በዛሬው ዕለት በሳይንስ ሙዚየም በተከፈተው የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ እና ቀጣይ ውጥኖችን የተመለከተ የአውደ ርዕይና አውደ ጥናት መርሃ ግብር ላይ ኩባንያችን በመሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡
በመርሃ-ግብሩ የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮች፣ የከፍተኛ ትምህርት ኃላፊዎች እና ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል፡፡
ኩባንያችን በዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የገነባቸውን መሰረተ ልማቶችና የዲጂታል ሶሉሽኖችን አውደ ርዕይ ከማቅረብ ባሻገር በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የተገኙ ስኬቶች እና በቀጣዩ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ላይ በተደረገው ውይይት ተሳትፏል።
ዋና ስራ አስፈጻሚያችን የዲጂታል ኢትዮጵያን እውን የማድረግ ራዕይ ሰፊ መሆኑን እና የተለያዩ ዘርፎችን እና የልማት አቅጣጫዎችን በቴክኖሎጂ በማስታጠቅና በመደገፍ በዲጂታል የበቃችና ተወዳዳሪ ሀገር የማፍራት እንጂ ጥቂት አገልግሎቶችን ዲጂታል በማድረግ የታጠረ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡
አክለውም ዲጂታል ኢትዮጵያ የአሰራር ስርአት፣ ፖሊሲና ፕሮሲጀር፣ የቀረበውን ቴክኖሎጂ የሚረዳ፣ የሚተነትን እና ቴክኖሎጂውን ተጠቅሞ ችግር የሚፈታ ማህበረሰብና አመራር መገንባት እንደሚያስፈልግ እንዲሁም ቴክኖሎጂ ማለትም ውስን የሆነውን ሀብታችንን በቅንጅት በመጠቀም መሰረተልማቶችን በመጋራት የኢንቨስትመንት ፍላጎቶችን መቀነስ እንደሚቻል አብራርተዋል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም ግዙፍ አስቻይ መሰረተ ልማቶች የገነባ በመሆኑ ዲጂታል መንግስት እና ኢ-ኮሜርስን እውን ለማድረግ የሚያስችል መደላደል መፍጠሩን የገለጹ ሲሆን፣ ኩባንያችን የ 5 ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠናን ከኢንተርኔት ክፍያ ነጻ ማድረጉን በማስታወስ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የዲጂታል ኢትዮጵያን ጉዞ እንዲቀላቀል ጥሪ አቅርበዋል፡፡