ይኩኖ አምላክ.....
*ይኩኖ አምላክ የአማርኛን ቋንቋ ብሄራዊ ቋንቋ እንዲሆን በይፋ ያወጀ፥ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥትን ያስቀጠለ የአማሮች አባት ነው።ይኩኖ አምላክ ከዛግዌ ዘመነ መንግሥት በኋላ በስደት የቀጠለው የአኩስም መንግሥት ዘር ነው።በስደት የቀጠለው የአኩስም ዘር፦
1.ማኅበረ ውድም
2.አግብአ ጽዮን
3.ጽንፈ አርአድ
4.ነጋሽ ዛሬ
5.አስፍሕ
6.ያዕቆብ
7.ባሕር አስገድ
8.እድም አስገድ
9.ተስፋ ኢየሱስ
10.ይኩኖ አምላክ ናቸው።
*ከላይ የዘረዘርናቸው የአኩስም ነገሥታት የአንበሳ ውድም የልጅ ልጆች በድልነዓድ ዘመነ መንግሥት ሥልጣን ወደ ሮሐ ከተዛወረ በኋላ የአገው ነገሥት 330 አመት ኢትዮጵያን ሲገዙ በስደት በተለይም በመንዝ በዱርና በዋሻ እየተደበቁ ዘመናትን አሳልፈዋል።
*የቤተ አምሓራ-አምባሰል ገዥ የነበረው እድም አስገድ ገድለ አቡነ ዜና ማርቆስ ላይ እንደተገለጠው የወግዳ ገዥ የማቴዎስን ልጅ እምነ ጽዮንን አግብቶ መቆናኛ (ሰገራት) ሲኖር ቀስውጦስ፣ተስፋ ኢየሱስን፣ገብረ ክርስቶስን፣
እና ሴት ልጃቸውን ማርያም ዘመዳን ወለደ።ቀስውጦስ በስብከተ ወንጌል ተሠማራ፥ገብረ ክርስቶስ ዘቢታንያን የዳግና ገብረ ክርስቶስ ገዳም መሠረተ፥ማርያም ዘመዳ ታዋቂውን አቡነ ዜና ማርቆስ ወለደች።
*ተስፋ ኢየሱስ የቤተ አምሓራ ገዥ ለነበረው አዛዥ ክላ አገልጋይ ነበረ።ተስፋ ኢየሱስ ይኖር የነበረው ሰገራት ውስጥ መሆነኛ ሲሆን ይኩኖ አምላክ የተወለደውም ከዚሁ መሆነኛ ልዩ ቦታው "ፍላጎ"ከተባለች ቦታ ላይ ነው።የአቡነ ኢየሱስ ሞዓ ገድል ይኼን ያረጋግጣል።አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ከይኩኖ አምላክ ጋርም ይዛመዳሉ።
*መሆነኛ የሚባለው አካባቢ ከኩታበር ከተማ በስተደቡብ ያለው ተራራ ነው።ዛሬም ዛሬም "ቤተ መንግሥት፣አማራ ሰፈር፣ አማራ መስፈሪያ፣ አማራ ካብ"በመባል የሚጠሩ ሰፈሮች አሉ፡፡“ሰገራት” ደግሞ አሁን ከኩታበር ሰሜን ምእራብ አቅጣጫ የሚገኝ አካባቢ ነዉ፡፡ ከየቁንባ ጀምሮ እስከ ንፋሳት ገደማ ሰገራት በመባል አሁንም ይጠራል፡፡
*ይኩኖ አምላክ ነአኩቶ ለአብ ደግፎ ስለተዋጋ በይትባረክ መሎጥ ላይ ታስሮ ከእስርቤት ቤት ከአመለጠ በኋላ ወደተማረበት ሐይቅ ገዳም መምህር ኢየሱስ ሞዓ ዘንድ መጥቶ በዚያም የቤተ አምሐራን ሕዝብ አደራጅቶ ከፍተኛ ትግል በማድረግ የዛግዌውን ይትባረክን ሐምሌ 7 ቀን 1263 ዓ.ም.ጣና አካባቢ ጦርነት ገጥሞ ከአሸነፈው በኋላ በአማራ ግዛት በምትገኘው ግሼን ላይ በሺህ የሚቆጠር ሕዝብ በተገኘበት በ1263 ዓ.ም.ነገሠ።
*ጉሣዊ ርዕሳቸውም "ሞዓ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ" ተባለ፥ ስማቸው ዐፄ ይኩኖ አምላክ በሚል የግዕዝ ስም ተሰጣቸው፥ትርጓሜው "አምላክ ጠባቂና ረዳት ይሁነው"ማለት ሲሆን መንግሥቱም ከሮሐ ወደ ተጉለት፣ከዛግዌ ወደ ቤተ አምሐራ ፣ከነአኩቶ ለአብ ወደ ይኩኖ አምላክ ተዛወረ።
*ይኩኖ አምላክ በወርቅ ዙፋን ሲቀመጥ የዛግዌ ዘር መስፍን በብር ዙፋን አስቀምጦ ከግብር ነጻ በማድረግ በላስታና በዋግ ሾማቸው።ይኩኖ አምላክ የመጀመሪያ መናገሻውን ያደረገው አማራ ሳይንት ተድባበ ማርያም አካባቢ ደብረ ታቦር ተራራ ላይ ሲሆን በዛግዌ ዘመነ መንግሥት የሠራዊቱና የሕዝቡ ቋንቋ የነበረውን አማርኛን በይፋ ብሔራዊ ቋንቋ እንዲሆን አወጀ።ከዚህ ዘመን ጀምሮ አማርኛ ቋንቋ በሥነ ጽሑፍ ሕዳሴው ዘመን የበለጠ ተስፋፋ፤የመንግሥትገዥዎች፥አስተዳዳሪዎች፥የጦር መሪዎች እና አስተማሪዎች የማዕረግ ስማቸው በአማርኛ ሆነ።
*ለዐፄ ይኩኖ አምላክ ወደ ሥልጣን መምጣት ቁልፍ ሰው የነበሩት አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ናቸው።ከእርሳቸው ሲማር እውቀትና እውቅና አግኝቷል።በኋላም ከመሎጥ እስርቤት አምልጦ አማራን ማደራጀት የጀመረው ሐይቅ ላይ ነበረ።ይህን የሐይቅ ገዳም ውለታ ለመመለስ ይኩኖ አምላክ አምስት ዐንቀጽ ያለው ዐዋጅ ዐውጆ ነበር።ይህም ዐዋጅ፦
1.የንጉሥ ደብዳቤ ሲላክ መነኮሳቱ ተቀምጠው እንዲሰሙ
2.በተሰጠው ጉልት የነገሥታቱ ልጆች እንዳይገቡበት፣
3.ገዳሙ የተማጽኖ ገዳም እንዲሆን
4.የገዳሙን ርስት ማንም ትውልድ ቆጥሮ እንዳይካፈለውና
5.መነኩሴ ላልሆነ ሰው የገዳሙ ርስት እንዳይሰጥ የሚገልጡ ናቸው።በዚህም ምክንያት ዐቃቤ ሰዓትነት እስከ 16ኛው መክዘ አጋማሽ ድረስ በሐይቅ እስጢፋኖስ አበ ምኔቶች እጅ ቆይቷል።ዐቃቤ ሰዓትነት በቤተመንግሥት ክሀነቱ ጉዳዮች ላይ የመወሰንና የንጉሡን የመገናኛ ሰዓት የመወሰን ሥልጣን ነበረው።
*ይኩኖ አምላክ እንደነገሠ ከየመንና ከግብፅ ሡልጣኖች ጋር ግንኙነት አድርጓል።በግብፅ ሳራካኖች የየብስና የባህር መተላለፊያዎች ሲዘጉ ከ1250 ዓ.ም.ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ ጳጳስ ባለመምጣቱ ጳጳስ እንዲላክላቸው በነገሡበት አመት በ1263 ዓ.ም.ለግብፅ ሡልጣን ባይባራስ (1253-70 ዓ.ም) በየመኑ ገዥ አል ማሊክ አል ሙዘፋር በኩል ደብዳቤ ልከው እንደነበር ተረጋግጧል።የየመኑ ገዥ ደብዳቤውን ወደ ካይሮ ልኮ የይኩኖ አምላክን መልእክተኞች ግን በየመን አቆያቸው።በዚህም ምክንያት ባይባራስ ደብዳቤው እንጂ ጉዳዩን የሚያስረዱ መልእክተኞች አልመጡም ብሎ መልሶታል።
*ይኩኖ አምላክ ኢትዮጵያ ጳጳስ እንዲኖራት ከነበራቸው ከፍተኛ ጉጉት የተነሳ እንደገና በኢየሩሳሌም በኩል ወደ አንጾኪያ-ሶርያ እና ለቆስጥንጥንያው ንጉሥ ሚካኤል ፓሌዎሎግ 8ኛ ከቀጭኔ ገጸ-በረከት ጋር ደብዳቤ መላካቸው ታውቋል።ይኩኖ አምላክ ወደ ካይሮ፥ሶርያ እና ቆስጠንጢኒያ የላኩት ደብዳቤ ምንም እንኳን አንዳንድ መረጃዎች ከአንጾኪያ ጳጳስት ተልኮላቸዋል ቢሉም በልጃቸው ዐፄ ውድም ረዓድ በ1306 ዓ.ም.መጨረሻ ከእስክንድርያ አቡነ ዮሐንስ ሁለተኛ የተባሉ ጳጳስ ተልኳል።
*ይኩኖ አምላክ በውጭ ግንኙነት በኩል እንደልፋታቸው ጳጳስ ባይመጣላቸውም በላሊበላ አቅራቢያ የጨረቃ ተራራ በመባል በሚታወቀው አቡነ ዮሴፍ ተራራ ላይ ቋጥኝ አስፈልፍለው ያሳነጿት ገነተ ማርያም መታወቂያቸው ናት።ደጇፏ ላይም የይኩኖ አምላክ ፊርማ እና የእጅ ጽሑፋቸው ይገኛል።በኋላም ቤተ መንግሥቱን ከሳይንት ወደ ተጉለት እንዳዛወሩት ታውቋል።አንድ መግቢያ በር ያላት ተጉለት (ሰወን፥ጸወን፥ማረዴ)፣መንዝ የአኩስም ነገሥታት መደበቂያ፥የዐፄ ልብነ ድንግል ልጅ አቤቶ ያዕቆብ መሸሸጊያ በጥቅሉ የአማርኛ መዳኛ ቁልፍ ቦታ ናቸው።ተጉለት የዐፄ ዓምደ ጽዮን፥ዐፄ ይሥሐቅና የሌሎችም የአማራ ነገሥታት መቀመጫም ነበረች።
*ዐፄ ይኩኖ አምላክ በጥቅሉ ሲገለጥ ሐይቅ ገዳም ተማረ፥የአማራን ሕዝብ አደራጅቶ የዛግዌውን ይትባረክ ከሥልጣን በማስገወድ ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥትን ሐምሌ 7 ቀን 1263 ዓ.ም.አስመለሰ፥የአማርኛን ቋንቋ ብሔራዊ ቋንቋ እንዲህን በይፋ አወጀ፥ወደ ግብፅ፥ሶርያና ቆስጠንጢንያ ደብዳቤ ላከ፥ገነተ ማርያምን አሳነጸ፥ቤተ መንግሥቱን ወደ ተጉለት አዛወረ፥ያግብዐ ጽዮንን ወለደ፥በመጨረሻም ሰኔ 16 ቀን 1277 ዓ.ም.ሞተ።ዐጽመም በዐፄ በዕደ ማርያም ዘመን በ1461 ዓ.ም.ተወስዶ አትሮንስ ማርያም አረፈ።
ዋቢ፦
1.ገድለ አቡነ ዜና ማርቆስ
2.ገድለ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ
3.ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ፣ባሕረ ሐሳብ፣232-233
4.ዳንኤል ክብረት፣የቤተ ክርስቲያን መረጃዎች፣48-49፣አራቱ ኃያላን,፣70
5.vantini፣494-5፣
6.tadese tamrat,Church and state,162፣
7.Pankhurst, Across the red sea,403)
8.A History of Ethiopia: Nubia and Abyssinia, 1928 (Oosterhout, the Netherlands: Anthropological Publications, 1970)፣285)