#𝘿𝙖𝙧𝙠 𝙥𝙨𝙮𝙘𝙝𝙤𝙡𝙤𝙜𝙮 𝙩rics
ባለፈው እንደተናገርኩት በአጭሩ 𝙙𝙖𝙧𝙠 𝙥𝙨𝙮𝙘𝙝𝙤𝙡𝙤𝙜𝙮 ማለት ሰዎች ሌሎችን እንዴት ያለ ፍላጎታቸው እንደሚቆጣጠሩዋቸው እና ተጽእኖ እንደሚያሳድሩባቸው የማወቅ ዘዴ ነው። እና ይህ #𝙙𝙖𝙧𝙠 𝙥𝙨𝙮𝙘𝙝𝙤𝙡𝙤𝙜𝙮 ደግሞ በውስጡ ብዙ ቴክኒኮችን ይይዛል ነገር ግን ዋና ዋና የምንላቸውን እንመልከት
1,#𝙈𝙖𝙣𝙞𝙥𝙪𝙡𝙖𝙩𝙞𝙤𝙣 :ይህ መንገድ ውሸቶችን እና ማታለሎችን በመጠቀም የአንድን ሰው ሀሳብ፣ ወሳኔ እንዲሁም እንቅስቃሴ የመቆጣጠር ሂደት ነው።
#ለምሳሌ: ገበያ ውስጥ አንድ ነጋዴ በሱቅ ውስጥ ብዙ እያለው እንኳን "ይህ እቃ የመጨረሻው ዕቃ ነው ብትገዙት ይሻላል ሌላ ሰው ከሚወስደው" ሊላቹ ይችላል ይህ እናንተ አአምሮ ውስጥ አስቸኳይ እንደሆነ እንድታስቡ እና ቶሎ ውሳኔ እንድትሰጡ ያደርጋቹዋል።
2,#𝙂𝙖𝙨𝙡𝙞𝙜𝙝𝙩𝙞𝙣𝙜: ይሄ ደግሞ አንድ ሰው ስተናገረው ወይም ስላደረገው ነገር እንዲጠራጠር ማድረግ ነው፤ ማለትም ትውስታውን ማሳጣት ወይም ማደናገር እና በራሱ ግራ እንዲጋባ ማድረግ ነው።
#ለምሳሌ: ለጓደኛቹ የሆነ መጽሐፍ ሰጥታቹት እንዲመልስላቹ ብትጠይቁት እና "በፍጹም ለእኔ አልሰጠኽኝም ምናልባት ተሳስተህ/በሀሳብህ ይሆናል" ብሎ ቢመልስላቹ ሳትፈልጉት ትውስታቹን መጠራጠር ትጀምራላቹ።
3,#𝙉𝙖𝙧𝙘𝙞𝙨𝙨𝙞𝙨𝙢 : ይህ ደግሞ አንዳንድ ሰዎች ከፍተኛ የሆነ በራስ መተማመን ሲኖራቸው እና የሌሎችን ስራ ራሳቸው እንደሰሩት በማድረግ የሚያቀርቡ /ለራሳቸው ዓላማ የሌሎችን ጉልበት፣ አአምሮ የሚጠቁሙ ናቸው።
#ምሳሌ፦ በስራ ላይ ሁላቹም በጋራ ተጠባቹ የሰራቹትን ስራ አንዱ ከመሀላቹ ተነስቶ ለአለቃቹ "ይህን ሀሳብ ያመጣሁት እኔ ነኝ" በማለት ሊነግረው ይችላል በዚህም የሚፈልገውን ዕድገት ሊያገኝ ይችላል።
4,#𝙀𝙢𝙤𝙩𝙞𝙤𝙣𝙖𝙡 𝙗𝙡𝙖𝙘𝙠𝙢𝙖𝙞𝙡 ፦ አንድን ሰው ለማስገደድ/ለመጫን/ ወይም የምትፈልጉትን እንዲያደርግ ፍርሃትን፣የጥፋተኝነት ስሜትን እንዲሁም ማስፈራሪያን መጠቀም ነው።
#ምሳሌ፦ሚስትህ/ 𝙨𝙤𝙢𝙤𝙣𝙚 "ብር የማትልክልኝ ከሆነ ለቤተሰቦች ግድ እንደማይሰጥህ ለሁሉም እናገራለው" ቢላቹ የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማቹ እያደረጓቹ ነው።
የቀሩትን ሌሎች ክፍሎች በቀጣይ እናይ እና እንዴት ቴክኒኮቹን ለራሳችን እንደምንጠቀመው አሳያቸዋለሁ ግን ልብ እንድትሉ የምፈልገው ነገር እነዚህ የሰጠኋቹ ምሳሌዎች ሀሳቡን ለመረዳት ቀላል ስለሆኑ እንጂ መንገዶቹ በጣም አደገኛ እና ሰዎችን እስከማሳበድ፣ ራስን አስከማጥፋት፣ እንዲሁም አንድሰው ላይ ጥገኛ ሆነው የህይወት ዘመናቸውን እንዲጨርሱ የሚያደርጉ ናቸው። ስለዚህ ስንጠቀምባቸው ሰዎችን በማይጎዳ መልኩ መሆን አለበት።
@ethioplotቻናሉን ለጓደኞቻቹ #ሼር ማድረግ አትርሱ