመረጡት ከንቲባ አስረክበዋል " ብለውታል።
በትግራይ ያለው የፓለቲካና የፀጥታ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢና ተለዋዋጭ ደረጃ ላይ ይገኛል።
@ethio_mereja_news