የቴሌብር አገልግሎት በ2017 የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት 5 ሚሊዮን ደንበኞች በማፍራት አጠቃላይ የአገልግሎት ተጠቃሚዎችን ቁጥር 51.5 ሚሊዮን በላይ በማድረስ የዕቅዱን 99.8% አሳክቷል፡፡
በግማሽ ዓመቱ በቴሌብር 1.03 ትሪሊዮን ብር የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ዝውውር የተከናወነ ሲሆን፣ እስካሁን ድረስ በአጠቃላይ 3.58 ትሪሊየን የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ በኢኮኖሚው ውስጥ ማንቀሳቀስ ተችሏል፡፡
ይህም የገንዘብ ዝውውርን ቀላል እና ቀልጣፋ በማድረግ አካታችና ተደራሽ የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት በማስቻል ላይ ነው፡፡
የቴሌብር አገልግሎት በዓለም አቀፉ የጥራት ደረጃ ማረጋገጫ ተቋም የ ISO 27001:2022 እና የ PCI DSS V4.0.1 የደኅንነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀቶች ያገኘ ሲሆን ይህም የቴሌብር ፋይናንሻል እና ክፍያ አገልግሎቶቻችን አስተማማኝ እና ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃዎችን ያሟሉ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው፡፡
የቴሌብር አገልግሎት ለማኅበረሰባችን ሁለንተናዊ ለውጥና መሻሻል ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ከመሆኑ ባሻገር ትርጉም ያለው ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ የፋይናንስ አገልግሎችን ማለትም የሞባይል አነስተኛ ብድር፣ የቁጠባ አገልግሎትና ተያያዥ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን እያቀረበ ይገኛል፡፡
ውድ የቴሌብር ደንበኞቻችን፣ አጋሮቻችን እና የኩባንያችን ቤተሰቦች በስኬታችን ጉዞ አብሮነታችሁ ስላልተለየን ከልብ እናመሰግናለን!
ለሙሉ ሪፖርቱ https://bit.ly/40RlnYV ይጫኑ
#telebirr #Ethiotelecom #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia