ከጎረቤቱ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት የፈላ ውሀ ሰውነቷ ላይ በመድፋት ከባድ የአካል ጉዳት ያደረሰው ግለሰብ በ7 ዓመት ከ5 ወር ፅኑ እስራት ተቀጣ
ተከሳሽ ሀብታሙ ተክለማሪያም ወንጀሉን የፈፀመው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው ኮንጎ ሠፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።
የግል ተበዳይና ተከሳሽ በአንድ ግቢ ውስጥ የሚኖሩ ሲሆን በሁለቱ ግለሰቦች መካከል በንግግር የተፈጠረን አለመግባባት ቂም በመያዝ የግል ተበዳይ ግቢ ውስጥ ቁጭ ብላ ስራዋን እየከወነች ባለችበት ወቅት ተከሳሽ በጀርባዋ በኩል በመሄድ የፈላ ውሀ ደፍቶባት ከባድ የአካል ጉዳት በማድረሱ በቁጥጥር ስር መዋሉን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የኮልፌ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አስታውቋል፡፡
ፖሊስ የተፈፀመውን ወንጀል መነሻ በማድረግ ተገቢውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ በማደራጀት በዐ/ህግ በኩል ክስ እንዲመሰረትም አድርጓል፡፡
የወንጀል ምርመራ መዝገቡን ሲከታተል የቆየው በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ፈጣን ችሎት የካቲት 25 ቀን 2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ሀብታሙ ተክለማሪያም በ7 ዓመት ከ5 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል፡፡
የግል ተበዳይ በተፈፀመባት ወንጀል ለከባድ የአካል ጉዳት መዳረጓን ገልፃ ተከሳሽ በህግ ፊት ቀርቦ ተገቢው እርምጃና ቅጣት የተላለፈበት መሆኑ እንዳስደሰታት ገልፃለች።
@ethio_mereja_news