ምስጢራዊ ምድር.....#share
*ተወደደም፥ተጠላም የዓለም መፈጠሪያና መገኛ የሚገኘው ኢትዮጵያ በተለይም አማራ ክልል ውስጥ ነው።እንዴት፣ለምን ለምትሉን እልፍ ማስረጃዎች አሉን።
1.ከኤዶም እየወጣ ገነትን ከሚያጠጡ ወንዞች መካከል ሁለተኛው ግዮን ነው።ግዮን ወይንም አባይ የኢትዮጵያን ምድር [7] ጊዜ ይከብባል።የሚያበራ እና የሚያብረቀርቅ ዕንቁም ይገኝበታል። (ዘፍ 2፥13) አዳም የተፈጠረው የግዮን ወንዝ ከሚወጣበት ኤዶም ሲሆን ግዮን ደግሞ መነሻው ጎጃም ሰከላ ውስጥ ነው።
2.ኖህ ከማየ አይኅ የጥፋት ውኃ ልጆቹ፣ሚስቱና የልጆቹ ሚስቶች የዳኑት በመርከብ ነው።የኖኅ መርከብ ማየ አይኅ መጉደል ሲጀምር በ7ኛ ወር ከወሩም በ27ኛው ቀን በአራራት ተራሮች ላይ ተቀመጠች።የኖኅ መርከብ ሐመር ያረፈችበት ስሙ ሉባር ተራራ ይባላል።አራራት ተራራ ደግሞ የሚገኘው ከዚሁ ጣና ውስጥ ነው።ኖኅ መርከቧ በአረፈችበት አራራት (ዘጌ) አካባቢ ወይን ሲተክል ኖረ። አካባቢውን ሳይለቅ ከጥፋት ውኃው በኋላ 350 ዓመት ኖረ።በኋላም የተቀመጠው በእንተላ፣በአይዋርካ፣በሽሌ፣በአይከል ቀሪ ዘመኑን የገፋ ሲሆን ጭልጋ ሳለ ሚስቱ እሜቴ አይከል አረፈች።የኖኅ ሚስት እሜቴ አይከል የተቀበረችው ጭልጋ ላይ ነው።በዚህም የጭልጋ ዋና ከተማ በስሟ አይከል ተባለች።ጭልጋ የአራራት ተራራ አዋሳኝ መሆኑ ይታወቃል።
3.ከእሜቴ አይከል እረፍት በኋላ ኖኅ ጎንደር ላይ ብዙ ዘመን ፈጣሪውን እያመሰገነ እየቀደሰ ኖረ።በ950 ዓ.ዓ ኖህ ሲሞት እዛው ጎንደር ላይ ተቀበረ።መቃብሩ ላይ ምንጭ ፈልቆ በርካታ ሰዎችን ይፈውስ ነበር።ከዚያም ለኖህ መታሠቢያ ይሆን ዘንድ አምላክ በቤተመንግስት አሳቦ የኖህ የመቃብር ሐውልት እንዲታነጽ ፈቀደ።ይህም በኋለኛው ዘመን በንጉሥ ፋሲለደስ የታነጸው የፋሲል ግንብ ነው።
4.በሌላው ዓለም በየትኛውም ስፍራ ወይም ምድር በተባለችው ፕላኔት ላይ በየትኛውም አገርና አህጉር የማይገኙ በኖኅ መርከብ ውስጥ ከነበሩት 7ቱ አጥቢ እንስሳት እንደ ዋሊያ፣ቀይ ቀበሮ፣ጭላዳ ዝንጀሮ የመሳሰሉት እና 13ቱ አእዋፋት የሚገኙት ከኢትዮጵያ 1ኛ ከአፍሪካ 4ተኛ ደረጃ ላይ በተቀመጠው የከፍታ መጠኑ 4620 ሜትር በሆነው በራስ ደጀን ተራራ ነው።ደጀን ተራራ በ1970 ዓ.ም.በዩኔስኮ አማካኝነት በአለም የቅርስ መዝገብ ላይ ተመዝግቧል።
5.ሊቀ ነብያት ሙሴን የአመራርነት ጥበብ የተማረው ከአማራ ካህን ዮቶር (ራጉኤል) ነው። ልጁንም ሲጳራ አግብቶ አልአዛር እና ጌርሣም የሚባሉ ልጆችንም ወልደዋል። መሴ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ያረፈው በጥንቱ በጌምድር ግዛት ምድያም ነው። ምድያም በዛሬው አማራ ሳይንት ውስጥ መደጊም ተብሎ የሚጠራው ቦታ ነው።
በግ ማርባት በምድያም (በቤጌምድር) ምድር የተለመደ ነው።የአማራ ክፍል የሆነው በጌምድርም የበግ ሀገር የተባለው በግ በማርባት ስለሚታወቅ ነው።በጌምድር ወይንም ሽሜ የአማራ ሀገር ነበር።እስከ ተድባባ ማርያም ድረስ በጌምድር ይባል ነበር።በታሪከ ነገሥት "ወዘዐምሐራ ወዘበጌምድር"ይለዋል።ምድያም የሚባል ቦታ በጂዎግራፊያዊ ማስረጃዎች በሲና ሰርጥ ደቡባዊ ክፍል ይገኛል።ይኼም አካባቢ በሲና ተራራ አጠገብ በመሆኑ ግመል እንጅ በግ ሊያረባ አይችልም።
6.የሌዋዊያን ካህናት ከእስራኤል በመጀመሪያው ፓትርያርክ አዛሪያስ መሪነት የመዝሙረኛው ዳዊት የወንድም ልጅ ሳቤቅ ጨምሮ ወደ ኢትዮጵያ ታቦተ ጽዮንን ተከትለው ከመጡት አስራ ሁለት ሺህ ነገደ እስራል ሁለት ሺህ አመስት መቶዎቹ ተከዜን ተሻግረው ወደ አምሐራ ሳይንት መጡ።ሊቀ ካህን አዛርያስ በጣና ቂርቆስ ሊቀካህን በመሆን መንፈሳ አገልግሎት ሰጥተዋል።ዛሬም ድረስ አራት ማዕዘን ቅርጽ ያለውና ከአናቱ ላይ እንደ ሙቀጫ የተቦረቦረው ድንጋይ ለዚህ ህያው ማሳያ ነው።የኦሪታውያን የብረት መስዋዕት ማቃጠያም ይገኛል።
*የጣና ቂርቆስ ገዳም ለሙሴ የተሰጠው የቃል ኪዳን ታቦቱ 800 ዓመት ቆይታበታለች።እንደገና ድንግል ማርያም ልጇን ይዛ ወደ ምድረ ግብጽ በተሰደደችበት ወቅት ለ3 ወራት ከ10 ቀን በዚሁ ገዳም ከልጇ ጋር ቆይተውበታል።ድንግል ማርያም በገዳሙ የነበራትን ቆይታ አጠናቃ ስትመለስ “ፀአና በደመና” በደመና ጫናት የተባለው በጊዜ ብዛት ለአሁኑ የሀይቁ መጠሪያ ስም “ጣና” መሰረት ሆኗል።
7.ቅዱስ ያሬድ የመጀመሪያውን የዜማ መጽሐፉን የፃፈውና ብዙ ተግባራትን ለመከወን የመረጠው ጣና ቂርቆስን ነው፡፡መጽሐፍ ሲጽፍ ለጥቁርና ቀይ ቀለማት መበጥበጫነት ይጠቀምባቸው የነበሩ ከድንጋይ ተቦርቡረው የተሠሩ ጉድጓዶች፣የቅዱስ ያሬድ ድጓና ካባ በገዳሙ ይገኛሉ።
9.ግማደ መስቀሉ የሚገኘው ቤተ-አምሓራ ግሼ ነው።መስቀሉን ከግብፅ በሰሜን ጎንደር በስናር በኩል ወደ ተጉለት (ሸዋ) ያስመጡት የበረራን ወይንም የአዲስአበባን ከተማ የቆረቋሯት ቀዳማዊ ዐፄ ዳዊት ናቸው።መስቀሉን በመስቀለኛ ቦታ በግሼ ተራራ ያስቀመጠው ደግሞ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ነው።
10. ቅዱስ ኡራኤል የጌታን ደም የረጨበት የሚገኘው ሰሜን ሸዋ መንዝ ነው።ቅዱስ ኡራኤል የክርስቶስን ደም የረጨበትን ጽዋ የሰወረው መንዝ እመጓ ቆጵሮስ ተራራ ላይ ነው።የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰይፍ የተሰወረው፣
ቅዱስ ጊዮርጊስ ያረፈው፣የቅዱስ ጊዮርጊስ የፈረሱ አሻራ ኮቲ የሚገኘው ከዚሁ ቆጵሮስ ተራራ ነው።
ዋቢዎች፦
1.የጎንደር ታሪክ ያሬድ ግርማ ሃይሌ 1999 ዓ.ም.
2.የ5000 ዘመነ ታሪክ ከኖኅ እስከ ኢህአዴግ መጵሐፍ 1 ፍስሐ ያዜ 2010 ዓ.ም.
3.መጽሐፍ ቅዱስ 81 መጽሐፍ 1980 ዓ.ም.በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር
4.ገድለ አዳም ማሕበረ ቅዱሳን 2008 ዓ.ም.
5.አኤል ታማክ በጥጋቡ ተፈሪ 2011 ዓ.ም.
6.መፅሐፈ ሰዋሰው ወግስ መዝገበ ቃላት ሐዲስ-በአለቃ ኪ/ወልድ
7.የኢትዮጵያ የ5ሺህ ዓመት ታሪክ-ፍስሐ ያዜ 2003 ዓ.ም
8.የዓለም ታሪክ -አቶ ዮሐንስ ወልደ ማርያም 1936 ዓ.ም
9.ስለ ቅዱሳት መጻህፍትና ሳንስ ስምምነት-ዶ/ር ሄሪ ሪመር-ትርጉም በጎበዜ ጣፈጠ 1953 ዓ.ም
10.Percy Horace Gordon Powell
Cotton፣ A sporting trip through Abyssinia a narrative of a nine month' journey from the plains of the Hawash to the snows of Simien፣ 1902
11.አእምሮ ንጉሴ,ጥንታዊ የኢትዮጵያ የሰላም ጥበቃ ታሪክ ,ከቅራት-ዘመናዊ ፖሊስ፣2000 ዓ.ም
*በቅርቡ በ YouTube ቻናል ስለምንመጣ ፕሮግራም እንዳያልፋችሁ subscribe በማድረግ ቤተሰብ ሁኑ።
https://www.youtube.com/channel/UC6m-V3zA2xrlwPPWtXLJ33A