✅በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሲሚንቶ ፋብሪካ የተመሠረተው በ1928 ዓ.ም በጣሊያኖች ሲሆን፣ በዓመት 60 ሺሕ ቶን የማምረት አቅም ነበረው። ፋብሪካው "ድሬደዋ ኖራ እና ሲሚንቶ ፋብሪካ" ቢባልም፣ ከጣሊያንኛ በመዋስ በይበልጥ የሚታወቀው "ሴሜንቴሪያ" ወይም "ሼሜንቴሪያ" እየተባለ ነበር (በጣሊያንኛ ቃሉ "ሲሚንቶ ማምረቻ" ማለት ነው)። ይህ የሀገራችን ቀዳሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ ወደ ግል ይዞታ ሲዞር፣ "ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ" የሚለውን መጠሪያ ይዞ ቀጠለ። ወደ 90 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ ያህል፣ በአገር ግንባታ ውስጥ ቁልፍ ስፍራ ይዞ ቀጥሏል።
አሁን #ናሽናል_ሲሚንቶ አ.ማ በቀን 3,500 ቶን ክሊንከር የማምረት አቅም ያለው ሲሆን፣ እኅት ኩባንያው #ለሚ_ናሽናል_ሲሚንቶ ደግሞ በቅርቡ ሥራ ሲጀምር በቀን 10 ሺሕ ቶን ክሊንከር የማምረት አቅም ይኖረዋል።
© East Africa Holding
https://t.me/ethioengineers1
አሁን #ናሽናል_ሲሚንቶ አ.ማ በቀን 3,500 ቶን ክሊንከር የማምረት አቅም ያለው ሲሆን፣ እኅት ኩባንያው #ለሚ_ናሽናል_ሲሚንቶ ደግሞ በቅርቡ ሥራ ሲጀምር በቀን 10 ሺሕ ቶን ክሊንከር የማምረት አቅም ይኖረዋል።
© East Africa Holding
https://t.me/ethioengineers1