በ1.2 ሚሊዮን በላይ LED ስለታጀበው እና አጠቃላይ ስፋቱ ከአስር የኳስ ሜዳዎች ስለሚበልጠው sphere ስለሚባለው አዳራሽ ሰምታችኋል???👇👇
ወትሮም በቅንጡ እና እጅግ ዘመናዊ ህንፃዎች የምትታዎቀው የሀገረ አሜሪካዋ Las Vegas ውስጥ የተገነባው የክብ ቅርፅ ያለው ሕንፃ የሰሞኑ መነጋገሪያ መሆን ችሏል።
ለመገንባት በአጠቃላይ ከ2.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ የፈጀ ሲሆን ይህም በአለም ላይ ካሉ ህንፃዎች በጣም ውዱ ያደርገዋል።
ይህን ህንፃ ከሌሎቹ የሚለየው ውድ መሆኑ ብቻ አይደለም። ይልቁንስ ህንፃውን ለመስራት ጥቅም ላይ የዋለው የቴክኖሎጅና የኢንጅነሪንግ ጥበብ እንጅ። ክቡ አዳራሽ 54 ሺህ ካሬ ሜትር(ወይንም 10 የኳስ ሜዳዎችን የሚያክል ስፋት ያለው) HD ቪድዮ ማጫዎት የሚችል ስክሪን የለበሰ ሲሆን ይህም ስክሪን ከ50 ሜትር ርቀት ላይ በአሁኑ ሰዓት ከ30cm ርቀት ከፍተኛ የምስል ጥራት ከሚሰጠው የapple Tab በብዙ እጥፍ የተሻለ የምስል ጥራት ይሰጣል።
አዳራሹ 18 ሺህ ሰዎችን መያዝ የሚችል ሲሆን 15ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት ያለው 360 ድግሪ እይታን የሚሰጥ ባለ 16K HD ስክሪን በውስጥ በኩል ተገጥሞለታል።
የተራቀቀ ሳዉንድ ኢንጅነሪንግ ጥቅም ላይ የዋለበት ይህ አዳራሽ በአጠቃላይ 167 ሺህ ስፒከሮች ከስክሪኑ ጀርባ ተገጥመውለታል። እንደ ባለሙያዎቹ ገለፃ ለእያንዳንዱ ታዳሚ የHead Phone ጥራት ያለው ድምፅ የሚያደርስ ሲሆን ይህም ማለት ለእያንዳንዱ ታዳሚ የ8 ስፒከሮች ድምፅ ይደርሰዋል እንደማለት ነው። ሌላው አስደናቂ ነገር ጎን ለጎን የተቀመጡ ሁለት ሰዎች አንዱ አንዱን ሳይረብሸው ሁለት የተለያየ ቋንቋ መስማት እንዲችሉ ማድረጉ ነው።
አዳራሹ ከውጭ ባለው ስክሪኑ በኩል ውስጥ ላይ ያሉትን ትዕይንቶች እንዲሁም የተለያዩ ክብ ቅርፅ ያላቸውን እንደ ኢሞጅ አይነት ምስሎች በማራኪ ሁኔታ ማሳየት ይችላል።
በአጠቃላይ ህንፃው ታዳሚዎች አዳራሽ ውስጥ ያሉ እስከማይመስላቸው ድረስ ስሜትን መቆጣጠር የሚችሉ ቴክኖሎጅዎች የተገጠሙለት ሲሆን ባለሙያዎቹ ህንፃውን ለመስራት ወደ ኋላም ወደፊትም ያሉ የፊዚክስ ቀመሮችን መጠቀማቸውን ተናግረዋል።
ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናሉን share ማድረግዎን እንዳይረሱ።🙏🙏🙏
@ethiotecchtalk